“Our true nationality is mankind.”H.G.

በታሪኩ – ኢህአዴግ የሚደመጥ "ሰው" አገኘ !!ዶክተር አብይ የሕዝብ ልጅ ሆነህ እለፍ፤

ያለማቋረጥ በተለያዩ መዋቅሮች ለአራት ወራት ያህል ስብሰባ ላይ የተቀመጠው ኢህአዴግ በመጨረሻ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደመጥ ሰው ማግኘቱን አስታወቀ። ዶክተር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነዋል። የመጀመሪያው ህዝብ ድጋፍ የሰጣጨው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነውም በይፋ ይሰየማሉ።

በሩን ዘገቶ ሲነታረክ የሰነበተው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ወደዚህ ውሳኔ እንደሚመጣ አስቀድሞ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ዶከተር አብይ ላይ ውሃ የማያነሳ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲካሄድ ነበር። በብአዴን ሰፊው አመራርና በአማራ ክልል፣ በድፍን “የኢትዮያ” ህዝብ ጥሩ ቀለም የሌላቸው አቶ በረከት ጻፉት በተባለ ጽሁፍ ዶክተር አብይ ተራና ዋጋ ቢስ ተደርገው ተስለው ነበር።

የዶክተር አብይ ነገር፣

abye4ከተቃዋሚዎች ጋር አብሮ ለመሥራት ጥሪ ማቅረብን እና በኢትዮጵያ የነበረውና ያለው የብሔር ሳይሆን የመደብ ጭቆና ነው የሚል አዲስ አቋም ማንጸባረቅን ጨምሮ ከአራቱ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች መካከል ጠንካራና ትርጉም ያለው መግለጫ ያወጣው ኦህ ዴድ እንደኾነ እናስታውሳለን። ኦህዴድ በዚያው መግለጫ ላይ፣ በኢህአዴግ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ያለምንም ማቅማማትና ማንገራገር ለማስፈጸም ውሳኔ ማሳለፉም አይዘነጋም። 
ይህን እውነታ እንዳለ አስቀምጠን ወደ ወቅታዊው ጉዳይ ስንመጣ ደግሞ ከአራቱ የኢህ አዴግ ድርጅት ሊቃነ መቃብርት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የይኹንታ ድምጽ ያልሰጠው የኦህዴዱ ዶክተር አብይ አሕመድ ብቻ ነው። የህወኃቱ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ የብአዴኑ ደመቀ መኮንን እና የደኢህዴዱ ሽፈራው ሽጉጤ የዲዮዶራንት ማስታወቂያ የሚሠሩ እስኪመስሉ ድረስ እጃቸውን ሽቅብ አውጥተው ብብታቸውን ሲያሸቱ ተመልክተናል። ዶክተር አብይ በስብሰባው ያልተገኘበትን ምክንያት በእርግጠኝነት አናውቀውም። ይሁንና ድርጅቱ ኦህዴድ ሳይቀር የኢህአዴግን ውሳኔ ያለማንገራገር ለማስፈጸም በመግለጫው ማሳወቁን ስናስታውስ ፣ ከሌሎቹ ሊቃነ መናብርት ተለይቶ ከስብሰባው በመቅረት የውሳኔው አካል ላለመሆን የወሰደው እርምጃ ተገቢና ትክክለኛ የፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን እንገነዘባለን።

እንደገና ለማስታወስ ያህል ፣እያወራን ያለነው ጫፍ ላይ ስላሉ የድርጅት ሊቃነ መናብርት ነው። በእርግጥ ዶክተር አብይ በፓርላማው ተገኝቶ አዋጁን በግልጽ በመቃወም አሁን ካደረገውም በላይ ማድረግ ይችል ነበር። ሆኖም ያን እንዲያደርግ ሌላው ቀርቶ በሊቀ-መንበርነት እንዲመራው በቅርቡ የሾመውና የኢህአዴግን ውሳኔ ለማስፈጸም የተስማማው የራሱ ድርጅትስ ይፈቅድለታል ወይ? ይህን በማወቁ “የመጣው ይምጣ ሕዝቤ ላይ ሞት የሚያውጅ ውሳኔ አካል አልሆንም!” ብሎ በሊቀመንበር ደረጃ ከሌሎቹ ሊቃነ መናብርት ተለይቶ ስብሰባውን መቅጣቱ ያስከብረዋል እንጂ እንዴት ያስነቅፈዋል? ወይ መሬት ያለ ሰው!!!

ሰውዬው ሌላ ያላወቅነው ችግር ካለበት አሳውቁንና አብረን እናውግዘው። አለበለዚያ ምክንያቱ ብስለትም ይሁን ድፍረት፣ ሥልጣንም ይሁን ሌላ፣ ሊያስከብረው በሚችለው በዚህ በሳል ፖለቲካዊ ውሳኔ እናውግዘው ማለት አይዋጥም። እደግመዋለሁ ከአራቱ ድርጅት መሪዎች ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ ላወጀው የሞት አዋጅ ድምጹን በማሳረፍ የወንጀል ተባባሪ አለመሆኑን ያስመሰከረ እሱ ብቻ ነው። 

(የተሰማኝን እውነት ለመመስከር ያህል ነው።) Amsale Getahun

ከቅርብ ወራት ውዲህ፣ በኦሮሚያ እየጋመ፣ በአማራ ክልል እየነደደ፣ በሌሎች አካባቢዎችም ሞቅ በረድ የሚለውን ህዝባዊ ቁጣ ተከትለው መድረክ ላይ ብቅ ያሉት ዶክተር አብይ ባቀረቧቸው ንግግሮች፣ ስብከቶች፣ ዲስኩሮች፣ ትምህርትና ስልጠና መሰል ጉባኤ በቀላሉ ስማቸው ናኝቷል። አንዳንዶች ” መለስ ቢኖሩ አብይን አናያቸውን ነበር ” ሲሉም ብዙ የተዘጋባቸው ባለብሩህ አዕምሮዎች ስለመኖራቸው ፍንጭ ማየታቸውን ተንብየዋል።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ውትድርናን የቀለለ ሙያ በማድረግ አዲሱን መሪ ለማጠልሸት በተበተኑ ጽሁፎች ስሜት ያልሰጣቸው ወገኖች ምስክርነታቸውን ላኩ። ህወሃትን ከሚገባው በላይ ቦላሌ ያለበሱትና የበትረ መንግስት ቁልፍ የሰጡት ኽርማን ኮሆን ስም ጠርተው “አብይ መጡቅ ነው” ሲሉ አገሪቱን ሊመራ የሚችል እንደሆነ በግልጽ ሃሳባቸውን ወረወሩ።

እነ አቶ መለስ ሲያበሻቅጡት የነበረውን ኢትዮጵያዊነትን ” ሱስ” ነው በማለት፣ ” የእኛ ስልጣን ገድል ይግባ” በሚል አገር እንድትቀድም ከፍ ባለ ቃልና፣ ከልብ በሚፈስ ስሜት በመናገር አደባባይ የወጡት አቶ ለማ መገርሳ ዶክተር አብይን ለዚህ ሹመት ሲያመቻቹ የገባቸው ” የወየበችውን ኢትዮጵያ አብረቅራቂ ውበት የሚያላብሱ ልጆች ተነሱ” ብለዋቸው ነበር።

Related stories   ኢትዮጵያ የውጭ ጣልቃ ገብነትን " ወግድ አለች" መንግስት መግለጫ ሰጠ

በድንብ የተጋመዱት የኦህዴድ ሃላፊዎች ድርጅታዊ ጉባኤያቸውን ካካሄዱ በሁዋላ ባወጡት መግለጫ የሕዝብ ቀልብ ሲስቡ፣ ይህ መግለጫ ምን አለበት የኢህአዴግ በሆነ በሚል የተመኙ ትንሽ አልነበሩም። ” በኢትዮጵያ የመደብ ልዩነት እንጂ የብሄር ጭቆና የለም” ሲል የእነ መለስን ሌጋሲና ተራ አስተምህሮት ጎርዶ የጣለው ኦህዴድ፣ ለሰላም ካደረገው ከሁሉም ወገኖች ጋር  የ”አንነጋገር” ጥሪ ጋር ተዳምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙሪያ የመወያያ ቅመም እንዲሆን አስችሎታል። ብአዴን ውስጥ ካሉ ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች ጋር!!

የተለያዩ አስተያየቶች የ ” እነ ለማ ቡድን” በሚል የሌሎቹን የኦህዴድ ሃይሎች አለት የሆነ አቋም ዋጋ ባይሰጡትም፣ ኦህዴድ በክልሉ ባሉት የለውጥ ሃይል ደጋፊዎችና በመንፈስ ኢህአዴግን በተለዩ አባላቱ ትግልና መስዋዕትነት፣ በውጪና በአገር ውስጥ ባሉ የለውጥ አራማጆች ድጋፍ እዚህ ደረጃ ሊደርስ መቻሉ ላፍታም የሚዘነጋ አይሆንም። ይህ ሲታሰብ ዶክተር አብይ የሚይዙት ሃላፊነት ከቶውንም አቶ ሃይለማሪያም ከተቀመጡበት መቀመጫ የተለየ እንዲሆን ያደርገዋል።

ዶክተር አብይ አሁን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲንደረደሩ የተለመደው ዓይነት ለዛ ቢስ ውሸት ይዘው ህዝብ የሚቀርቡ ሊሆን አይገባም። ቅጥፈትን ለአፍታም ቢሆን ሊያስቡት አይገባም። በውስን ጉዳዮች ያየንላቸው ብቃት ሳይንሸዋረር አገርን ሊጠቅም በሚችል፣ ቂምና ጥላቻን ሊሰርዝ በሚችል፣ ከሁሉም አይነት ሃሎች ጋር ተቀራርቦ በመነጋገር የአገሪቱ ፈተና የሚወገድበትን አግባብ የሚከተሉ መሪ ሊሆኑ ይገባል።

ዶክተር አብይ በመጀመሪያው ንግግራቸው ምን ዓይነት መሪ እንደሆኑ በግልጽ ሊናገሩና ይህንን የተበታተነና ቀና አውራ የተራበ ህዝብ ድጋፍ ሊጠይቁ ግድ ነው። ከጅምሩ በግልጽ ምን እንደሚፈልጉ ተናግረው፣ ሕዝብ ላነሳቸው የዴሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ መልስ እንደማይሰጡ ካላረጋገጡ ለመናቅና ለመገፋት እጅግ የፈጠነ ጊዜ ያለው መሪ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም። ምክንያቱም ኢትዮጵያ አሁን በቅብና በጥገና የሚቃና ቀውስና በሽታ ላይ አይደለችምና።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ድምጽ

ዶክተር አብይ – 108  ድምጽ –  አቶ ሽፈራው ሽጉጤ –  59 ድምጽ  –  ዶክተር ደብረጽዮን  – 2  –  ደመቀ መኮንን ጭራሽ አልተጠቆመመ 

በሌላም ወገን የዶክተር አብይን ወደዚህ ሃላፊነት መምጣጥት ሲቃወሙ የነበሩ፣ ስም ሲያጠፉ የቆዩ፣ እሳቸው የስልጣን ጉጉት ስላላቸው አይመረጡም በሚል ሲያውጁ የነበሩ ” ውስጥ አዋቂ” ነን ባዮች በገጻቸው ዜናውን አውጀውታል። ለማንኛውም ፋና ስለ ዶክተር አብይ ካለው ይህንን ወስደናል

ዶክተር አብይ አህመድ ማን ናቸው?
የትውልድ ስፍራ፦ ጅማ ዞን

የትምህርት ዝግጅት፦ የመጀመሪያ ዲግሪ በኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ፣ ሁለተኛ ዲግሪ በትራንፎርሜሽናል ሊደርሺፕ እና ቼንጅ፣ ማስተርስ ኢን ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን እና በክሪፕቶ ግራፊ እንዲሁም የዶክትሬት ትምህርታቸውን በ“ፒስ ኤንድ ሴክዩሪቲ” አግኝተዋል።

የስራ ልምድ፦ በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ እስከ ሌፍተናንት ኮሎኔል ድረስ በተለያዩ ስፍራዎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል፣ የፌደራል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የልህቀት ማእከል ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል፣ በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ውስጥም በምክትል ዳይሬክተርነት አገልግለዋል። በተጨማሪም የኢፌዴሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በመሆኑ አገልግለዋል።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት እና ቤቶች ቢሮ ሃላፊ በመሆን ሰርተዋል። ዶክተር አብይ አህመድ የኢህአዴግ አባል ድርጅት የሆነው ኦህዴድ ሊቀመንበር ናቸው

 
 
 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0