“Our true nationality is mankind.”H.G.

ሽፈራው ሽጉጤ መጡ – ተወዳዳሪዎቹ ተለዩ፤ የኦህዴድና ብአዴን ክንድ አብዛኛው የሸንጎው ይዞ ኢህአዴግን መለየት ነው

በህወሃትም በኩል እሳቸውን ወደ ፊት ለማምጣት ፍላጎት አለ። ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የኢህአዴግ ምክር ቤት የድርጀቱን ሊቀመንበር ሲመርጥ ህወሃትና ደህዴን ሙሉ ድምጽ ያላቸውን ድምጽ አንድ ላይ አስደምረው ከብአዴን የተወሰነ ድምጽ ስለሚያገኙ ኦህዴድን ያሸንፉታል።

የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ደህዴንን እንዲመሩ ተመርጠዋል። የመከላከያ ሚኒስትርና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈጻሚ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ምክትል ተደርገዋል። በዚሁ መሰረት የጠቅላይ ሚኒስርነቱን ቦታ ለመያዝ የሚወዳደሩት አራት እጩዎች ይፋ ሆነዋል።

ኢህአዴግ ” አለኝ” በሚለው የቀድሞው ባህሉ መሰረት ነገሮች በዝግ ስብሰባ ተወስነው እዛው የሚጠናቀቁበት ሁኔታ ብዙም የሚሰራ አልሆነም። ልክ እንደ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ ውዝግብ የጠቅላዩ ሩጫ ክረት አስገራሚ ሆኗል። አስተያየት የሚሰጡ እንደሚሉት ፍትጊያው ኢህአዴግ የውስጥ ችግሩ የከፋ መሆኑን አመላካች ነው።

የህወሃት ደጋፊ የሆኑ መጨረሻ ላይ እናየዋለን ሲሉ በድርጅታቸው ኢህአዴግ ላይ ያላቸውን እምነት እየገለጹ ነው። የሌሎች እህት ፓርቲ ደጋፊዎች ግን ይህን ያህል የጎላ ይድጋፍና የተቃውሞ ዘመቻ ውስጥ ባይገቡም ኦህዴድ ግን ላቀረበው እጩ በገሃድ እየተሟገተ፣ የማስተዋወቂያ ስራ እየሰራ፣ ኢትዮጵያን እንደ አገር መምራት የሚችል ብቃት ያለው ሰው ማቅረቡን ይፋ እያስታወቀ ሲሆን፣ በማህበራዊ ሚዲያ ከውስጥም ከውጭም ቀላል የማይባል ድጋፍ እየጎረፈለትም ነው።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

አሁን ባለው ይፋዊ መረጃ መሰረት አቶ ደመቀ መኮንን ” የተፈተኑ ” በሚል ውዳሴ እየተሰጣቸው ሲሆን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑም እሳቸውን ያስቀድማሉ። በህወሃትም በኩል እሳቸውን ወደ ፊት ለማምጣት ፍላጎት አለ። ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የኢህአዴግ ምክር ቤት የድርጀቱን ሊቀመንበር ሲመርጥ ህወሃትና ደህዴን ያላቸውን ድምጽ አንድ ላይ አስደምረው ከብአዴን የተወሰነ ድምጽ ስለሚያገኙ ኦህዴድን ያሸንፉታል።

ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት በብአዴን ውስጥ አንዳችም ለውጥ ሳይደረግ የታለፈው ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግና አስተማማኝ ድምጽ ከወዲሁ ለማግኘት መሆኑንን ይናገራሉ። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት አቶ ሃይለማሪያም በፓርቲያቸው ሲገመገሙ ” እንደንገፋ አድርገኸናል” በሚል በመሆኑ፣ ደህዴን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያጣውን ቦታ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመያዝ ሲል አቶ ደመቀን ይደግፋል። አቶ ሽፈራው በተለያዩ ከኪስ ጋር በተያያዘ ግምገማና በብልሹ አሰራር አቶ ሃይለማሪያም ከክልሉ እንዳነሷቸው፣ በዚህም የሲዳማ ህዝብ ማኩረፉ በወቅቱ መዘገቡ አይዘነጋም። ዛሬ ያ የተገመገሙበት የቡና ንግድ ጉዳይ የት ተጥሎ ሃላፊ ሆነው እንደመጡ ውሎ አነጋጋሪ እንደሚሆን ነው። አቶ ሽፈራው ከጉራፈርዳ በተፈናቀሉ አማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ለደረሰው የማያሽር ጠባሳ አመራር በመስጠት ሊጠየቁ ሲገባቸው አቶ መለስ ከለላ ሆነውላቸው መታለፋቸው አይዘነጋም።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

የኦህዴድ ወኪል ላይ ከየአቅጣጫው የተጀመረው የማጠልሸት ዘመቻ ምን ያህል እውነት መሆኑ ውሎ አድሮ የሚጸዳ ቢሆንም፣ አማራ ክልል ለአቶ ሽፈራው ድምጽ የሚሰጥ ከሆነ እስከዛሬ በህዝቡ ላይ ከፈጸመው ክህደት ሁሉ የከፋ እንደሚሆን ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ እየገለጹ ነው። ምንም እንኳ አማርኛ ተናጋሪው ህዝብ ” በነፍጠኛነት” ከተፈረጀ ወዲህ አንድ ሆኖ የሚታገልለት ድርጅት ለማግኘት ባይታደልም በጉራ ፈርዳ ለአንደኛ ክፍል ተማሪ የተጻፈው ” አገራችንን ለቀህ ውጣ” የሚለው ደብዳቤ ከአእምሯቸው ሊወጣ እንደማይችል እነዚሁ ክፍሎች ያስታውሳሉ።

በዚሁ መነሻ ኦህዴድ ያሰበውን ለማሳካት በፓርላማ ደረጃ ባሉት አባሎቹ አማካይነት አስገዳጅ አቋም ሊይዝ ማሰቡ አንዳንድ መረጃዎች ሽው እያሉ ነው። በአማራ ክልልም ደስተኛ ያልሆኑ ያፓርላማ አባላት ድጋፍ የሚያደርጉበት አግባብ ከተፈጠረ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢህአዴግ ምክር ቤት ተወስኖ የመጣውን ውሳኔ ባለመቀበል፣ ቦይ ኮት በማድረግ ታሪክ ሊያስመዘግብ እንደሚችል ማስታወቂያዎችም እየተበተኑ ነው። አሁን አገሪቱ ካለችበት የፖለቲካ አጣብቂኝ አንጻር፣ ይህንኑ አጣብቂኝ ለማለፍ በተወሰዱ የሃይል እርምጃዎች በርካታ ህይወት ማለፉ፣ እጅግ የበዛው ነብስ የጠፋው ደግሞ ከኦሮሚያና ከአማራ መሆኑ ሁለቱን ክልሎች ሊያያዝ እንደሚችልም ግምት አለ። በሌላ ወገን ደግሞ አስቸኳይ አዋጁ ጥሩ ታኮ ስለሆነ ምንም አያመጡም። ሁሉም ይሰክናሉ የሚሉም አሉ። የሰሞኑንን የአስቸኳይ አዋጁን መጣስ የሚያዩ ችግሩ እንዳይባባስ ያሳስባሉ። ችግሩ ወደ ባሰበት ቀውስ እንዳያመራም ፍራሃቻቸውን ይገልጻሉ። ለማንኛውም ግን የፊታችን አርብ አስቸኳይ የተጠራው ሸንጎ የሚለው ይሰማል። በቅርቡ ሽንጎው ሲያንገራግርና ውሳኔ ለመውሰን አንድ በሚያዳግት መልኩ ስብሰባ መቅረቱን ሪፖርተር በምስል አስደግፎ መዘገቡ ይታወሳል።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0