መግብያ
ከመጋቢት 19/07/2010 ዓ/ም ጀምሮ ለኣራት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየና፣ ከመላ የትግራይ ኣከባቢዎች የተወከሉና ከመላው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች የተሳተፉበት ህዝባዊ ኮንፈረንስ በድል ተጠናቀዋል፡፡


የትግራይ ህዝብ እንደ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች ፣ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች ሁሉ በፀረ ህዝብ ፣ በፀረ ዴሞክራሲና በፀረ ልማት ስርዓቶች ለዓፈናና ድህነት ተጋልጦ ረጅም የመከራ ዘመን ያሳለፈ ህዝብ ነው፡፡ ከዚህ ብሄራዊ ጭቆናና መደባዊ ብዝበዛ የተነሳም ብሄራዊ ማነነቱ ተነፍጎ፣ ሰብአዊና ዴሞክራስያዊ መብቱ ተከልክሎ በከፋ ድህነትና ኋላቀርነት ሲማቅቅ የነበረ ህዝብ ነው ፡፡ የዓፈናና የጭቆና ስርዓቱን ከጫንቃው አሽቀንጥሮ ለመጣል በተለያየ ወቅት ሲያካሂደው የቆየው እንቅስቃሴ በተደራጀ አኩኋን ወደ ትጥቅ ትግል ተሸጋግሮ ለዴሞክራሲና ዴሞክራስያዊ አንድነት በከፍተኛ ፅናትና ብርታት ታግሏል ፡፡
ከመላ የኢትዮጵያ ህዝቦችና ዴሞክራስያውያን ኃይሎች ጋር በመሆን የትጥቅ ትግሉን አስተባብሮ ህዝባዊ አላማን ታጥቆ ፣ብቁ የአመራር አቅምና ፅናት በመፍጠር የድህነት ሆነኛ ዘብ ለነበረው ፋሽሽታዊ የደርግ ስርዓትና መሰል የትምክህትና ጠባብ ሃይሎች ዳግም ላይመለሱ ግብአተ መሬታቸው እንዲፈፀም አድርጓል፡፡ ወደርየለሽ የትግል ፅናት በማንገብና ለማመኑ የሚያዳግት ከፍተኛ መስዋእትነት በመክፈልም ድል ተቀዳጅተዋል ፡፡ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዲመሰረትም የራሱን ድርሻ ተወጥቷል ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች በመሪ ድርጅታቸው ኢህአዴግ እየተመሩ ባስመዘገቡት ከፍተኛ ድል የትግራይ ህዝብም ከሌሎች ወንድም ህዝቦች እኩልነቱን ተረጋግጦ መድሎና ሌሎች የጭቆና ቀምበር ተወግዶለት ሁሉም ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም የሚያረጋግጥለት ዴሞክራሲያዊ ስርአት ተመስርተዋል ፡፡
በውጤቱም ትናንት የድህነትና የኋላቀርነት ተምሳሌት ተደርጋ ትታይ የነበረች አገርና ክልል ከሌሎች ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን ባደረገው ትግልና እንቅስቃሴ ዛሬ የፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ፣ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታና የዘላቂ ሰላም ተምሳሌት ሃገርና ክልል እየገነባ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ በመሪ ድርጅታችን የተጀመረው የልማት፣ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታና ዘላቂ ሰላም የመገንባት ጉዳይ በታለመለት አኩኋንና ፍጥነት እንዳይራመድ ተግዳሮቶች አጋጥመውታል ፡፡ ድርጅታችነ ህወሓትም በኣሁኑ ወቅት ያጋጠሙት ፈተናዎች በሚገባ በመገምገምና በመተንተን እንዲሁም የመፍትሄ ኣቅጣጫዎችና መንገዶች በሚገባ ኣንጥሮ ዛሬም እንደ ትናንቱ ውስጡን በሚገባ በማየት እንሆ ወደ ተሃድሶ መድረክ ገብቶ ይገኛል፡፡የተሃድሶ እንቅስቃሴውም በውስጠ ድርጅት ብቻ ታጥሮ መቅረት የለበትም በማለት የተሃድሶ ንቅናቄው ወደ መላው የትግራይ ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች እያሸጋገረ ይገኛል፡፡
ህዝባዊ ትግላችን በየትግል ምእራፉ በርካታ እንቅፋቶች እየተሻገረና ያጋጠሙት ፈተናዎች በብቃት እየመከተ በድል ጎደና እየተረማመደ እዚህ ደርሰዋል፡፡የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ከቀላል እስከ በእጅጉ የተቆላለፈና የተሳሰረ የውስጥና የውጭ እንቅፋታች ያጣመረ ችግር እንደነበረ ይታወቃል፡፡ኣሁንም ኣለ፡፡ ድርጅታችን እንዲህ ኣይነቱ የተቆላለፉ ችግሮች ሲያጋጥም፣ ለውጭ ሃይሎች ክሴታ እያቀረበና እጅ እየነሳ ለመፍታት የሞከረበት ኣካሄድ ኣልነበረም፡፡የትግራይ ህዝብ በጭቆና የደሀየና በሁሉም ዓይነት መለክያ የተሰቃየ ህዝብ እንደነበር ድርጅታችን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ሆኖም የሁሉም ችግሮች መፍትሄ ራሱ የተጨቆነውና ድሃው ህዝብ መሆኑን ድርጅታችን ለኣንድም ቀን ቢሆን ዘንግቶ ኣያውቅም ፡፡ ከህዝቡ የተገኘውን ተካፍሎ፣የህዝቡ ቁራሽ እንጀራና ቆሎ ተካፍሎ ከህዝቡ ጋር በመሆን ሁሉም የህዝብ ችግሮችና መሰናክሎች በድል ተሻግሮ ለዚህ መድረክ ደርሰዋል፡፡
የህዝብ ወገንተኛ ያልሆኑ ሃይሎች ችግር ሲያጋጥማቸው ሊፈታልን ይችላል ወደሚሉት ጌታ ሲሯሯጡ ይስተዋላል፡፡ህዝብ ችግር ፈጣሪ እንጂ ችግር ፈቺ ነው ሊያስብል የሚያስችል ተፈጥሮም ዓላማም እንደ ሌላቸው የትግራይ ህዝብም ይሁን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀውና የሚረዳው ነው፡፡የድርጅታችን ጌታና ወሳኝ ሃይል ግን ህዝብና ህዝብ ብቻ ነው፡፡ችግርና እንቅፋት ሲያጋጥም መፍትሄ ለማግኘት ቅድምያ ሰጥቶ የሚሄደው ወደ ህዝቡ ነው፡፡ ለህዝብ በሚገባ በማስረዳትና መፍትሄዎችን በማስቀመጥ የህዝብ ምክርና ሃሳብ ኣዳምጦ፣ በህዝብ ተሳትፎና ወሳኝነት ተንቀሳቅሶ ችግርን በድል እየነሳ የመጣ ድርጅት ነው፡፡
ይህ ኣሁን “ኮንፈረንሳችን ለሰላም፣ ለልማትና ዲሞክራሲ” በሚል መሪ ቃል ታጅቦ ለ4 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ኮንፈረንስ ከላይ ላስቀመጥነው መሰረታዊ እውነታ በሚገባ ሁኔታ የሚያሳይና ድርጅታችን በህዝቡ ያለው የፀና እምነት በግልፅ የሚያረጋግጥ ነው፡፡እኛ ከ2000 በላይ ከመላ የትግራይ ኣከባቢ ህዝባችን ወክለን የመጣንና፣ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የምንኖር ቁጥራችን 100 የሚደርስ የትግራይ ተወላጆች እንዲሁም ከሁሉም የሃገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ወክለን የተሳተፍን ከ400 ተሳታፊዎች፣ የሃይማኖት መሪዎችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶቸ ይብዙሃንና ሙያ ማህበራት ተወካዮች ጨምሮ ከ2500 በላይ ተካፋዮች የተሳተፍንበት ኮንፈረንስ ነው፡፡በኣሁኑ ወቅት እያጋጠመን ያለው ችግር መነሻው በሚገባ ተረድተን፣ መፍትሄዎቹ በጥልቀተ በመለየት ከመላ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ያለንን ዲሞክራስያዊ ኣንድነት ኣጠናክረን የምንወጣበት ልዩና ታሪካዊ ኮንፈረንሰ ኣካሂደናል፡፡
ይህ በክልል ይሁን በሃገር ደረጃ ኣጋጥሞ ያለውን ችግር ስር ነቀል በሆነ መንገድ ለመፍታት የሚችል ኣብነታዊ የሆነ ድርጅት በማጠናከር ለተልእኮው ብቁ የሆነ የመንግስት መዋቅር በመፍጠር እና የህዝብ ሁሉን ኣቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር እንደሆነ መላው የትግራይ ህዝብና ወንድም ህዝቦች በሚገባ የምናምንበትና በውል የምንረዳው እውነታ ነው፡፡ስለዚህም ከመጋቢት 19 እስከ 22/07/2010 ዓ/ም ለኣራት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ኮንፈረንሳችን የተወያየንባቸው ርእሰ ጉዳዮችና የተደረሱ ድምዳሜዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
2. ህዝባዊ ኮንፈረንስና ውይይት የተረገባቸው ጉዳዮች
ያካሄድነው ኮንፈረንስ ትኩረት ያደረገባቸው ቁልፍ ኣጀንዳዎች የመሪ ድርጅታችን ህወሓት/ኢህኣዴግ ግምገማ መሰረት ያደረገ የሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ፣ የውስጠ ድርጅት ሁኔታና የትራንስፎርሜሽን ኣጀንዳዎች ኣፈፃፀም፣ የትግራይ ህዝብ ኣስተዋፅኦ፣ የዲሞክራሲ ስርኣት ግንባታ፣ ልማትና መልካም ኣስተዳደርና ቀጣይ ኣቅጣጫዎች የሚሉ ኣራት መሰረታዊ ኣጀንዳዎች ላይ ሰፊ ግምገማና ውይይት በማድረግ፣ በኣንድ ወይ ተመሳሳይ ኣስተሳሰብና ድምዳሜ ደርሰናል፡፡በመሆኑም እንደህዝብ የሚደርሰን ኣስተዋፅኦ ለማንጠናክር የሚያስችል ባለ 15 ነጥብ የያዘ የኣቐም መግለጫ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
1. የትግራይ ህዝብ ጥሪን ኣክብረው ከሁሉም የሃገራችን ኣቅጣጫዎች እዚሁ ኮንፈረንስ ለመሳተፍ የመጡ የሁሉም ብ/ብ/ህዝቦች ተወካዮች በዚሁ ኮንፈረንስ ለነበራቸው የላቀ ተሳትፎና ላበረከቱት ገንቢ ሃሳብ ፣ ለትግራይ ህዝብ ይጠቅማሉ ብለው ያነስዋቸው ጥያቄዎችና ኣስተያየቶች ከልብ ለማመስገን እንወዳለን፡፡ ከሁሉም የኢ/ብ/ብ/ህዝቦች የተወከሉ ተሳታፊዎች ከሰጡት ገንቢ ሃሳብ በመነሳት የሃገራችን ህዝቦች ህይወት እና ልማት በጋራ መተጋገዝ እና መረዳዳት የተመሰረተ እንደሆነ እና መስራት እንደሚገባም ኣረጋግጠዋል፡፡ ለቀጣይም ቢሆን ሃገራዊ ጥቅማችን እና ኣንድነታችን ኣጠናክረን እንደምንቀጥል እያረጋገጥን ዴሞክራስያዊ አንድነታችን ለማጨናገፍ ላይ ታች የሚሉ ፀረ ህዝብ ሃይሎች በጋራ እንደምንታገላቸው ቃል እንገባለን፡፡
2. የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅታችን ህወሓት ያካሄዱት እልህ ኣስጨራሽ ትግልና ከፍተኛ መስዋእትነት ኣዲሲትዋ ፌደራላዊት ዴሞክራስያዊት ኢትዮያ በመገንባት የተጫወቱት ኣስተዋፅኦ መተክያ የለውም፡፡እኛ የዚህ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የህን የሁሉም የሃገራችን ብ/ብ/ህዝቦች ተወካዮችና የትግራይ ህዝብና ህወሓት ይህንን ኣዲስ ስርዓት በመገንባት የነበራቸው ኣስተዋፅኦ ታሪክ የማይረሳው የኢትዮያ ህዝብ ቀዋሚ ሃወልት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ የትግራይ ህዝብ ኣሁንም ከሌሎች የሃገራችን ህዝቦች በመሆን ዋስትና ያለው ሰላም ፣ ፈጣንና ፍትሃዊ ልማት፣ የዴሞክራሲ ስርኣት ግንባታና መልካም አስተዳደር በማረጋገጥ የሃገራችን ህዳሴ እውን ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ ፅኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መከታ ሆኖ እንደሚቀጥል አንጠራጠርም፡፡
3. ባለፉት 27 ዓመታት በሃገር ደረጃ የተመዘገቡ የሰላምና የዴሞክራሲ ድሎች የሁሉም ብ/ብ/ህዝቦች ጥቅም ያረጋገጡ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ በከፍተኛ መስዋእትነትና ትግል ያገኘነው ሰላም የሚበጠብጡና፣ ፌደራላዊ ስርአታችን ለአደጋ የሚጋልጥ ሁኔታዎች ገጥሞናል፡፡ እኛ የዚህ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ለነዛ ሰላማችን የሚነሱን አካላት በሚገባ እየተቃወምንና በፅናት እንደምንታገላቸው እያረጋገጥን ዋስትና ያለው ሰላማችን ወደ ቦታው ለመመለስ በሚደረገው ርብርብ ከኛ የሚጠበቅ ሁሉን አቀፍ ትግል ለማካሄድ መዘጋጀታችን ቃል እንገባለን፡፡
4. የሃገራችን ብ/ብ/ህዝቦች ለብዙ መዋእል እና ትውልድ በደም፣ በታሪክ፣ በባህል፣ በእምነት፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ሰንሰለት የተጣመርንና የተሳሰርን ነን፡፡በደስታም ይሁን በኣስቸጋሪ ግዜና ሁኔታ በፍቅርና መተጋገዝ የተገነባ አንድነታችን ቀደም ሲሉ የነበሩ አፋኝና ግፈኛ ስርአቶች ሊበጣጥሱት አልቻሉም፡፡ በዚሁ ወቅትም አንድነታችንና አብሮነታችን ሕገ መንግስታዊ መሰረት ይዞ በእኩልነት ፣ መከባበር፣ በጋራ ፍላጎቶቻችንና ጥቅም ተንተርሶ የታነፀ አንድነታችን በበለጠ ለማጠናከርና ያለን ብቸኛ አማራጭ ኣብሮ መልማት ወይ አብሮ መጥፋት እንደሆነ በማመን ሰላማችን የሚያደፈርስ ማናቸውም ተንኮልና መሰሪ ተግባርና ሴራ በጣጥሰን ፌደራላዊ ዴሞክራስያዊ ስርአታችን በአንድነት ለመጠበቅ ቃል እንገባለን፡፡
5. የትግራይ ህዝብና የህወሓት የበላይነት አለ በሚል በውስጥም በውጭ ማህበራዊ ሚድያዎችና ድህረገፆች ፣ በሌሎች ፅንፈኛ ዲያስፖራ በመረጨት ያለውና የነበረው የጥላሸት ወሬ፡ የተሳሳተ ነጭ ውሸት እንደሆነ በኢህአዴግ ባደረገው ግምገማ የተረጋገጠ ነው፡፡ እኛ የዚሁ ኮንፈረንስ ተሳታፊ የሁሉም ብ/ብ/ህዝቦች ተወካዮችም በተመሳሳይ መልኩ በዓይናችን አይተን ያረጋገጥነው ስለሆነ የኢህአዴግ ውሳኔና ግምገማ ትክክል እንደሆነ ደግመን እናረጋግጣለን፡፡ የዚሁ አጀንዳ መነሻና መዳረሻ የዚሁ እንቆቁልሽ ባለቤቶች አንድነታችን የማይፈልጉ የጥፋት ሃይሎች የፈጠሩት፣ በዚሁ የጥፋት አጀንዳዎቻቸው የእርስበእርስ መጠፋፋት እንዲኖር ሆን ብለው ያሴሩት ሴራ እንደሆነ ግልፅ ሆነዋል፡፡ ይህ እንቆቁልሽ በማናፈስና በማስፋት የተጠመዱ አካላት ዋነኛ ዓላማቸው ለትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት ነጥሎ በመምታት ፣ በህዝቦች መካከል ክፍተት በመፍጠር ህዝቡና መሪ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ህዝቦች ለይቶ ፣ ለዚሁ አዲስ ተስፋ ለፈጠረ ህዝብና ሃገር በከፍተኛ ደረጃ የማፈራረስ አደጋ እንዲያጋጥመው ያለመ ነው፡፡ ስለዚህም ሁሉም የኢህአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶችና፣ ፍትሃዊና ዴሞክራስያዊ ፌደራላዊ ስርአታችን ለማንኛውም ብሄር በተለየ መልኩ የሚያዳላና የተለየ ጥቅም እንደማይፈቅድና በዚህ ዙርያ የሚነሳ መሰረት የለሽ አጀንዳ መሆኑን ተረድተው እንዲመክቱትና ፣ የትግራይ ህዝብና ህወሓት የበላይነትና ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ የሚል የጠላት አጀንዳ መሆኑን በመገንዘብ መላ የሃገራችን ህዝቦች በፅናት እንደምንታገለው ልናረጋግጥ እንወዳለን፡፡
6. በልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚታዩ ችግሮች ዋነኛ ምንጭ ኋላቀርነትና ድህነታችን መሆኑ አጥብቀን የምንረዳውና የምናምንበት ነው፡፡ ይህ ኋላቀርነታችንና ድህነታችን ምንጭ የሆነ ጠላታችን ዛሬም እንደትናንቱ በልማታዊና ዴሞክራስያዊ መስመራችን በፈጠረልን ፀጋዎች ተጠቅመን ፣እስከአሁን ያረጋገጥነው የህዳሴ ሂደት በማስጠበቅና የቀሩንን በማማላት ለአንዴና ለመጨረሻ ድል በማድረግ፣ በወጣት ልጆቻችን ያለው የማብቃትና የተጠቃሚነት ጉድለት በወሳኝ መልኩ የወላጆችና የህዝብ ተሳትፎ አስፈላጊ በመሆኑ ተረድተን የበኩላችን ኣስተዋፅኦ እንዲኖረን ፣በሴት እህቶቻችን የሚደርስ ማናቸውም ጥቃት ለመከለከልና በዚሁም የትራንስፎርሜሽን ዕቅዶቻችን በብቃት ለማሳካት እንደሚገባን ኣምነን፣ በገጠር የክረምት ምርታማነትን የሚጨምሩ የአቅርቦትና ቴክኖሎጂዎች በመልካም ፍላጎቶቻችን ኣሟልተን መጠቀም ፣በከተማም ዕድገት ተኮር በሆነ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቛማት ስራዎቻችን በተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በሚደረገው ትግል የመሪነት አስተዋፅኦኣችን ለማበርከት ቃል እንገባለን፡፡
7. በፌደራላዊ ስርአታችን ፣ ሕገመንግስታችን በተለይም ከአብራካችን የተፈጠረና የመጨረሻው የፌደራላዊ ዴሞክራስያዊ ስርአታችን መከታና አለኝታ የሆነውን የሃገራችን የፀጥታ/መከላከያ ሓይል ህዝባዊነቱ በተመለከተ እኛ ብቻ ሳንሆን መላ የዓለም ህዝብ የመሰከረለት ሆኖ ሳለ በትምክህትና ጠባብ ሃይሎች እየደረሰ ያለው የስም ማጉደፍ ዘመቻና ጥቃት መሰረታዊ ዓለማው ፣ ስርአት ለማፍረስ ዓልሞ የሚደረግ እንቅስቃሴ መሆኑን ድምዳሜ ላይ ደርሰናል፡፡ በመከላከያ ሃይላችን የሚካሄድ ማናቸውም የስም ማጥፋት ዘመቻና ኣሉቧልታ እንቃወማለን፡፡ በዚሁ መሰሪ ተግባር ለተሳተፉት ሁሉ ያለምንም ድርድር አጥብቀን እንቃወማለን፡፡
8. የዜጎች መብት ከዜጎች ግዴታ ነጥሎ የሚታይ ኣይደለም፡፡የዜጎች መብት የሚከበር የሌሎች መብት እስካልነካና እስካልጣሰ ነው፡፡ዴሞክራሲና አመፅ አብረው አይሄዱም፡፡ አንዱ የሌላኛው ፀር ነውና፡፡ህዝብና መንግስትም ይህንን ዓይነት ተግባር በምንም ዓይነት መልኩ ለድርድር የሚያቀርቡት አይደለም፡፡የዜጎች ሂወት እንዳይጠፋ፣የዜጎችና የመንግስት ንብረት እንዳይወድም አስፈላጊው ትግልና መስዋእትነት በመክፈል ለመጠበቅ ያለንን ዝግጁነት ከፍተኛ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ይህ ስለሆነም መንግሰት ሰላማችንን ለማስጠበቅ አልሞ ያወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ያለንን ድጋፍ እየገለፅን ለተግባራዊነቱ እንደምንረባረብ ቃል እንገባለን፡፡
9. ሕገ መንግስታችን ለማንኛውም ዜጋ በመረጠው የሃገሩን አከባቢ ሂዶ በማናቸውም ህጋዊ የስራ ዘርፍ እንደሚሳተፉና በህይወትም ሆነ በንብረቱ በማናቸወም ሃይል ጉዳት እንዳይደርስበት ዋስትና ማግኘቱ ይታወቃል፣መንግስትም ይህን ህገመንግስታዊ መብት የሚጥስ አካል ይሁን ግለሰብ ወይም የተደራጀ ሃይል ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምት ሊያደርግለት እና ያለምንም ድርደረ በፍጥነት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲወሰድ ጥርያችን እናቀርባለን፡፡
10. በሃገር ደረጃ ኢህአዴግና መንግስት፣በክልል ደረጃ ደግሞ ብሄራዊ ድርጅቶችና ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ለህዝቦች ጥያቄ በሚችሉት ዓቅም ሊፈቱ፣የወጣቶቻችን ችግር የቤተሰብ፣የመላው ህዝብና የተተኪው ትወልድ ችግር መሆኑ በመገንዘብ የተለየ ትኩረት እንዲሰጡት ጥርያችንን እያቀረብን፣ ቃል መግባት በሚመለከትም ሊተገበር የሚችልና የህዝብ ጥያቄ በሚገባ የሚመለስ ለይቶ ቃል መግባት የማይቻል ኮሆነም ከህዝብ ጋር በግልፅ በመመካከር እንደማይቻል መግባባት እንዲደረግለት፣አጉል ተስፋ መስጠት ህዝብ በድርጅትና መንግስት ላይ ያለው እምነት የሚያሳጣ አካሄድ መዘጋት እንዳለበት ለድርጅቶቻችንና መንግስታችን ማሳሰብ እንፈልጋለን፡፡
11. የተሃድሶ እንቅስቃስያችን በፍጥነት ጨርሰን በመውጣት ወደ ተግባር መግባት አለብን ፡፡በዚህ የተግባር እንቅስቃሴ ህዝብ ባለቤት ሁኖ በሚገባ የድርሻው እንዲወጣ ሁሉም በየደረጃው ተጠቃሚ እንዲሆን እንሰራለን፡፡ስለዚህ በድርጅት መሪነትና በመንግስት አስፈፃሚነት የተቀናጀ ሁሉአቀፍ የህዝብ ተሳታፊነት በሰላም፣ልማት፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በሚደረግ ርብርብ ከኛ የሚጠበቅ ሁሉ እንደምንፈፅም ቃል አንገባለን፡
12. በፀረ-ዴሞክራሲ፣መልካምአስተዳደርና ፍትህ እጦት ፣በኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና ላይ የሚደረግ ትግል በድርጅት የውስጥ ዝግ መድረክ ታጥሮ የሚካሄድ መሆን የለበትም ፡፡በድርጅት አጥር የሚወሰን ከሆነ ውጤት አይኖረውም፡፡የግልፅነትና ተጠያቂነት መርህ የሚረጋገጥ ፣ህዝብ ባለቤት አድርጎ የሚያሳትፍ አመለካከትና መምርያ በመያዝ እንዲካሄድና ተግባር ላይ እንዲውል ጥርያችን እናቀርባለን፡፡ህዝብም ለተጀመረው የተሃደሶ እንቅስቃሴ ለማሳካት ትግሉ እንዲያበረታና ከሁሉም ኋላቀርነት ነፃ በመሆን የመስመሩ ጥራት ለማረጋገጥ ከሱ የሚጠበቅበት ሁሉ እንደሚያደርግና የዚህ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎችም የበኩላችን የመሪነት ድርሻችን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጠለን፡፡
13. በኢህአዴግ እሀት ድርጅትና አጋር ድርጅቶች ማናቸውም መጠራጠር በማያዳግም ሁኔታ ተፈቶ የድርጅቶቹ አንድነት፣ህብረት ተረጋግጦ የጋራ ብቁ መሪነት የሚረጋገጥበት ሁኔታ ከልተፈጠረ ጉዳቱ የህዝቦች አንድነት በመፈታተና ጉዳት እንደሚያደርስ በተግባር እየታየ ስላለ ሁሉም ድርጅቶች አንድነታቸው በፍጥነት እንዲያረጋግጡ ጥርያችን እናቀርባለን፡፡በዚህ በኩል የሚታይ ችግር የአመራር አንጂ የህዝብ እንዳልሆነ ልናሰምርበት እንፈልጋለን፡፡በዚህ በኩል ሁሉም እህት ድርጅቶች በመርህ የተመሰረተ ዴሞክራስያዊ አንድነታቸው እንዲያጠናክሩ እንደ ህዝብ ተደራጅተን በምናረገው ትግል የድርሻችን እንደምንወጣ ቃል እንገበለን፡፡
14. ብሄር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማናቸውም መንገድ ተቀባይነት የሌለው የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰበች የአንድነታቸውና ወንድምነታቸው ፀር ነው፡፡ይህ እኩይ ተግባር ለማንኛውም ብሄር የማይወክል የትምክህተኞችና ጠባቦች ተንኮል መሆኑ አንጠራጠርም፡፡ከዚህ ተነስተን አንድነታችንና አጋርነታችን ለማጠልሽት ላይ ታች ለሚሉ አካላት አንድ ሁነን ለመታገል ቃል እንገባለን፡፡
15. ይህ ዓይነቱ የሰላም፣የልማትና ዴሞክራሲ ህዝባዊ ኮንፈረንስ ብሄር ብሄረሰበች እርሰበርሳችንን የበለጠ እንድንተዋወቅና በችግሮቻችንና ድሎቻችን ላይ አብረን እንድንመካከር በዚህም አንድነታችን ለማጠናከር ሰፊ እድል የሚፈጥር በመሆኑ የህ በህወሓትና የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተጀመረ አብነታዊ ተግባር አድናቆታችንና ድጋፋችን እየገለፅን እንዲህ ያለ መድረክ የህዝቦች አንድነትና ተሳትፎ ለማጠናከር ጠቀሜታው ከፍ ያለ መሆኑ ተገንዝበን ተመሳሳይ መድረኮች በፌደራልና በሁሉም ክልላዊ መንግስታት እንዲካሄድ ጥርያችን እናቀርባለን፡፡

ዘለአለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማእታት!
ህዝብ ያመነ ያሸንፋል!
መጋቢት 22/2010ዓ.ም
መቐለ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *