ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጊታቸው አምባዬ አሁን በአገሪቱ በተለመደው አግባባ ህግ የሚያስከበር የፌደራልና የክልል መንግስት የለም። በዚህም ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ታውጇል ሲሉ ወታደራዊ አገዛዝ መኖሩን በማመን ደረጃ ማብራሪያ ሰጡ። በአገሪቱ ህግ የለም የሚባልበት ደረጃ መደረሱን አመለከቱ።

በተለያዩ የስልጣን አካላት እና ደጋፊዎች በዚህ መልኩ ትንታኔ ያልተሰጠበትን ጉዳይ አቶ ጌታቸው ብስጭት በተሞላው አነጋገር መናገራቸው አስገራሚ የሆነባቸው ክፍሎች ” በኢትዮጵያ ኩዴታ መካሄዱን አቃቤ ህግ አምኗል” ብለዋል። ሲያብራሩም ” አቶ ጌታቸው እንዳሉት ህግ ማስከበር የሚችል የፌደራልና የክልል መንግስት ከሌለ አገሪቱ የምትመራው በወታደራዊ አገዛዝ ነው ማለት ነው”

አቶ ሃይለማሪያም መልቀቂያ እንዲያስገቡ ከተደረገ በሁዋላ ይፋ የሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤትም ሙሉ ድጋፍ እንዳላገኘ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ነው። በዋናነት ግን ዶክተር ነገሪ ሌንጮና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ አዋጁ እንደማይታወጅ፣ አዋጁን የሚያሳውጅ አንዳችም ምክንያት እንደሌለ እየገለጹ ባለበት ቅጽበት አዋጁ ይፋ መሆኑ ነው።

የፓርላማ አባል.png

ይህ ከፍጥረቱ ጀምሮ ሳንካ እንዳለበት በኦሮሚያ ክልል ድጋፍ ያጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ፓርላማ ሲቀርብ ደግሞ በድራማና ሊታመን በማይችል ተቃውሞ መታጀቡ መጨረሻው ወዴት የሚል ጥያቄ እያስነሳ ነው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሚስጥሩ ገሃድ የሚወጣበት፣ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ቁርስ፣ ምሳና እራት የሆነው ኢህአዴግ፣የፓርላማውን የድምጽ ሂደትና ስሌት በተቃራኒው ይፋ ማደረጉን ተከትሎ የተነሳው መራወጥ ከአዋጁና ከተቃውሞው በላይ አስገራሚ ሆኗል።

የኢህአዴግ አባል የፓርላማ እድምተኞች ምለው ተገዝተው የሚከተሉትን ድርጅታቸውኢህአዴግን አቋም ይዘው በገሃድ ሲቃወሙና ድጋፍ ሲነሱ ይህ በታሪክ የመጀመሪያ ነው። ከመቶ በላይ አባላት ስብሰባው ላይ አልተገኙም። ሰማንያ ስምንቱ ድምጽ ነፍገዋል። ሰባቱ ” የለንበትም” ሲሉ ድምጽ ከተቆጠረና ይፋ ከሆነ በሁዋላ ማሻሻያ ተደርጎ ሰሚን፣ ተመልካችን ግራ ባጋባ መልኩ የአስቸኳይ አዋጁ ማለፉ ታውጇል። አቶ ጌታቸው ወሃ እየተቀዳላቸው በንዴት የሰጡትን አስተያየት እዚህ ላይ ይመልከቱ

 

 

[wpvideo brqmbGIn]

ጋዜጠኛ 395 ይላል። አፈ ጉባኤው 346 ይላል። በአፈጉባኤው ቁጥር አዋጁ ወድቋል። በጋዜጠኛው ቁጥር አልፏል። አፈ ጉባኤው መድረክ ላይ ሆነው የቆጠሩት ያስቆጠሩትና ቃለ ጉባኤውም ላይ የሰፈረው 346 ነው። በድምፅና በቪድዮ የተቀረፀውም 346 ነው። እኩለ ቀን ላይ ለኢትዮፕያ ህዝብ የተነገረውም 346 ነው። ውስጥ የነበሩ ጋዜጠኞችም የመዘገቡት 346 ነው። የቱን እንመን – source FB

Related stories   የአቶ ሽመልስ ንግግር በብልጽግና ስራ አስፈሳሚ በጥለቀት እንዲገመገምና እርምት እንዲወሰድበት ከስምምነት ተደረሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *