አሳሳቢው ነጥብ ግን ለዶ/ር አብይ አህመድ የሰጠነውን ጊዜ እየተጠቀመ ያለው አልሞት ባይ ተጋዳዩ ህወሀት ሰለሆነ ከፈርዖን መንደር የተገኘ አዳኙ ሙሴ ከጨዋታ ውጭ ሊሆንበት የሚችለው መንገድ በጣም ሰፊ ነው።

 
በእርግጥ እንደ ብዙሃኑ ስጋት በስርዓቱ ወሳኝ የተባሉ እንደ ደህንነት፣መከላከያ፣ የምጣኔ ሀብት ይዞታዎች፣ ወዘተ በህወሀት እጅ እያለ ስልጣን አልባው የጠቅላይ ሚንስቴርነት ሰውየው ለውጥ አራማጅ ቢሆኑም እንኳ አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው እሙን ነው።
 
ችግሩ ግን ይህ ብቻ አይደለም፣ ሀገረቷ ያለችው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም በታወጀው ወታደረዊው አስተዳደር ስር መሆኗ ነው። የሄ ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትሩ በህገ-መንግስት ከሚሰጣቸው ስልጣኖች አብዝኞቹን ያነሳባቸዋል።
 
በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ለውጥ አራማጆቹ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የሚጠብቁት የመጀመሪያው እርምጃ ይህንን አዋጅ በማንሳት እራሳቸውን ባለ ሙሉ ስልጣን እንዲያደርጉ ነው። ምክንያቶቻቸው ደግሞ ግልጽ ነው። አሻንጉሊት ተነስቶ ስልጣን አልባው መሪ መቀየሩ ትርጉም ስለማይሰጥ ነው።   በደፈናው ግን እስኪ ጊዜ እንስጠውና እንየው የተባለ ይመስላል።
 
ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከመተዋወቂያ ንግግራችው ጀምሮ በስልጣን መንበራቸው ባሳለፉት ጥቂት ቀናቶች ምን ይመስላሉ ካልን፣ ተስፋ ለጣለባቸው እንደ አፋቸው ያድርግልን ስያሰኝ፣ ለተቀሩት ደግሞ ስጋት መደቀኑ አልቀረም።
ይህ ስጋት እንደሁ ዝም ብሎ ስጋት ብቻ ሳይሆን መኖርም ያለበት ስጋት ነው።
 
ምክንያቱም ህወሀት አዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ ያለውን ሀይል በሙሉ እየተጠቀመ ይገኛልና።
 
ባጠቃላይ ሰውየው አንደበተ ርቱዕ ናቸው፣ ሰለዚህ ባፋቸው የተናገሩትን በተግባር ለማሳየት ጊዜ ሰለሚያስፈልግ እስኪ ጊዜ እንስታቸው መባሉ ተገቢ ይመስለኛል።  ተገቢ ይመስለኛል።ተገቢ ይመስለኛል። የስጠነ ጊዜ ለህወሀት እንደ መልካም አጋጣም የሚያዩም አሉ።
 
ህወሀት እጅ ላለመስጠት እያደርገ ካለው ትግል አንዱ ከተለመደው ሁኔታ በተለየ ብሄርን ከብሄር በማጋጨት ጠቅላይ ሚንስትሩ በህዝብ ዘንድ ያገኙትን ተቀባይነት እንዲያጡ ለማድረግ እየታገሉ መሆኑ መዘንጋት የለለበት ጉዳይ ነው።
 
ከዚህ ጋር በተያያዘ ህወሀት በኢህአዴግ ግንባር ውስጥ የገጠመው ሽንፈት ለማካካስ ትናንት እራሱ አናሳ ብሄር፣ አጋር ፓርቲ ሲላቸው የነበሩትን እንደ ሶማሌ፣ አፋር፣ ቢንሻጉል ጉሙዝ፣ ሃረሪ የመሳሰሉትን እኛም የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብላችሁ ጠይቁ በማለት እያሰላጠኑ መሆኑን አረጋግጠናል።
 
በእርግጥ እነዚህ ክልሎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በመሳተፍ መብታቸውን የመጠየቅ ብቃት አላቸው እንጂ ከማንም አያንሱም፦
 
ግን ይህ የሚሆነው ለህወሀት አብላጫ ድምጽ ለማስገኘት ሳይሆን በነጻነት፣ በዲሞክራሲና በእኩልነት ሰለሀገራቸው ጉዳይ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ የህዝባቸው ሙሉ ውክልና በማገኘት መሆን አለበት።
 
በተለይ አፋር ክልልን የሚመራው የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( አብዴፓ ) ህወሀት ከጫካ ባመጣቸው ያልተማሩ የህወሀት ካድሬዎች በሚመራበት ሁኔታ፣ እኛ ከለለን አብቅቶላቹሃል በሚል ማስፋራሪያ የአፋር ህዝብን የማይወክሉ ማሃይሞችን በማምጣት መሆን የለበትም። እየቀሰቀሱ ይገኛሉ።
 
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር በተሾሙ ማግስት በውጭ ሀገራት የሚገኙ አንዳንድ የኢትዮጲያ ኢምባሲዎች የአፋር ድጋፍ እንዳላቸው ለማስመሰል ከጥቂት ሆድ አደሮች ጋር በመሆን ህፃናትን የአፋር ባህል ልብስ በማልበስ ማስተላለፍ የተፈለገውም አፋር ምን ጊዜም ከህወሀት ጋር ነው የሚለው መልዕክት ነው።ተላለፍ የተፈለገውም አፋር ምን ጊዜም ከሀወሀት ጋር ነው የሚለው መልዕክት ነው።
ለዚህ ደግሞ ብዙ ገንዘብ እያወጡ መሆኑን ይታወቃል።
 
የአፋር ህዝብ ከሚፈልገው ለውጦች ቀዳሚው መሆን ያለበት አብዴፓን ወደ ኢህአዴግ ማምጣት ሳይሆን መጀመሪያ ፓርቲው በህዝብ ተቀባይነት ባላቸው ምሁራን መሪዎች በመቀየር፣ ሙስኞችንና አፋኞችን ለፍትህ ማቅረብ ነው። በመጨረሻም ጊዜ የስጠነው ለጣቅላይ ሚንስቴር ቢሆንም ጊዜውን ወያኔ እንዲጠቀምበት መፍቀድ የለብንም።

ከአካደር ኢብራሂም

Related stories   የአዴፓ በረራዊ ጋዜጣዊ መግለጫ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *