በኬንያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሞያሌ ስደተኞች ቁጥር የተጋነነ እና ለፖለቲካና ኢኮኖሚ ትርፍ እየዋለ ነው ሲል ለፋና ተናገሩ። አምባሳደሩ በስፍራው አልተገኙም፤ ቁጥሩ የተጋነነ ስለመሆኑ መከራከሪያ ዳታና መረጃ አላቀረቡም። አቶ ዲና የዓለም ሚዲያዎችን፣ የኬንያን መንግስት፣ የኬንያን የሰባዊ ድጋፍ ሰጢዎች፣ ቀይ መስቀልና ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸውን በሙሉ ነው ያወገዙት።


ሞያሌ.png

ከሞያሌ የተሰደዱትን ወገኖች ቁጥር በትክክል ለማወቅ መቸገራቸውን የኬንያ የቀይ መስቀል ሃላፊዎችና የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ሲናገሩ ነበር። አሁን ድረስ በየመንደሩ ነዋሪዎች ጋር ተጠግተው ያሉ እንዳሉ እየተዘገበ ባለበት፣ ስደተኞች አሁንም እየፈለሱ መሆን በሚገለጽበት፣ የኬንያ መንግስት ሰራዊት ለማሰማራት ባቀደበት በአሁን ሰዓት ናይሮቢ ተቀማጭ የሆኑት አቶ ዲና ለምን ይህን እንዳሉ ግልጽ አይደለም።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

ለሪኮርድ ይሆን ዘንድ ፋና እሳቸውን ጠቅሶ የዘገበው የሚከተለው ነው። 

የሞያሌ ተፈናቃዮችን ቁጥር በማጋነን የሚዲያ አካላትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትርፍ ለማግኘት እየጣሩ መሆኑን በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፁ።

አምባሳደር ዲና ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በሞያሌ ከተፈጠረው ክስተት በኋላ በርካታ ዜጎች ወደ ኬንያ ገብተው እንደነበር አስታውሰዋል።

ይህንን ዘገባ እንዴት ማስተባበል ይቻላል!!
https://www.bbc.co.uk/programmes/p061qnjg/player

ከሞያሌ ወደ ኬንያ የገቡትን ዜጎች ቁጥር በትክክል መግለፅ ለማንኛውም ወገን አስቸጋሪ ነው ያሉት አምባሳደሩ፥ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ዜጎችወደ ሀገር ቤት እተመለሱ መሆኑን አንስተዋል።

ዜጎች በየእለቱ ከሞያሌ ወደ ኬንያ እየጎረፉ ነው ተብሎ የሚወራውም በመሬት ላይ ያለውን እውነት የማያሳይ ነው ብለዋል።

ከቁጥሩ ጋር ተያይዞ ከአንድ በኩል ትክክለኛ እርዳታ ለማግኘት ትክክል የሆነ አሃዝ የሚገልጹትን ያክል እንዳሉ ሁሉ፥ ተገቢ ያልሆነ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጥቅም ለማግኘት የሚያጋንኑ መኖራቸውንም ጠቅሰዋል።

አምባሳደር ዲና አያይዘውም፥ የሞያሌ ተፈናቃዮች ወደ ኬንያ ከገቡ በኋላ አመቺ ባልሆነ ሁኔታ በአራት መጠለያዎች ውስጥ መቆየታቸውንም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም የአካባቢው እና እና የሀገር ሽማግሌዎች ተፈናቃዮችን አግኝተው ካነጋገሯቸው በኋላ ሁኔታዎች መረጋጋታቸውንም ነው የተናገሩት።

ተፈናቃዮቹ ሀገር ቤት መመለስ እንደሚችሉ ከተነገራቸው በኋላም በርካታ ህፃናት፣ አሮጊቶች እና ሽማግሌዎች እየተመለሱ ነው ብለዋል።

በርካታ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተፈናቃዮችን ለማስተናገድ የሚጥሩትን ያክልም፥ በተቃራኒው ሁኔታውን ለግል ጥቅም ለማዋል ያሰቡ አካላት ዜጎችን የመመለስ ሂደት ላይ እንቅፋት እየፈጠሩ መሆኑንም አስረድተዋል።

በእነዚህ አካላት ዘንድ ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱትን ሳይሆን ከሀገር የሚወጡትን ማበረታታት፣ የተመለሱትን እንዳልተመለሱ አድርጎ ቁጥሩን የማጋነን ሁኔታ እንዳለ ጠቅሰው ሁኔታው አሳዛኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ተፈናቃይ ዜጎች ወደቀያቸው የመመለስ ፍላጎት አላቸው ያሉት አምባሳደር ዲና፥ ስጋታቸው በተቀረፈ መጠን እና አንዳንድ አካላት የሚፈጥሩት ውዥንብር በቀነሰ መጠን ዜጎች በብዛት ወደቀያቸው እንደሚመለሱ ተስፋ አለን ብለዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *