ዶክተር መረራ የሚመሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ፓርቲ መንግስትን እከሳለሁ ማለቱን ተከትሎ የትኛው ፍርድ ቤት? የሚል ጥያቄ እየተደመጠ ነው። እንኳን በህልውና ጉዳይ በተራ የፓርቲዎች አቤቱና ክስ ነጻ ሂነው የሚበይኑ ዳኞች በሌሉበት አገር እንዲህ ያለውን ጉዳይ ለህግ መውሰድ ከጅምሩ አድካሚ መሆኑ ተጠቁሟል። ይሁን እንጂ የሚበረታታና ለታሪክ የሚመዘገብ ይሆናል ተብሏል። ነጻ ፍርድ ቤት ካለ መረጃ መኖሩንና የእለቱን ስብሰባ ሙሉ የቪዲዮ ቅጂ ለአብነት ለማቅረብ የሚፈልጉ ዜጎች ፊልሙን በጃቸው ማስገባታቸው ታውቋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ፓርቲው ወደ ፍርድ ቤት ሲያመራ በምን መከራከሪያ እንደሚያቀርብ ያላብራራ ሲሆን አንዳንድ ምንጮች እንዳሉት በእለቱ በስብሰባው የተገኙት አባላት አቴንዳንስ/ የምዘግባ ሰነድ አለ። ምርጫው ሲካሄድ ድምጽ የነፈጉትም ተለይተው ይታወቃሉ። ማስረጃ ተደርገው ቢቀርቡ ፊርማቸውን አሰባስበው ሊሰጡ እንደሚችሉ ነው

ቢቢሲ ይህንን ዘግቧል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) በቅርቡ የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀበት መንገድ ህጋዊነት የጎደለው በመሆኑ መንግስትን ሊከስ እየተዘጋጀ እንደሆነ አስታወቀ።

የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት የቆየ ስብሰባ ካደረገ በኋላ ባወጣው የአቋም መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንደሚቃወም ገልጿል።

የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ በቀለ ገርባ ለቢቢሲ እንደገለፁት ፓርቲያቸው አዋጁን አስፈላጊ የሚያደርግ ነባራዊ ሁኔታ አለ ብሎ አያምንም።

ከዚህም ባለፈ አዋጁ በሕዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የፀደቀበት አግባብ ህጋዊነት እንደሚጎድለው ፓርቲያቸው ስለሚያምን ጠበቃ አቁሞ መንግስት ወደችሎት ሊወስድ ተሰናድቷል።

አዋጁ የፀደቀበት ሒደት የቁጥር ስህተት ያለበት፥ ይህንንም በመገንዘብ አባላቱ ከወጡ በኋላ የተሰጠው ድምፅ ሁለት ሶስተኛ እንደማይሞላ በመረዳት ማስተካከያ የተደረገበት፥ ሁለት እጃቸውን ያወጡ አባላት የተስተዋሉበትም ጭምር ነው ሲል ኦፌኮ በመግለጫው ነቀፌታውን አቅርቧል።

“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታወጀበትም የፀደቀበትም አካሄድ ህገ መንግስቱን የሚጥስ እና በህግም የሚያስጠይቅ ነው። እኛ አሁንም አገሪቷ በህግ ነው የምትመራው ብለን ስለምናምን ጠበቃ ቀጥረን ጉዳዩን ወደፍርድ ቤት እንወስዳለን” ሲሉ አቶ በቀለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *