“Our true nationality is mankind.”H.G.

ጊዚያዊ የወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ቢከለክልም ኦሮሚያ “ነፍሰገዳዮቹና አዛዦቹ ተላልፈው ይሰጡኝ፤ በመደበኛ ፍርድ ቤት አየዋለሁ” እያለ ነው

በተመሳሳይ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ግድያ መፈጸሙን ተከትሎ ክልሉ በይፋ ” ገዳዮች ተላልፈው ይሰጡኝ” ሲል አልተሰማም። የኦሮሚያ ክልል ግን ከሶማሌ ክልል መፈናቀል በሁዋላ ቀደም ሲል በጨለንቆ፣ አሁን ደግሞ በሞያሌ የተካሄደውን ግድያ በግልጽ ቋንቋ አውግዟል። ግድያውን የፈጸሙና ያዘዙ አካላት የፈጸሙት የጦር ወንጀል መሆኑንን በመጠቆም በመደበኛ ፍርድ ቤት ለማየት ተላልፈው እንዲሰጡት ጠየቀ።

የክልሉ የፍትህ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ እንደሚሉት የታጠቀ ጠላትም ቢሆን እጁን እንዲሰጥ ሊጠየቅ ይገባል። ከንቲባው እንዳረጋገጡት ይህን የመሰለ አሰቃቂ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስገድድ አንድም ነገር በሌለበት ሁኔታ ሰላማዊ ወገኖችን መግደል በመንም መመዘኛ ስህተት ሊባል አይችልም ብለዋል።

“አንዳንዶቹ ተንበርከኩ ተብለዋል” ያሉት አቶ ታዬ ድርጊቱ ስህተት ሊባል እንደማይችል ያብራራሉ። የተንበረከኩትን ንጹህ ዜጎች በጥይት ተደብድበዋል። አንዳንዶቹም በጥይት ከተመቱ በሁዋላም በወደቁበት በጥይት ሶስት አራት ቦታ ተመተዋል። 

እንዲህ ያለውን ወንጀል ” በስህተት የተፈጸመ ነው ማለት አይቻልም” ሲሉ የከረረ ስሜት የታየበት ምላሽ የሰጡት አቶ ታዬ፣ በስህተት ነው ያለው ክፍል፣ ያዘዘው፣ ግድያውን የፈጸሙት ሁሉ ወንጀለኞቹ በክልሉ መደበኛ ፍርድ ቤት በግልጽ ችሎት ሊሆን እንደሚገባና ይህም እምነታቸው እንደሆነ በይፋ አስታውቀዋል።

moyale.jpg

” ወንጀሉ ግድያ ነው” በማለት ማብራሪያ የሰጡት ሃላፊው ” ወንጀሉ የተፈጸመው በጦርነት ውስጥ አይደለም” ሲሉ ክልላቸው ብይኑን በመደበኛ ፍርድ ቤት ሊመለክተው እንደሚገባ ተናግረዋል። የሞያሌ ከተማ ከንቲባ አቶ  አስቻለው ዮሃንስ በተመሳሳይ ለቪኦኤ እንዳሉት ብይኑ በክልሉ መደበኛ ፍርድ ቤት በግልጽ ችሎት ሊታይ እንደሚገባ አስቀድመው ተናግረው ነበር።

ይህ ወታደራዊ ኮማንድ ፖስቱ በይፋ ያመነውን ግድያ አስመልክቶ ግምገማ የተቀመጠው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ እስካሁን ያለው ነገር የለም። ይሁን እንጂ በአገሪቱ የመደበኛው ህግ አግባብ ማስተዳደር የሚችል የፌደራልና የክልል መንግስት ባለመኖሩ እንደተቋቋመ የተነገረለት ወታደራዊ ኮማንድ ፖስቱ አምስት ወታደሮችና የሻለቃ መሪውን ትጥቅ አስፈትቶ በቁጥትር ስር ማዋሉን ይፋ አድርጓል። አያይዞም ከፍተኛ የተባሉት የጦር አዛዦች ለቅሶ እንደሚደርሱ፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን እንደሚያጽናኑ ጠቁሟል።

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ተጎጂዎቹ ከተለያየ ክልልና ስፍራ የመጡ የተለያዩ ብሄረሰብ አባላት በመሆናቸው፣ ከፍተኛ የተባሉት የጦር አዛዦች ስራ ለማጽናናት ከቦታ ቦታ ሲዛወሩ በኮማንድ ፖስቱ ውስጥ የአሰራር ክፍተት እንዳይፈጠር የሰጉ በፌስ ቡክ ገጾቻቸው ላይ ጥንቃቄ እንደሚያሻቸው ገልጸዋል።

ለዚህ ይመስላል የኦሮሚያ የፈትህ ቢሮ ጉዳዩን ራሴ አጣርቼ ብይን እሰጣለሁ ሲል ጠይቋል። የሞያሌ ከተማና ሃዘኑ የጎዳቸው ሁሉ የፍርድ ሂደቱ በግልጽ ችሎት እንዲሆን ጠይቀዋል። ኮማንድ ፓኦስቱን የወከሉት ጀነራል ግን ” የጦር ፍርድ ቤት አለ” ብለዋል። ሙሉውን ዜና ከቪኦኤ ያድምጡ

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

 

ወታደራዊ ክማንድ ፖስቱ መግለጫ መስጠትን ቢከለክልም የኦሮሚያ ክልል ሃላፊዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ለተጠየቁት መልስ በመስጠት ይገምገሙ አይገምገሙ የታወቀ ነገር የለም። የሞያሌ እና አካባቢው ነዋሪዎች ፈልሰው ኬንያ መግባታቸውና ህጻናት በምግብ እጥረት፣ በመኝታ ችግር፣ እንዲሁም በተለያዩ አቅርቦት ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸው እየተገለጸ ነው። መቼ ወደ መኖሪአ ቀዬያቸው እንደሚመለሱም በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0