“Our true nationality is mankind.”H.G.

ውጤት አልባ የኢህአደግ አስመሳይ ግምገማ ስመለከተው? -አስደገ ብረስላሴ

የአሁኑ በህወሓት የጀመረው የኢህአደግ አባል ፓርቲዎች እና አጋራቻቸው አስመሳይ የለውጥ (መታደስ ) ግምገማ ገና ከጅምሩ የህወሓት ኢህአደግ ግምገማ ውጤቱ ውሀ ቢወገጥ አምቡጭ ብዬው ነበር ። አሁን ስመለከተውም ትክክል ነበር ። መቸ እኔ ብቻ የተናገሩት እጅግ ቡዙ ኢትዮጱያውያን የአሁኑ የተሀድሶ ግምገማቸው ካለፉት የተሀድሶ ግምገማቸው የተለዬ ውጤት አያመጡም ብለው የተነበዩ እጅግ ቡዙ ወገኖች ናቸው ።

ኣስገደ ገብረስላሴ

ይህን  አረዳድ ልንይዝ  የቻልንበት  ምክንያት  የኢህአደግ  ቡዱን  ስርአቱ  የሆው 27 አመቱ ሊያስቆጥር ነው ። ይህ ቡዱን በተጠቀሱት አመታት  እጅግ ብዙ የውሼት ለውጥ አመጣለሁ እያለ ከመምጣቱ በላይ ያልሰራው ሰራሁ ፣በመሬት በውሼት ክምር እና ዳታ  ለሀዝብ እያደነዘዘው አመምጣቱ በላይ  ራሱ የፈጠራቸው የመድረክ ምርጥ ስያሜዎችና ሞፎኮሮች  ለመላው ህዝባችን በተለይ ለወጣት አርሶ አደሮች ሙሁራኖች  ማታለል ፣ የውሼት ናዳ  በመሬት የማይታይ የህልም እንጀራ  ለማጉረስ ቢሞክርም  ፣ በአንጻሩ ወደ ውድቀት እያሽቆለቆለ ከምምራቱም አልፎ ፣ ለማሽቆልቆሉ  ከነመዋቅሩ የህዝብ   አንጡራ ሀብት የመዘበረውና ያካበተው  ሀብት ለመጠበቅ    የስልጣኑ እድሜ  ለማራዘም ፣በቡዙ  የተወሳሰበ  ሴራ በመደራጀት ወይ በመቃናጀት የዘር የሀይማኖት  ከዚህም አልፎ ቢሄር ተኮርና የድንበር ( ወሰን) ግጭት ሆን  ብለው  በመቀጣጠል ፣ ህዝባችን ወዳጅና  ጠላቶቹ አውቆ ለመሰረታዊ የስርአት ለውጥ  እና  ለጨቋኞቹ  በአንድነት ተጠናክሮ እንዳይቋወማቸው  ታሳቢ በማድረግ   ያደኸዩት ህዝባችን በመከፋፈል እርሱ በእርሱ እንዲተላለቅ  በማድረግ  እኖሆ  በህዝባችን መተላለቅ  ተጠልለው  የአፋኝ ስርአታቸው እድሜ እያራዘሙ ይገኛሉ ።

በሌላላ በኩል  ባገር ውስጥ ፣በውጭ  ሀገር  የሚገኙ  ፓለቲካ ፓርቲዎች ፣ስቢክ  ማህበራት ፣ ሙሁራን  ግለሰዎች  የኢህአደግ  በቢሄር ተኮር ግጭት ፣ከፋፍለህ ግዛ  የስልጣን እድሜ ማራዘሙ መቋጫ  እንዱያገኝ  በአንድነት አንድ ወጥ ሆነው  ወደ   ህዝብ እምብርቲ ገብተው  ህዝባችን በኢህአደግ  ሴራ ምክንያት እርሱ በእርሱ  መተላለቁ  አቁሞ ተፋቅሮ እንደ ድሮው አብሮ  በመኖር  የመደብ ጠላቶቻቸው  አውቆው  እንደ አንድ ሰው ቆሞው  እንቢ ለከፋፍለህ ግዛና  ዘረኛ ስርአት ብሎው  ለመብታቸው  እንዲጣበቁና  እንዲታገሉ  ከመምራት ይልቅ   አብዛኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተባብረው በአንደነት አለመታገላቸው በአንድ ማእቀፍ  ሲመደቡ   ።  በሌላ በኩል ጥቂት ፓርቲዎችና ግለሰዎች   በኢህአደግ  የውሼት ፕሮፕጋንዳ  እየተነዲ በስሜት   ለኢህአደግ ሰረኛ ተግባር  የሚያጠናክሩ  ጥቂት ፓርቲዎች እና  የውጭ ሚዲያዎች  ፣እንዲሁም ጥቂት የማህበራዊ  ሚዲያ ጸሀፊዎች  በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብና  የህወሓት መሪዎች  ሳይለዩ  የትግራይ ህዝብና  ህወሓት  ልዩነት የአንድ ሳንቲም ሁለትገጽ ነው በማለት   በሁሉም ነገር   እጁ የሌለ እና ምንም  ተጠቃሚነት የሌላቸው  የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ በጅምላ በጠላትነት የሌላው ቢሄር  ህዝብ  በሙሉ ወደ ትግራይ ህዝብ ና የግል ሀብቱ ጧቱን በመቀሰር  የዘር  ግድያ ፣እልቂት  ፣ የሀብት ወረራ እንዲያካይድ አድርገዋል እያደረጉም ይገኛሉ ።

አጅጉን የመገርመው ግን የትግራይ ህዝብ ወናው ኢትዮጱያ የምትባል ሀገር መሰረት ከመሆኑም በላይ ለኢትዮጱያ አንድነት የቆመ  ከህወሓት በጸረ ደርግ ትግል እስከ መጨረሻ ተፋልሞ ወደ ስልጣን ከያዙ በኃላ ኢህአደግ ስለከዳው የትግራይ ህዝብ ለህወሓት ኢህአደግ መሪዎች ከ1984 ዓ /ም ወዲህ  ግንኝነት አለነበራቸውንም ። ሆድና ጀርባ እያለ ግን ተዳክሞ ስለቆዬ ዝምታ መርጦ ነረዋል ። የትግራይ ህዝብ የህወሓት መሪዎች በደለንሀል ከደተንሀል ቢሉዋቸውም አልረኩም ። ታድያ አሁን ለትግራይ ህዝብ በጠላትነት የሚፈሩጁ ከዬት የመጡ ናቸው ?
ይህ ሀላፍነት የጎደለው ወንጀል የኢህአደግ ባለስልጣናት የስልጣን እድሜያቸው ለመራዘም ታሳቢ በማድረግ  በህዝቦች መካከል  ለፈጠሩት  ግጭት  የማይተናነስ ወንጀል እየፈጸሙ ይገኛሉ ።
እጅጉን የሚገርመው  ደግሞ  እኒህ ወገኖች ተቃዋሚ ሆነን ኢህአደግ አስወግደን ዲምክራሲያዊት  ኢትየጱያ  ንመሰርታለን  የሚሉ ሰዎች ናቸው ። ግን የትግል  የኢትየጱያ መሰረት የሆነው  የትግራይ ህዝብ   ካጠፉ ለመሆኑ ከዚያ በኃላ ኢትዮጱያ የምትባል አገር  ትኖራለችን  ?  በበኩሌ  ግን ህዝብ አስተባብረውና አዳራጅተው ቢቃወሙና ቢታገሉ  ልደግፋቸው ካልሆነ  በስተቀር  ፍጹም  ተቃውሞ የለኝም ። ነገር ግን ቢሄር ከቢሄር ዘር ከዘር ፣ሀይማኖት  ከሀይማኖት  እያጋጩ  ካስተላለቁ   እና አገር ከተከፋፈለች፣  የስርአት  ለውጡ በየተኛው ህዝብና አገር ነው ስርአቱ  የሚመሰርቱት ?
በጎንደርና  በጎጃም  በወልድያ በሌሎች አካባቢዎች በትገራይ ህዘብ ያነጣጠረ ቢሄር ተኮር እልቂት የህወሓትና  የባአዴን መሪዎች በራሳቸው ባአመኑበት  ለስልጣናችን እድሜ ለመራዘም ስንል ራሳችን ነው የፈጠርነው ብለው ተገደው የተናገሩት ተጠያቂ ራሳቸው ፈራጆች ራሳቸው ስለሆኑ ነው እንጅ ለፍርድ መቅረብ ነበረባቸው ። ይህ ወንጀል ግን  ለወደፊቱ ይህ ትውልድ ታሪኩ መቆፈሩ አይቀሬ ነው ።
ሌላ ግን ጥግ ጥግ ሆነው በውጭ ተጠግተው ወደ ህዝቡ በኦሮሞና በሱማል ፣በጎንደር ፣በጎጃም ፣በወሎ አማራ እና ትግሬ እያሉ የዘረኝነትና የቢሄር  ግጭት  የእሳት ሰደድ እያቃጣጠሉ በህዝቦች መካከል ትርምስ የሚፈጥሩ   ወንጀልም  ይህ ተውልድ መጠዬቁ አይቀሬ ነው ።

ከዚህ ተንደርድረን ከኢህአደግ  ተሀድሶ ምን ለውጥ  አገኜን
————————————————————
1   ከዚህ ተሀድሶ በሀገራችን  የተራቀቀ ወታደራዊ አገዛዝ ሲደግም እየተመለከትን ነው ፣
2  ከቆየው ጉዛችን የተጠናከረ ሁሉም አይነት መብቶች በመነጠቃችን የአፈና አገዛዝ   የኢትዮጱያ ህዝቦች ዳግም ዲክታቶሪያል ወታደራዊ መንግስት ተረክበዋል ።
2 ሰላማዊ ትግል መክሰሙ  አራጋግጠውልናል
4 በሙሱ  በሽርክናና በቡዱን የሀገር ሀብት የመዘበሩ  ፣ በውሼት ልማት ለ100 ሚሊዮን ህዝብ ያታለሉ ፣ በቂም በቀል ዜጎች የጎዱ ፣ በዘመድ አዝማድ በኔት ወርክ  ተዘርግተው ሰልጣን በሞኖፓል ተቆጣጥረው አገርማጥፋታቸው ተመልክተናል ።
5  የህወሐት ግምገማ ብዙ  ከፍተኛ አመራር በህዝብ ሀብት ስርቅ ፣በመልካም ኣስተዳደር  እጦት ህዝባችንእንደጎዱ ፣ ወሸታሞች  በመሆናቸው  ፣ ሌላሌላም ስህተቶች እንደፈጸሙ ተናዝዘዋ ።  ያሁሉ ወንጀል የፈጸሙ ግን  ከስልጣን አወረድናቸው ፣አሻጋሽገናል ብለው  ተናግረው   ነበር። በአንጻሩ ግን  ሀገር በመጉዳታቸው   ከስልጣን ወረዱ  ፣ተቀጡ ያሉዋቸው በሙሉ ከነበሩበት የበለጠ የሚመነዘሩበት እና ለስርቅ ሙቹ በሆነ ቦታ ተመድበዋ የህወሓት መሪዎች ግምገማ ወጤት ባዶና አስመሳይ ተሀድሶ ነው ።  ያልኩበትም ከገለስኩት ሀሳብ በመንደርደር ነው።

በሌላ በኩል የበአዴን ፓርት ግምገማም  የባሰውን ያሁሉ የዘረኝነትን በመቀስቀስ  ህዝብ  እርስ በእርሱ ሆን ብሎ  ያስጨረሰ የድሀ የትግራ ወገኖቹ   (ዜጎቹ ) ሀብት  ያወደሙና እንዲወድም አድርገው ።  ወንጀል የፈጸሙ መሪዎች  በተጨመሪም  የህዝብ ሀብት የወረረ ያስወረረ ፣ በሀገራችን  አማራ ቅማንት ፣ትግራይ አማራ ፣ ጉሙዝ  እያለ  በመከፋፈል  የዘረኝነት  ግጭት እንዲፈጠር ያደረገ  ራሱም ያመነበት  እያለ በመሸፋፈን ተሸላልመው ወጡ ።
በኦሆዴድና በዴሄደን  ገምገማም  ከጠቅላይ ምኒስቴር ሀይለማርያም ጀምረው የደቡብ ህዝቦች ልክ እንደ ህወሓት መሪዎች  የሞት የቃል ኑዛዜ ቢያደርጉም  ፣ የኦሮሞው ኦዴድ በነለማ መገርሳ አፈቀላጤነት ቢናዘዙ ውጤታቸው ልክ እንደ ህወሓት እና በአዴን  አስመሳይ ግምገማቸው  ነው ያሰሙን ። በአጠቃለይ የኢህአደግ አባል ፓርቲዎች አስመሳይ የተሀድሶ ለውጥ እንደ ሱናሚ የንፋስ  መእበል በኖ የጠፋና በ100 ሚሊዬን ህዝባችን ቀልዶና አጭበርብሮ ያለፈ ነው ።

ዋናው የኢህአደግ  የውሼት ተሀድሶና ግለሂስ ያመጣልን ትልቁ ለወጥ በመጀመሪያ የዚህ ጽሁፍ እንደመንደርደሪያ  ጠቅሼው ያለፍኩ ነጥብ ቢኖር ፣ ይህ  ተሀድሶ ኢህኣደግ 27 አመት ሙሉ በበረሀ ወታደር እየመራን እንደቆዬ እዳለ ሆኖ ።አሁን ግን አይኑ ያፈጠጠ ወታደራዊ ደርግ የተካ ስርአት  ሆኖ ነው የተገኜው  ። የሚያመሳስላቸው ደግሞ ሁለቱም  ዜጎች ሰላማዊ ሰልፊ የማድረግ   የመሰብሰብ  ፣  በፖለቲካ ፓርት በማህበራት የመደራጀት  መብት ከልክለዋል  ።  ባገርውስጥና በውጭ ሀገር  የሚገኙ ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲውች ፣ ስቢክ ማህበራት  ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ አጨልመውታል ።ሁሉም አይነት ሚዲያዎች የህትመት ወጤቶች ዘግተዋል ።ያለፍርድቤት ትእዛዝ  ዜጎች እንዲታሰሩ ፣ ቤታቸው እንዲቦረቦር አውጀዋል ፣በቡዱን ሆነህ  መሄድ  እንቅስቃሴ እንዳይኖር  አውጀዋል ።በመሆኑ ከደርግ ጋር አነድ ወጥ አቋም  ይዘው የወጡ  ወይ ያመጡልን ለውጥ መሆኑ ነው   ።
ትልቁ ለውጥ ያየነው ደግሞ 27 አመት ሙሉ በኢህአደግ አባል  ፓርቲዎች በፓርላማ ፣በጉባኤአቸው  የሚደረጉ  ወሳኔዎች ተቃውሞ ፣ድምጽ ተአቅቦ አይተን ሰምተን አናውቅም። ተቃውሞ ያሳዬ ከተገኜ ከሁለም ነገር ይገሉሉታል  በስራውና በኑሮው  አደጋ ያደርሱበታል ።
አሁን የተገኜው አዲሰ ግኝት ግን። ለሁሉ ነገር ለተባለቹ ቃል  የስ የሚል  የነበረ  ካድሬና  ፓርላማ  አባል ከኢህአደግ    አባል ፓርቲ   አመላካከት በማፈንገጥ  በአንድ  ወሳኝ ውሳኔ ላይ  88 ተቃውሞ  ፣7 ድምጽ ተአቅቦ  መታየቱ  እና የራሱ አቋም ይዞ መውጣቱ ኢህአደግ ምንኛ ወስጡ ተፍረክርኮ እዳለ የሚያሳይ ነው  ።በተጨማሪም  ለኢህአደግ  በስልጣኑ ላይ ቀይ  ካርድ እንዳዬ ያመለክተዋል ።ለህዝብም መልካም ተስፋ ይህ ሰልጣል ።  ከላይ የዘረዘርኩት ነጥብ ካልኩ ስመለከተው ግን ለአህአደግ እና አባል ፓርቲዎች እንዲሁ ለአጋር ፓርቲዎች እምጠይቃቸው አለና   ይመሉሱልኝ?

1   ህሓት ኢህአደግ  ደርግ ፋሽሽታዊ ስርአቱ ካወጀ በኃላ በአጭር  ጊዜ ተደራጅተው  በደርግ ስርአት ውስጥ  ሰላማዊ  ትግል ማካዬድ  አይቻልም ብለው  በመሏው ሀገራችን ደፈጣ ተዋጊ ግንባሮች እንደ ፋብሪካ ተፈብርከው በደርዘን የሚቆጠሩ  ተፈጥረው 17 አመት  ሙሉ ታግለው ደርግን  አንኮትኩተው  ጥለው መምጣታቸው  ራሳቸውም በነሱ ማእቀፍ ተጉዘው ለዚሁ ስርአታቸው እየመሩ  እንዳሉ መሆናቸው ይገባቸው ይሆን ?

2 ኢህአደግ ከራሱተምክሮ ተነስቶ በ1983 ዓ/ም
ደርግን  ከደፈጣ ውግያ  ተነስቶ አስወግዶ  ስልጣኑ ከተቆጣጠረ በኃላ  ለይምሰል ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሳተፉበት የሽግግር መንግስት እመሰርታለሁ ብሎ ሲያበቃ ፣ነገር ግን ለስልጣኑ ያሰጉኛል ያላቸው ከቂም በቀል  እና ከስጋት የመነጨ  በወቅቱ የነበሩ ትላልቅ ፓርቲዎች እንደጠላት በመቁጠር ጦርነት በመክፈቱ እጅግ ቡዙ ፓርቲዎች ወደ ደፈጣ ውግያ ተሰማሩ  ። ቆየት ብለውም እነ ደድሚሒት ከፋኝ ወጡ ፣ከ1997 በኃላም የኣርቦኞች ፣ጉንበት ሰባት የጋንቤላ የጉሙዝ እያሉ ወጡ ። በዝህች አገር ኢህአደግ ከተፈጠረ ጀምሮ  አስከ አሁን  27 አመት ሙሉ ጦርነት ሞት እስራት አመጽ፣ ስደት  አልተለያት  አደረጋት  ።
3     አሁን ደግሞ  ልክ እንደደርግ ሁሉም አይነት ዲሞክራሲያዊ መብቶችና  ጥያቄዎች ማንሳት መደረጀት በሰላም የመታገል  መብት ፍጹም ተዘግተዋል ።ኢህአደግ አሁንስ ከደርግና ከራሱ ተሞክሮ ቀስሞ   አይማርም ?
ታድያ 6 ወር ሙሉ  በሀገራችን የተፈጸሙ ወንጀሎች ከጠቅላይ ምኒስቴር እስከ ቀበሌ የተሰገሰው የኢህአደግ ባለስልጣናት እና ከነሱ በዘመድ በጥቅሚ ተሳስረን  የሀገር  ሀብት ወረናል   ብለውናል  ነገር ግን ባዶ ዲስኩር እንጅ ሌቦች ሲመቱ አላዬንም  ይልቁንስ ተጠናክረው ወጥተዋል
4 ስልጣን በሞኖፓል ይዘን ለአዲሱ ትውልድ  ልናስተላልፍ አልቻልንም ብለው ነበር ።  ይህም አልተገበሩትም  ።የነበረው  አማራር ነው ባለህበት ርገጥ  የሚለን  ያለው ።
በመጠቃለል የዘንድሮ የኢህአደግ ጥልቅ ተሀድሶ  የተባለው ምርጥ ቃላት የመምረጥ የተካኑ በመሆናቸው ነው እንጅ ተሀድሰው እስመሳይ  እንደሆነ   ነው የሚገባን ። a
አስደገ ብረስላሴ
መቀለ
26 /06 /2010

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሻለቃ ሰከን ይበሉ እንጂ! – ባይሳ ዋቅ-ወያ
0Shares
0