ኢህአዴግ የሚያውቀው የኦህዴድ መዋቅር እንደፈረሰ ተመለከት። ለድርጀቱ እጅግ ቅርብ የሆኑ ለዛጎል እንደተናገሩት ” የወታደራዊ ኮማንድ ፖስቱ ካርታ አልባ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው” ለዚህም ምክንያቱ የኦህዴድ የዞን፣ የወራዳና የቀበሌ መዋቅር ሙሉ በሙል ህዝብን ተቀላቅሏል።

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የኦህዴድን መዋቅር ኢህአዴግ ሊቆጣጠረው እንደማይችል የጠቆሙት የዜናው አቀባይ ” አስቸኳይ ልዩና ድፍረት የተሞላው ውሳኔ ግድ ነው” ብለዋል። አሁን ያለው ግንኙነት የፈረሰ ደረጃ ላይ ስላለ መልሶ ለመተገን የሚቻል እንደማይመስላቸው አመልክተዋል። 

እንደ እሳቸው እምነት አሁን የወታደራዊ ኮማንድ ፖስቱ በፈረሰና እዝ ሰንሰለቱ በተበተሰ መዋቅር ውስጥ እየሰራ ነው። በዚሁም ሳቢያ በጥፋት ላይ ጥፋት እየከመረ ለወደፊቱ ሊታረቅ የማይችል ጥፋት ውስጥ ገብቷል። እየተወሰደ ያለው የክፋ እርምጃ የህዝቡን ብቻ ሳይሆን ድፍን የኦህዴድን አባላትና መላክ ካድሬ አስዝኗል። በዚህ መልክ ኢህአዴግ ውስጥ መቀጠል ከባድ ነው። 

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ከበፊቱ የተለየ መረጃ በይፋ ይወጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ያመከቱት የመረጃው አቀባይ “ኦህዴድ የትኛውም ዓይነት የማሻሻያ እርምጃና /ሪፎርም ላድርግ ቢል ህዝብ አይቀበለውም። ገዳይና ተገዳይ ሆኖ በአንድ ፓርቲ ጥላ ስር መቀመጥም አይቻልም፤ ለጊዜው እዚህ ጋር ተደርሷል” ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ለሶስት ቀን የተጠራው አድማ እየተካሄድ መሆኑንን የመንግስት ሚዲያዎች አስታውቀዋል። አስተባባሪዎቹ እንደሚሉት ከዚህ በጠነከረ መልኩ ይቀጥላል። 

Related stories   ኦነግ ሸኔ ከ770 በላይ ገድሏል ከ1300 በላይ አቁስሏል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *