“ከተፈታሁ በኋላ ሰው ሞልቷል። ታስሬ ግን ልጆቼን እንዴት ናችሁ? ብሎ የሚጠይቃቸው አልነበረም። ባለቤቴን የሚያበረታታት ሰው አልነበረም። አሁን እኔ ስፈታ ሰው ሞልቷል።……”  ስሰማው አመመኝ!

ግን እንደገና አመመኝ!… አንዱዓለም ከተፈታ በኋላ ወደ ቤቱ ሄደን ታምሜ ነበር የተመለስኩት። አንዱዓለም ቅን፣ ደግሞ ቀጥተኛ ሰው ነው። ጥሩ እያወራን እያለ፣ የእኛን ክፉ ባህል በግልፅ ነገረን። ያሳምም ነበር።

 

“ከተፈታሁ በኋላ ሰው ሞልቷል። ታስሬ ግን ልጆቼን እንዴት ናችሁ? ብሎ የሚጠይቃቸው አልነበረም። ባለቤቴን የሚያበረታታት ሰው አልነበረም። አሁን እኔ ስፈታ ሰው ሞልቷል።……” ነበር ያለን።

አንዱዓለም ሲያንሰው ነው! ሲፈታ መሄዳችን መልካም ነው፣ ሲፈታ መሸለማችን ሸጋ ነው! ግን ታስሮ ሳለ፣ ሚስቱ ብቻዋን ስትሆን፣ ልጆቹ ሲያለቅሱ ይህን ማድረግ ነበረብን!

ናትናኤልን፣ አበበን፣ ሌሎቹንም ያኔም ማስታወስ ነበረብን። ሲፈቱ የምናደርግላቸውን ሩቡን ታስረው ሳለ ብናደርግላቸው እንዲህ ባልተጎዱ ነበር። አሁንም ቢሆን መልካም ነው! አሁን ስንሸልማቸውም ግን “ረስተናችሁ ስለነበር ይቅርታ አድርጉልን” ብለን ጭምር መሆን አለበት! ምክንያቱም ሲያንስባቸው ነው! ምክንያቱም ታስረው ሳለ ረስተናቸው ነበር። ምክንያቱም አሁንም በርካታ እስረኞችን ረስተናቸዋል! ልብስ ከሌላ እስረኛ ተውሰው የሚለብሱ የፓርቲ አባላት፣ ስለ ሕዝብ የታሰሩ ሞልተዋል። ዛሬ በእስር ቤት እያሉ እነሱንና ቤተሰቦቻቸውን አግዘን፣ ነገ ሲወጡ ብንንጋጋ፣ አንገታቸውን አንቀን ፎቶ ብንነሳ፣ ብንሸልማቸው “ሸለምናቸው!” ማለት እንችል ነበር! አሁን ግን እያፈርን ነው “መሸለም” ያለብን!

ማሳሰቢያ:_ ወቀሳው በጣም ጥቂት ወጣቶችን አይጨምርም!

ጌታቸው ሽፈራው

Related stories   ባለቤቱ ያልታወቀው የኦሮሚያ በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም ለመወሰን የወጣ አዋጅ (ረቂቅ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *