ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃላፊዎች ጋር የተደረገውን ውይይት በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ መልካም እንደነበር በማመልከት የሚጀምረው የአሜሪካን ኤምባሲ ቃል አቀባይ መግለጫ፣ የአስቸኳይ አዋጁን በብርቱ እንደሚቃወም ይፋ ባደረገው አቋሙ ግን ፍንክች ሳይ እንደሚጸና ነው ያስረገጡት። ኤች አር 128 አስፈሪ ሆኗል።


ሪፖርተር የካቲት 21 ቀን 2018 ” መንግሥት የአሜሪካ ኤምባሲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ላወጣው መግለጫ ማብራሪያ ጠየቀ” በሚል ርዕስ ስር የተባለውን ሲያስተባብል ” በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክል ሬነር ያልተናገሩት፣ የአሜሪካንም አቋም ያልሆነ” ነው ያለው።
ሪፖርተር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምንጮቹን በመጥቀስ አምባሳደሩ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ማብራሪያ እንዲሰጡ ታዘው ነበር። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክቶ አሜሪካ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መቃወሟን ተከትሎ አምባሳደሩ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ” አምባሳደሩም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ሐሳብ እንደሚረዱና አስተያየታቸውም በአሉታዊ ከማሰብ እንዳልሆነ መግለጻቸውን፣ ወደፊት በመመካከር ለመሥራት ፍላጎታቸው እንደሆነ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል ” በማለት ሪፖርተር የዘገበውን ነው ” ሃሰት፤ እንደዚህ አልተባለም” በሚል ያስተባበሉት።
አሜሪካ ወደፌት በመመካከር ለመስራት ፈቃደኛ እንደሆነች ያነሱት አስቸኳይ አውጁን አስመልክቶ የተያዘውንጠንካራ አቋም ለማለዘብ እንዳልሆነ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት የኤምባሲው ቃል አቀባይ ኒኮላስ ባርኔት ናቸው።
ቃል አቀባዩ ስብሰባው ማብራሪያ የመስጠና አሜሪካ በያዘችው አቋም ላይ የመናዘዝ ሳይሆን የግል እንደሆነና በግል በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ አስተያየት አንደማይሰጥ ነው የጠቆሙት። “እናም” አሉ ቃል አቀባዩ በሪፖርተር ማለታቸው ነው “የተጠቀሰው ኤምባሲውን አይገልጽም”
ዜናውን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ቃል አቀባይ ማነጋገር አልተቻለም። ዜናውን አዲስ አበባ ሆኖ ያደራጀው እስክንድር ፍሬው እንዳለው። እስክንድር በተደጋጋሚ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለምን በተደጋጋሚ ከአገር ውጭም ሆነ አገር ውስጥ ለማነጋገር የማይችገር መሆኑ ከዚህ ቀደም ያቀረባቸው ዜናዎች ምስክር ናቸው። በዚህኛው ዘገባ ቃል አቀባዩ ወይም ምክትላቸው ለምን ምላሽ እንዳልሰጡ የተባለ ነገር የለም።
አሜሪካ ፈርጣማ አቋም መያዟዋ በአስቸኳይ አዋጁ ብቻ ሳይሆን ነገ ለውሳኔ ሃሳብ ይቀርባል የተባለውን ኤችአር 128 ህግም የሚገለጽ ነው። በተለይም በህጉ የተካተተው የሰብአዊ መብት ጥሰዋል የተባሉ ሃላፊዎችን በዓለም አቀፍ ህግ የሚያስጠይቅ፣ በየትኛውም ቦታ ያለ ንብረትን የሚያግድ፣ የባለስልጣናትን ጉዞ የሚያግድ እና እስከ ቤተሰብ ድረስ የሚዘልቅ ማእቀፍ ያለው ይህ ረቂቅ ከወዲሁ ከፍተኛ ፍርሃቻ መፍጠሩ ይታወቃል።

የኤች.አር. 128 አስገዳጅ ህግ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ የህሊና እስረኞች፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም በሐይማኖትና በዘር በማንነታቸው ምክንያት የታሰሩ ወገኖች በሙሉ እንዲለቀቁ የሚያዝ ሲሆን በተለይም የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ድርጅት አጣሪ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ ገብቶ መንግስት በህዝብ ላይ የወሰደዉን ኢሰብአዊ ጭፍጨፋዎች በሙሉ እንዲያጣራ የህወሃት አንጃ ቡድን እንዲፈቅድ ያስጠነቅቃል። ኢህአዴግም ይህንኑ አምኖ የተባበሩት መንግስታት ነጻና ገለልተኛ አጣሪ ቡድን እንዲገባ የሚፈቅድበት የጊዜ ገደብ ዛሬ ነገ የሚያበቃ ይሆናል።

Related stories   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ወሰነ

በባራክ ኦባማ አስተዳደር የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር የነበሩት ቶም ማሊኖውስኪ “አገሪቱ አሁን ያለችበት ሂደት በእሳት ላይ ተጥዶ እንደሚንተከተክ ማሰሮ ይመስላል። እናም እንዲህ የሚንተከተክ ማሰሮ ለማስተንፈስ ያለው ምርጫ ክዳኑን ማንሳት ብቻ ነው፤ ያ ካልተደረገ መንተከተኩ አያቆምም። በዚያ ከቀጠለ ደግሞ መገንፈሉ አይቀርም። ከዚያ በኋላ የሚሆነው ሁላችንም እናውቀዋለን” ብለው እንደነበር የሚታወስ ነው

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *