ከተቃዋሚዎች ጋር አብሮ ለመሥራት ጥሪ ማቅረብን እና በኢትዮጵያ የነበረውና ያለው የብሔር ሳይሆን የመደብ ጭቆና ነው የሚል አዲስ አቋም ማንጸባረቅን ጨምሮ ከአራቱ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች መካከል ጠንካራና ትርጉም ያለው መግለጫ ያወጣው ኦህ ዴድ እንደኾነ እናስታውሳለን።

ኦህዴድ በዚያው መግለጫ ላይ፣ በኢህአዴግ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ያለምንም ማቅማማትና ማንገራገር ለማስፈጸም ውሳኔ ማሳለፉም አይዘነጋም። 
ይህን እውነታ እንዳለ አስቀምጠን ወደ ወቅታዊው ጉዳይ ስንመጣ ደግሞ ከአራቱ የኢህ አዴግ ድርጅት ሊቃነ መቃብርት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የይኹንታ ድምጽ ያልሰጠው የኦህዴዱ ዶክተር አብይ አሕመድ ብቻ ነው። የህወኃቱ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ የብአዴኑ ደመቀ መኮንን እና የደኢህዴዱ ሽፈራው ሽጉጤ የዲዮዶራንት ማስታወቂያ የሚሠሩ እስኪመስሉ ድረስ እጃቸውን ሽቅብ አውጥተው ብብታቸውን ሲያሸቱ ተመልክተናል።

ዶክተር አብይ በስብሰባው ያልተገኘበትን ምክንያት በእርግጠኝነት አናውቀውም። ይሁንና ድርጅቱ ኦህዴድ ሳይቀር የኢህአዴግን ውሳኔ ያለማንገራገር ለማስፈጸም በመግለጫው ማሳወቁን ስናስታውስ ፣ ከሌሎቹ ሊቃነ መናብርት ተለይቶ ከስብሰባው በመቅረት የውሳኔው አካል ላለመሆን የወሰደው እርምጃ ተገቢና ትክክለኛ የፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን እንገነዘባለን።

እንደገና ለማስታወስ ያህል ፣እያወራን ያለነው ጫፍ ላይ ስላሉ የድርጅት ሊቃነ መናብርት ነው።

በእርግጥ ዶክተር አብይ በፓርላማው ተገኝቶ አዋጁን በግልጽ በመቃወም አሁን ካደረገውም በላይ ማድረግ ይችል ነበር። ሆኖም ያን እንዲያደርግ ሌላው ቀርቶ በሊቀ-መንበርነት እንዲመራው በቅርቡ የሾመውና የኢህአዴግን ውሳኔ ለማስፈጸም የተስማማው የራሱ ድርጅትስ ይፈቅድለታል ወይ? ይህን በማወቁ “የመጣው ይምጣ ሕዝቤ ላይ ሞት የሚያውጅ ውሳኔ አካል አልሆንም!” ብሎ በሊቀመንበር ደረጃ ከሌሎቹ ሊቃነ መናብርት ተለይቶ ስብሰባውን መቅጣቱ ያስከብረዋል እንጂ እንዴት ያስነቅፈዋል?

ወይ መሬት ያለ ሰው!!!

ሰውዬው ሌላ ያላወቅነው ችግር ካለበት አሳውቁንና አብረን እናውግዘው። አለበለዚያ ምክንያቱ ብስለትም ይሁን ድፍረት፣ ሥልጣንም ይሁን ሌላ፣ ሊያስከብረው በሚችለው በዚህ በሳል ፖለቲካዊ ውሳኔ እናውግዘው ማለት አይዋጥም። እደግመዋለሁ ከአራቱ ድርጅት መሪዎች ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ ላወጀው የሞት አዋጅ ድምጹን በማሳረፍ የወንጀል ተባባሪ አለመሆኑን ያስመሰከረ እሱ ብቻ ነው።

(የተሰማኝን እውነት ለመመስከር ያህል ነው።)
Amsale Getahun

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *