የዩናይትድ ስቴስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሪክስ ቲለርሰን የኢትዮጵያ ጉብኝት በዋናነት ትኩረት የሚይደርገው አገሪቱ አሁን ከለችችበት ቀውስ እንዴት ልትወጣ እንደምትችል ለመነጋገር መሆኑን ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶናልድ ያማማቶ አስታወቁ። እሳቸውን ጠቅሰው የተሰራጩ ዜናዎች እንደሚያስረዱት ሚኒስትሩ በተፈናቀሉት በሚሊዮን ጉዳዮች ዙሪያም ማብራሪያ ይጠይቃሉ።

የአስቸኳይ አዋጁን አጥብቃ የተቃመመችው አሜሪካ ስለሁሉም ጉዳይ ከበቂ በላይ መረጃ እንዳላት፣ ያማምቶ እና ሌሎች ክፍተኛ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ አዲስ አበባ በተደጋጋሚ መመላለሳቸውንና የአሜሪካን ኤምባሲ እለት ከእለት ከሚያሰባስበው መረጃ አንጻር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ጉዳዩን አጥብቆታል።

ከሩሲያ ጋር ተፍ ተፍ ማለት የጀመረው ኢህአዴግ አሁን ከገባበት ቀውስ ሊወጣ የሚችልበትን አቅጣጫ አሚሪካ በተለያዩ ሃላፊዎቿ መንገሯን አስተያት ሰጪዎች ያመለክታሉ። በባራክ ኦባማ አስተዳደር የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር የነበሩት ቶም ማሊኖውስኪ ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ የአገሪቱን ሁኔታ የገለጹበትን አስመልክቶ ጎልጉል ይህንን መዘገቡ ይታወሳል። ለለውጥ የተገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥትብቸኛ ሃላፊነት ነው፤ … በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚፈለገው ለውጥ ሥርዓቱን ለዝነተ ዓለም ለማፅናት በሚደረግ ትግል ወይንም ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በሚወሰድ እርምጃም ሊሆን አይገባም፤ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ሥልጣን ማስረከብ ደረጃ ሊደረስ ይችላል” ሲሉ እንደ አንድ ወዳጅ አገር መምከራቸውን ለአሜሪካ ሬዲዮ ተናግረው ነበር።

ከሳቸውን ቀጥሎ የድህነት ከፈተኛ ሃላፊዎችና ዶንለድ ያማማቶ በዚሁ ጉዳይ ከኢህአዴግ ሰዎች ጋር መክረዋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አሜሪካ የሽግግር ሂደት እንዲካሄድ ሁሉ እምነት እንዳላት ማሳሰቧን በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጦ ነበር። በስተመቸረሻ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ በዋናነት አገሪቱ የገባቸበት ቀውስ ላይ ትኩርተ እንደሚደረገ መገለጹ ሲባል የቆየውን ጉዳይ አጠናክሮታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ጉብኝቱ በድህንነት ጉዳይና በአካባቢያዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑንን ለመንግስት መገናኛዎች ካሰራጨው መረጃ ለምረዳት ተችሏል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *