ከየአቅጣጫው የሚወጣው የዜጎች ድምጽ ያማል። ለመስማትም ሆነ አድምጦ እውነት ነው ቦ ለመቀበል ይከብዳል። ግን እውነት ነው። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን በአንድ ምክንያት ነው የስልጣን ጥማት፣ እኔ ካልገዛሁ ከሚል እብሪት፣ ነብሰ በላ ከመሆን ተፈጥሮ የሚመነጭ ነው። ከዚህ ውጪ አንዳችም ምክንያት ሊቀርብ አይችልም። ቢቀርብም ከተራ ውሸትና ድንፋታ የዘለለ አይሆንም።

እስኪ ጉደር አቅራቢያ የሆነውን አስቡት፣ ይህቺ ገና ሳይነጋ በ70 ዓመት የሚገመቱ አዛውንት ባለቤቷን ቤቷ ድረስ ዘልቀው በጥይት አናታቸውን ማፍረስ ምን ማለት ነው? አልበቃ ብሎ ልጃቸውን በጥይት መደብደብ ምን ይባላል? ወንድም ” ግና ቀበቶ እንኳን አልታጠቅንም” ሲል ከእንቅልፍ አለመነሳታቸውን ነው የገለጸው። የተኛ ሰው ገብቶ በጥይት መደብደብ የደም አባዜ እንጂ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም። እብሪት እንጂ ምንም ስያሜና ምክንያት የለውም። ጥጋብ እንጂ ምንም ሊባል አይችልም።

እናት “ምን እናድርግ እግዚአብሄር ካለ አንኖራላን ወይም እናልቃለን። ለመላው ኢትዮጵያ እጮሃለሁ። የቤተሰቤን ደም እንዲከፍለኝ እጸልያሁ። ይህ ኑሮ አይደለም። አገሪቱ በሙሉ እሳት ውስጥ ነች…” ስትል እንዴት የሰው ልጅ አይራራም። ፖለቲከኞቹስ ቢሆኑ ከእናት አልተፈጠሩም? የሰውን ልጅ ማስጨፍጨፍ ምን እርካታ አለው። እኔ ካልገዛሁ በሚል አገሪቱን በደም ማበስብስ አድሮ ዋጋ አያስከፍልም? ስለምን ይህንን ድርጊት የተወሰኑ የህበረተሰብ ክፍሎች ብቻ ያወግዙታል?

Related stories   US: Aid Pause to Ethiopia No Longer Linked to Dam Dispute

የዛሬ ዓመት ወለጋ እናትን በልጇ አስከሬን ላይ አስቀምጠው ደበደቡ። እናት ልጇ አስከሬን ላይ ሆና የተፈጸመባትን ተናዘዘች። ሳግ አንቋት ጉዷን …. እናትን አስከሬን ላይ አስቀምጠው ግፍ መፈጸማቸው እንዴት ሌላውን አያሳዝነውም? ምን እየሆነ ነው ያለው? በጎንደር ሰው ተጨፈጨፈ። ባህር ዳር፣ ወልደያ፣ መርሳ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ሻሸመኔ፣ ሀረር፣ ጅግጅጋ፣ ሃማሬሳ…. ደም ጎረፈ። ምን እስኪሆን ነው የሚጠበቀው? ስንት ሚሊዮን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ነው የታሰበው? ከዛስ ስንት ዓመት ለመግዛትና ለመኖር ነው እቅድ የተያዘው?

ሰው አልፈልግም ካላ አለ ነው። ህወሃት ” ከፋኝ” ብሎ ትግራይን “ነጻ” አወጣ። በቃ ለምን ሌሎች ላይ ግፍ ይሰራል? አማራው፣ ኦሮሞው፣ ጉራጌው ተለጣፊ ሰለቸን አሉ። በምንፈለገው እንተዳደር የሚል ጥያቄ አነሱ። ለምን አይፈቀድላቸውም? ” ተሃድሶ” ቅብጥርሴ እየተባለ ስንት ዓመት ሰው ይጭበረበራል? ጥያቄው አንድ ነው። ” በቃችሁ” ነው። በምንፈልገው እንተዳደር ነው!! አለቀ!!

እንደዚህ ደም ፈሶ ካሁን በሁዋላ ምን ዓይነት እርቅ ሊፈጠርስ ይችላል? ማን ይቅር ይላል? ሕዝብ “በቃኝ” ካለ በቃኝ ነው። እንደ ቀድሞው ጥቂቶች እየተባለ የሚዘፈነው ዘፈን ጊዜው አልፎበታል። በሃሰት ዜናና ፕሮፓጋንዳ በዚህ ዘመን መኖርም አይሆንም። በተራ ድጋፍና ጥላቻ የሚሰራጩ ደምና ስጋ አዘል ሪፖርቶች ዋጋ የላቸውም። ዛሬ ሁሉም ሚዲያ አለው። ስውር ነገር የለም። የነቃ ትውልድ ነው። ይህንን ትውልድ መግደል፣ እናቶቻቸውን በሃዘን ማቆራመድ … እንደው ለመሆኑ የፈጣሪስ ፍርሃት የት ገባ?

Related stories   ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት - ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለም

በዩቲብና በየማህበራዊ ገጹ አጉል ተላላኪ መሆን ማንንም አይጠቅምም። አሁን ወደ ቀልብ መመለስና ህዝብን አክብሮ መፍትሄው ላይ መስራት እንጂ መልከስከስ ዋጋ የለውም። እንዲያውም የሚፈሰውን ደም የመጎንጨት ያህል ነው። ዛሬ ሁሉም ራሱን ችግር በሚጠብሳቸውና ጥይት በሚዘንብባቸው ወገኖች ጫማ ውስጥ በማስገባት ወደ ሃቅ ሊመጣ ይገባል። በቀናት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ህዝብ የተፈናቀለበትን ሲስተም ደግፎ መሟዘዝ ያሳፍራል። ከውጪ ለሳንቲም ለቀማ ሲባል እንደ ህንድ ፊልም ፖስተር የሰለባዎችን ምስል በመለጣጠፍ የወሬ ማስጮህ ተግባርም ሊገታ ይገባል።

ዜና በማጯጯህና በደም የተነከረ ምስል በማስደገፍ የዩቲብ ለብ አድክም ሪፖርቶች ማሟሟቂያ ማድረግ ፍጹም ኢሰብአዊነት ነው። የህጻናትን ምስል መለጠፍና መነገድ አግባብ አይሆንም። ከተለያዩ ሚዲያዎች የሚወሰዱ የድምጽ ሪፖርቶች ተፈጥሯቸውን እየቀየሩ ማቅረብም ተራ ቁማር እንጂ ሌላ ስም የለውም። ዜናውን ማሰራጨትና ላልሰማው ማዳረስ ከተፈለገ አግባብና ህጋዊ አካሄድ መከተል ግድ ነው። አንድ ሰው በሰራው ስራ ላይ እንደ ጉንዳን በመረባረብ ሳንቲም ለማግኘት መሮጥ ነውር ነው።

ዛሬ በሁሉም መስክ መልስ የሚሰጥ የለ፣ የሚጠየቅ የለ፣ በር ቀርቅሮ ህዝብ መጨረስ እንዴት አይነት የከፋ ወንጀል እንደሆነ አለመረዳት አስገራሚ ነው። ይህ ሁሉ ወንጀል ሪኮርድ ተደርጎ የተያዘ ነው። ያስጠይቃል። ነጹሃንን እየጨፈጨፉ እድሜያቸውን ያረዘሙ የሉም። የፍርድ አምላክ በበቀል ይነሳባቸዋል። ሳያስቡት ያስፈነጥራቸዋል። ጡንቻና መሳሪያ ተማንኖ እድሜ ሳይመርጡ ደም መጋት …. አሁንም ተነጋገሮ መፍትሄ መፈለግና ህዝብ የሚለውን መስማት ግድ ነው። ያለው አማራጭ እሱ ባቻ ነው!! ሕዝብ ን መስማት!!

Related stories   አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያን የተራዘመ ብድርና ገንዘውብ ድጋፍ ስምምነት ገመገመ

የክልሉ መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋም ሆነ የፌደራል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የእጅ ስልክ ላይ ለተከታታይ ቀናት ባደረግነው የስልክ ሙከራ ስልካቸውን ስለማያነሱ ልናገኛቸው አልቻልንም። የወረዳና የዞን አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው ጉዳዩ ከእነርሱ ቁጥጥር ስር እንዳይደለ ገልፀው ኮማንድ ፖስቱን እንድናነጋግር ገልፀውልናል። የመከላከያ ሚኒስትር እና የኮማንድ ፖስቱ ዋና ጸሐፊ አቶ ሲራጅ ፈጌሳና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌታቸው አምባዬና የእጅ ስልክ ላይ ደውለን ነበር እነርሱም አይመልሱም።በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በክልሉ እየተፈፀመ ነው ስለተባለው የመብት ጥሰት በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በንቲን ለማነጋገር ሞከረን ስልካቸው አይነሳም። ቪኦኤ እንዳለው የሚጠየቅ የለም። ሚዲያ መጮህ ያለበት እዚህ ላይ ነው!!  ይህንን አሳዛኝ ሪፖርት ከቪኦኤ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *