“ወልቃይት እኮ ትግራይ ክልል ነው “አለኝ። እኔም “አዎ! ግን መሬቱና ሰው አማራ ነው” ስላቸው ተበሳጩና እስከ ሌሊቱ ስድስት ስዓት ድረስ ሲደበድቡኝ አመሹ። በመጨረሻም “ሂድ ቆሻሻ” ብሎ ገፍትሮ አስወጣኝና ሳቤሪያ ወደ ሚባለው ቀዝቃዛና ጨለማ ቤት አስገቡኝ።

ጌታቸው ሺፈራው – ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው የተፈፀመብኝ። ይህ ሁሉ የደረሰብኝ አማራ ነኝ ስላልኳቸው ነው። “አሁንም አማራ ነኝ። ግደሉኝ እንጅ ብሔሬንማ አልቀይርም” ስላቸው ተናደው ነው በደል የፈፀሙብኝ”
” እኔ ከግንቦት 17 ቀን 2009 ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት ከምሽቱ 2 ስዓት እስከ ሌሊቱ 9 ስዓት እያቆዩ መርምረውኛል። ምርመራው ሁሌ በቀን 3ጊዜ ሲሆን ለ29 ቀን 87 ጊዜ አመላልሰው መርምረውኛል። ለተከታታይ 10 ቀን በአንድ ሌሊት 3ጊዜ በድምሩ ለ30 ጊዜ መርምረውኛል። በአጠቃላይ 117 ጊዜ በአሰቃቂ ሁኔታ መርምረውኛል። ስጋየን በልተዋል። ደሜን መጠዋል። 2 ቀን ቁጭ ብድግ 900 ጊዜ አሰርተውኛል። እየደበደቡ ሁለት እግሬን ሽባ አደረጉት። መደብደብ ሲሰለቻቸው በኮምፒውተር ጌም ይጫወታሉ። በአንድ እግራችን ቆመን እጆቻችንን በካቴና ይታሰራሉ። ግድግዳ ተደግፈን እንድንቆም ያደርጋሉ። ከግድግዳው ላይ 12 ቁጥር ሚስማር ተሰክቷል፣ ሚስማሩ ላይ በካቴና የታሰረውን እጅህን ያንጠለጥላሉ። በቃ እንደሚገፈፍ ፍየል ትንጠለጠላለህ። ሙሉ ክብደትህ በካቴና ላይ ይሆናል። የተንጠለጠለውን እግርህ በካቴና ትገረፋለህ”

”የከፈልኩት መስዋዕትነት ሁሉ ያኮራኛል” 1ኛ ተከሳሽ ነጋ የኔነው

(ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ ፌስቡክ ገፅ ላይ የተወሰደ)

መቸም ቢሆን የማረሳው ቀን ሚያዚያ 4 ቀን 2009 ዓ•ም ነው። በጎንደር ከተማ ን የታሰርኩት። ወደ አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ ወሰዱኝ። አስር ሆነው እንደ ኳስ ተቀባበሉኝ።

እስከ ሚያዝያ 16 ማታ 6ስዓት ድረስ ምግብ አልሰጡኝም። ሚያዚያ 16ቀን 2009 ዓ•ም ከሌሊቱ 11ስዓት በማፈን በክፍት ፓትሮል ጭነው ወደ ማዕከላዊ አመጡን። በመቀጠልም ትንሽ እንኳ ሳላርፍ ነጥለው ወደ አንደኛ ፎቅ ቁጥር4 የምርመራ ክፍል ወሰዱኝ። ሶስት ደህንነቶች እንደ ውሻ ወረወሩኝ። ፂሜንና የራሴን ፀጉር እየነጩ መጠየቅ ጀመሩ። ከመካከላቸው አንዱ “ከየት ነው የመጣህው?” አለኝ “ከጎንደር አልኩት። ቀጥሎም”ብሄር? ” ሲለኝ “አማራ ነኝ” አልኩት። የትውልድ ቦታዬን “ወልቃይት” ብየ መለስኩ ።

“ወልቃይት እኮ ትግራይ ክልል ነው “አለኝ። እኔም “አዎ! ግን መሬቱና ሰው አማራ ነው” ስላቸው ተበሳጩና እስከ ሌሊቱ ስድስት ስዓት ድረስ ሲደበድቡኝ አመሹ። በመጨረሻም “ሂድ ቆሻሻ” ብሎ ገፍትሮ አስወጣኝና ሳቤሪያ ወደ ሚባለው ቀዝቃዛና ጨለማ ቤት አስገቡኝ።

“84 ቁጥር”የሚባል በውስጡ 4 ጠባብ 3ክንድ የጎን ስፋት ያላቸው ጨለማ ክፍሎች አሉት። መስኮት እና መብራት የለውም፣ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ለፀሀይ ታጅበህ ከበሩ ትወጣለህ። ከጨለማዋ ክፍል ስትወጣ አይንህ ለ5ደቂቃ ያህል ለማየት ይቸገራል።ገና ከመውጣትህ በቅጡ ተረጋግተህ ቁጭ ከማለትህ “ተነስና ግባ”ትባላለህ። ለሽንት መውጣት የሚፈቀደው በቀን ሁለቴ ጠዋት 11ስዓት ተኩል እና ማታ 10ስዓት ላይ ነው። ከ1 ቁጥር እስከ 10 ቁጥር ያሉ ክፍሎች ሲኖሩ ስምንት ቁጥር ጨለማ ቤት ነው። መጀመሪያ ለወር ያህል ከሰው ጋር በሳይቤሪያ ቁጥር 6 ክፍል አስረው ሲመረምሩኝ ከቆዩ በኃላ ለብቻየ እንድታሰር በመወሰኑ ወደ 8 ቁጥር ጨለማ ክፍል ነጥለው ወስደው አሰሩኝ።

ይህ ክፍል ከሌሎች የሚለየው ብቻህን የምትታሰርበት መሆኑ ነው። ምርመራ ሌሊት ሌሊት እየመጡ ምርመራ ይወስዱሀል። ከሌሊቱ 9 ስዓት ይመልሱሀል። ምግብ በፖሊስ እጅ ነው የሚሰጥህ። እኔ ከግንቦት 17 ቀን 2009 ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት ከምሽቱ 2 ስዓት እስከ ሌሊቱ 9 ስዓት እያቆዩ መርምረውኛል። ምርመራው ሁሌ በቀን 3ጊዜ ሲሆን ለ29 ቀን 87 ጊዜ አመላልሰው መርምረውኛል። ለተከታታይ 10 ቀን በአንድ ሌሊት 3ጊዜ በድምሩ ለ30 ጊዜ መርምረውኛል። በአጠቃላይ 117 ጊዜ በአሰቃቂ ሁኔታ መርምረውኛል። ስጋየን በልተዋል። ደሜን መጠዋል። 2 ቀን ቁጭ ብድግ 900 ጊዜ አሰርተውኛል። እየደበደቡ ሁለት እግሬን ሽባ አደረጉት። መደብደብ ሲሰለቻቸው በኮምፒውተር ጌም ይጫወታሉ። በአንድ እግራችን ቆመን እጆቻችንን በካቴና ይታሰራሉ። ግድግዳ ተደግፈን እንድንቆም ያደርጋሉ። ከግድግዳው ላይ 12 ቁጥር ሚስማር ተሰክቷል፣ ሚስማሩ ላይ በካቴና የታሰረውን እጅህን ያንጠለጥላሉ። በቃ እንደሚገፈፍ ፍየል ትንጠለጠላለህ። ሙሉ ክብደትህ በካቴና ላይ ይሆናል። የተንጠለጠለውን እግርህ በካቴና ትገረፋለህ።

በኤሌክትሪክ የተገረፍኩት እግሬ ደም በደም ሆኖ መንቀሳቀሻ አጥቸ ነበር።በካቴና ላይ በመንጠልጠሌ የተነሳ ሁለቱ የእጀ አውራ ጣቶች አይሰሩም።
ነጥለው ለምን አስቀሩኝ:አሁንም ይህ ጠባሳና ግፉ እንዳይታይ ነው ወደ ኃላ ነጥለው ያስነጥለው ያስቀሩኝ። ምክንያቱም እኔን ለመበቀል ሲሉ የማላውቃቸውን ከሰሜን ጎንደር በለሳ 3፣ ከደቡብ ጎንደር 3 ሰዎችን መልምሏል ብለው 1ኛ ተከሳሽ አድርገው ከሰሱኝ።

በዚህ መዝገብ 7 ሰዎችን በፀረ ሽብር አዋጁ አንቀፅ 3(2)(4) ብለው የከሰሱን ሲሆን 3ቱ ባለፈው ዙር ክሳቸው ተቋርጦ ተፈትተዋል። ያልተፈታን 4 ሰዎች እስር ላይ እንገኛለን።

ጥቃቱ ለምን?

ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው የተፈፀመብኝ። ይህ ሁሉ የደረሰብኝ አማራ ነኝ ስላልኳቸው ነው። “አሁንም አማራ ነኝ። ግደሉኝ እንጅ ብሔሬንማ አልቀይርም” ስላቸው በጣም ነው የተናደዱ። ጎንደር ላይ የነበረውን እንቅስቃሴ የታወቀ ነው። “ያቀናበሩትንና እጃቸው ያሉበትን ሰዎችን ጥራ፣ብዙ ሚስጥር ታውቃለህ አውጣ!” በሚል ነው የደበደቡኝ። ማንነቴን አለቅም በማለቴ ነው ተሰቅየ የተቀጠቀጥኩት። በዚህም ምክንያት የጤና ሁኔታ ታውኳል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *