ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ 1 (ሀ) መሰረት በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ በ346 ድጋፍ፣ በ88 ተቃውሞ እና በ7 ድምጸ ታእቅቦ አፅድቆታል። ሲል ፋና በሰበር ካበሰረ በሁዋላ ባለሙያዎች ሂሳብ በማስላት አዋጁ የሚፈለገውን ድጋፍ አለማግኘቱን ይፋ ሲያደርጉ  ፓርላማው የቁጥጥር ስህተት ገጥሞኛል…

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የካቲት 6 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ለስድስት ወራት ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፀደቀ።

ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ 1 (ሀ) መሰረት በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ በ346 ድጋፍ፣ በ88 ተቃውሞ እና በ7 ድምጸ ታእቅቦ አፅድቆታል።

ለምክር ቤቱ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ያመለክታል።

መንግስት ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ የመከላከልና የመጠበቅ፣ የአገርን ሰላምና ደህንንነት የማስከበርና የህዝቦችን አንድነትና እኩልነት እውን በማድረግ የዜጎችን በነፃነት የመዘዋወር፣ በመረጡት ቦታ የመኖርና ሀብት የማፍራት ህገ መንግስታዊ መብታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን በመገንዘብ መታወጁም ተጠቅሷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ደህንነት የሚጥስና ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ እየተስፋፋና እየተራዘመ መሄዱ ተነስቷል።

በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ የተነሳ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች መንግስት የህግ ጥበቃና ከለላ እንዲያደርግላቸው መንግስትን በተለያዩ መድረኮች መጠየቃቸውንም ነው መንግስት ከዚህ ቀደም የገለፀው።

በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ላይ የተጋረጠውን ይህን አደጋ በመደበኛው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱንና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመጠበቅ የሚያስችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣት አሰፈላጊ መሆኑ እንደታመነበትም አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የመርማሪ ቦርድ መካከል የስድስቱ አባላት ዝርዝርም ዛሬ ቀርቦለት አጽድቆታል።

Fana B.C

ዜናው ይፋ መሆኑንን ተከትሎ አንቀጽ 93-2 መሰረት የተባለው ድምጽ አለመገኘቱን፣ በዚህም ምክንያት አዋጁ አለመጽደቁን የሚያበስሩ ድምጾች ተሰሙ። እነዚህ ክሎች እንዳሉት ቆጠራው ሲካሄድ በግልጽ አባላቱ እያዩ ነበር። አባላቱ ቀድሞውንም አባዱላ ገመዳ ላይ ስቀዋል። የሳቁትም አዋጁን በስምምነት እናጽድቀው ሲሉ ነው። ከዚህ በሁዋላ ” በድምጽ ይሁን” ሲሉ ” አዎ” የሚል መልስ ከመቅጽበት ተሰጣችው።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ይህንንና የምርጫውን ውጤት አፈ ጉባኤው ሲናገሩ በተደጋጋሚ ያቀረቡት ክፍሎች እንዳመለከቱት የተገኘው ድምጽ 395 መሆኑን የፓርላማው የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ማስተካከያ መስጥታቸውን ይፋ አድርገዋል። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት ይህ ” የቀሽም ሌባ” ተግባር ነው። ይህ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ጀመሮ ሲደነቃቀፍ እዚህ የደረሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሙሉ ድጋፍ እንዲያገኝ የፓርላማ አባላቱ በግልና በቡድን ሲወሰወሱ እንደነበርም ለዋቅ ተችሏል። ሆኖም ግን 95 የኢህአዴግ አባላት ኢህአዴግን መቃወማቸው ከአዋጁ መጽደቅ በላይ ዜና ሆኗል።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

በራሱ በኦህዴድ መካከልና በኢህአዴግ መካከል ያለውን ግንኙነት ፍንትው አድርጎ ያሳየው የተቃውሞ አካሄድ ወዴት ሊአመራ እንደሚችል ባይለይም ስጋት እንደሆነ ግን አያጠራጥርም

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *