ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ከአማራ ድርጅቶች እና ማህበራት ስብስብ(አድማስ) የተሰጠ መግለጫ

በትግሬ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር(ትሕነግ) የሚመራው ዘረኛና ከፋፋይ፣ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ የሆነው  ድርጅት የሚመራው ኢሕአዴግ ፣በ27 ዓመታት አረመኔአዊ አገዛዝ በአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም፣ ግዛታዊ አንድነት፣ በሕዝቡ አብሮነት ስሜት ላይ የፈጸማቸው አፍርሽ ተግባሮች ኢትዮጵያን እንደ አገር ልትቀጥል ወደ ማትችልበት አደገኛ አዘቅት ውስጥ እየከተታት እንዳለ ይታወቃል።

ከዚህ አስከፊ የመበታተን እና የእርስ በርስ እልቂት መውጣት እንዲቻል፣ ዜጎች በዜግነታቸው፣ የፖለቲካ፣ የሲቪክ፣ የሙያ ማኅበራትና የብዙኃን መገናኛዎች አገሪቱና ሕዝቡ ከአስከፊ ጥፋት ራሳቸውን መከላከል እንዲችሉ በየፊናቸው የተቻላቸውን ሲያስተምሩና ሲመክሩ የነበሩና ያሉ ግለሰቦችን ከመግደልና ከማሰደድ የተረፉትን በሀሰት ክስ ወንጅሎ ለበርካታ ዓመታት አስሮ ማሰቃየቱ ይታወቃል።

አፈና፣ ግድያ፣ እስራትና ሥቃይ የበዛበት ሕዝብ በአፋኙና በገዳዩ ላይ ማመጽ ተፈጥሮአዊ ግዴታ በመሆኑ፣ የትግሬ-ወያኔ(ትሕነግ) የጫነበትን የመከራ ቀንበር ሰባብሮ ለመጣል ሕዝቡ ፣ባገኘውና በመሰለው መንገድ በተናጠልና በቡድ ባቀጠጣለው ሕዝባዊ አመጽ: የአፋኙ አገዛዝ የአፈና እና የግድያ መዋቅሩ ከሥሩ በመናጋቱ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ አማራው ብሄርተኝነቱን አጠናክሮ ብሄሩን መሰረት አድርጎ በፖሊሲ ደረጃ ተቀርጾ ሊያጠፋው የመጣውን ጠላት ለመከላከል በየአለበት ከመደራጀት ጀምሮ እስከ ነፍጥ አንስቶ በመታገል ህልውናውን ለማስከበር ቆርጦ በመነሳቱ ፣ ወያኔ የቆመበትን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረት ከሥሩ አናጋው።

ይህን ከሥሩ የተናጋና የተናወጠ ፖለቲካዊ መሠረት ለመጠገን ሲል ወያኔ፣ ለዐሥር ወራት የዘለቀ አስቸክይ አዋጅ አውጆ አያሌ ዜጎችን በመግደል፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን በማሰር ጊዜ ሊገዛ መሞከሩ ይታወሳል። ይህ ድርጊት ምዕላተ ሕዝቡን ለመሠረታዊ ለውጥ እንዲነሳ ግፊት ከማሳደር አልፎ፣ የወያኔ አገዛዝ ድጋፍ ሰጭ ሆነው የቆሙትን ምዕራባዊ ለጋሽና አበዳሪ መንግሥታት፣ወያኔ በገዛ ሕዝቡ ላይ የሚፈጽመውን ዘግናኝ ግፍ ሊታገሱት ከሚችሉት በላይ ሆኖ ስላገኙት ያሠራቸውን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና አባሎች ፣ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን እንዲፈታ ቢገደድም ቅዳሜ መጋቢት 16/2010 ዓ.ም በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤት ከጠባቧ እስር ቤት መውጣታቸውን አስመልክቶ የምሳ ግብዣ በማድረግ ላይ እያሉ የአባቶቻችሁን ሰንደቅ ለምን ያዛችሁ በሚል የማሰሪያ ምክኒያት

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን፣ ታዋቂውን ፖለቲከኛ አቶ አንዷልም አራጌን፣ ጋዜጠኛ በፈቃዱ ሃይሉ፣ ጸሃፊ፣ዘላላም ወርቃገኘሁ፣ ይድነቃቸው አዲስ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አዲሱ ጌታነህ፣ ተፈራ ተስፋዬ፣ ማህሌት ፋንታሁንና ወይንሸት ሞላ ጨምሮ ሌሎችም ንጹሀን ዜጎችን ለስር ዳርጔል። በተጨማሪም በተመሳሳይ ቀን በባህር ዳር ከተማ እራሱ አፋኙ ቡድን እመራበታለሁ የሚለውን ህገመንግስት ተከትለው ህገመንግስታዊ መብታቸው የሆነውን የመደራጀት ተደራጅቶም በሰላማዊ መንገድ መታገል መብት ተጠቅመው የፖለቲካ ድርጅት ለማቋም በመንቀሳቀስ

ላይ የነበሩ የአማራው ስቃይ ገፈት ቀማሽ እና በአማራው ወገናቸው ላይ የተጋረጠውን የዘር ማጥፋት አደጋ ለመከላከል ያሰቡ ከአማራው አብራክ የወጡ ምሁራን በአፋኙ ቡድን ታፍነው ድብደባና እስራት ደርሶባቸዋል:: በግፍ ከታሠሩት መካከልም የሚከተሉት ይገኛሉ፦

1, ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ (ባ/ዳር ዩንቨርሲቲ መምህርና የጣና ደህንነትና የአካባቢ ጥበቃ ማህበር ፕሬዚደንት

2, አቶ ጋሻው መርሻ

3, የሱፍ ኢብራሂም (ወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበረና አሁን ጠበቃ)

4, ተመስገን ተሰማ (ወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር)

5, በለጠ ሞላ (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር)

6, ንጋቱ አስረስ (የአማራ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ)

7, በለጠ ካሴ (የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረ)

8, ኢንጂነር ሲሳይ አልታሰብ

9, አቶ ዳንኤል አበባው

10, አቶ መንግስቴ ተገኔ

11, አቶ ቦጋለ አራጌ

12, አቶ ካሱ ኃይሉ (የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መምህር)

13, አቶ ተሰማ ካሳሁን

14, አቶ ድርሳን ብርሃኔ

15, አቶ በሪሁን አሰፋ

16, አቶ ፍቅሩ ካሳው

17, አዲሱ መለሰ (ደ/ታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህር)

18, አቶ ተመስገን ብርሃኑ

19, የሱፍ አልታሰብ የሕግ ሙያተኛና ሌሎችንም በማሰር ላይ እንደሆነ ተረጋግጧል::

ይህን የወገናችን መታሰርና መሰቃየት የዐማራ ድርጅቶች ኅብረት በጽኑ ከማውገዝ ባሻገር፣ የታሰሩት እንዲፈቱ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኝነቱን በዐማራ ሕዝብ ስም እየገለጸ፣ የሕዝባችን አንድነት ፣ሰላምና መረጋጋት ዕውን የሚሆነው አፋኙንና ዘረኛውን የትግሬ ወያኔ አገዛዝ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ መንጭቆ መጣል ሲል ብቻ ስለሆነ፣ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ከድል መልስ የማይመለስ መሆኑን አውቆ ከተደራጁት ልጆቹ ጎን በመቆም የአገዛዙን ዕድሜ ለማሳጠር የሚደረገው ግብግብ አካል እንዲሆን ጥሪያችን ስናቀርብ በማክበር ነው።

ማስታዎሻ:

አድማስ የአማራ ድርጅቶች እና ማህበራት ስብስብ በሰሜን አሜሪካ ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 02 በተካሄደው

የመጀመሪያው የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊ ድርጅቶች የፈጠሩት የአማራ ድርጅቶች የትብብር ስብስብ ነው::

Related stories   የፌደራልና የክልል ፖሊስ አዲስ የአደረጃጀት ሰነድ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቀረበ