ዶክተር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑበት ቀን ጀምሮ ካደረጉዋቸው ንግግሮች ሁሉ አደገኛውን ቀጣና የነኩት የዶላር እጥረትን አስመለክቶ ” መልሱ ስል የገባችኋል” በማለት ያስተላለፉት መልዕክት ነው። በተለይም አገር ጥርተው መናገራቸው ለዓመታት በዝምታ የታለፈ መሆኑ ጉዳዩን መነጋገሪያ አድርጎታል።


Image result for dubai bank

ከኢትዮጵያ በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ በህገወጥ መንገድ እንደሚጋዝ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ አገር ወዳዶችና የሃገር ውስጥ የመረጃ ምንጮች ይፋ ካደረጉት በላይ  የኢህአዴግ ደህንነት ጠንቅቆ ያውቀዋል። አነጋጋሪ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ማጋዙ ላይ ተዋናይ የሆኑት ክፍሎች የፖለቲካው ወሳኔ ሰጪ በመሆናቸው ሳቢያ ርምጃ መወሰድ አለምቻሉ ነበር።

ሹመቱን ከተቀበሉ ወዲህ ተሰሚነትና ተቀባይነታቸው ያየለው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ቀደም ሲል ከሚሰሩበት ተቋም ልምድ ብመነሳት የወጭ ምንዛሬ እጥረትን አስመልክቶ ሲናገሩ ጥርጥር አይታይባቸውም ነበር። ባለባቶችን ሰብሰበው ሲያናገሩ ” እንደ መንግስት ሳይሆነ እንደ አገር በውጭ ምንዛሬ ችግር ታመናል” አሉ። አያይዘውም ” መልሱ” አሉ።

” መልሱ ስል የገባችኋል አይደል” ሲሉ ተጨበጨበ። ቀጠሉና ኢትዮጵያ በዱባይና በቻይና የተከማቸ የውጭ ምንዛሬ እንዳላት አመለክቱ። እንደ ቻይና ያሉ አገራት ባለስልጣኖቻቸው የውጭ ምንዛሬ ሲያግዙ አቅማቸውን ተጠቅመው እንደሚያስመልሱ ገለጹ። አያይዘውም ” እኛ አቅማችን እዛ ላይ አልደረሰም። ነገር ግን እመኑኝ የቀን ጉዳይ ነው እዛ ደረጃ እንደርሳለን” አሉ። አሁንም ተጨበጨበ።

Image result for የቻይና ባንክ

“ከኢትዮጵያ ሆቴል ያለንን የዶላር ክምችትም እናውቃለን” ሲሉ የተናገሩት ዶክተር አብይ፣ ለምን እየታወቀ ዝም እንደተባለ ድብቅ አለመሆኑን ገልጸዋል። ” በዚህ አይቀጥልም” ሲሉም ዝርዝር ባይናገሩም የታሰበ ነገር እንዳለ አመላክተዋል።

ግሎባል ፋይናንሺያል ኢንተለጀንስ ብ2004 – 2013 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ26 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከአገሪቱ በህገወጥ መንገድ መውጣቱን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚሁ ስሌት መሰረት በዓመት ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የማሸሽ ተግባር እንደሚፈጸም ጥናቱ ይፋ አድርጎ ነበር።

በአገር ቤት የተለያዩ ድርጅቶችና ባለሃብቶች ለፕሮጀክት ብር እየተበደሩ ከጥቁር ገበያ ዶላር በመሰብሰብ ከአገር እንደሚያሸሹ የፌደራሉ የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በምርመራ ቢያረጋገጥም ምንም ዓይነት ርምጃ ሳይወሰድ መቆየቱ የሚታወስ ነው። መለስ ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥፋት ያቋቋሙት ይህ ተቋም፣ በመረጃና በማስረጃ ችግር ባይኖርበትም ከተቋቋመለት ዓላማ አንጻር አነስተኛ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ የተራ ጠባቂ ስራ ለመስራት መገደዱን በድርጅቱ ውስጥ ያሉ አገር ወዳዶች በጓሮ የሚናገሩት እውነት ነው።

Related stories   የ 305 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት- የጀሪካን ውሃ ዋጋ ወደ ሰባት ብር አሳደገ፤ ሰበቡ ኤሌክትሪክ ነው

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *