በዛሬው እለት መከላከያና  የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ቡድንን እየተጫወቱ ሳለ መከለከያ ወደ ግብ የላካት ኳስ መስመር አልፋለች በሚል ጎል አድርገው ያጸድቃሉ። ከዛ በሁዋላ ሁሉም ተጨዋቾች ዳኛውን ማባረር ይጀምራሉ። ዳኛው ነብሴን አውጪኝ ብለው ሜዳ ለሜዳ ይሮጣሉ።

ሜዳውን አልፈው ወጥተው የመሮጫው ቦታ ደርሰውም በሚችሉት ሁሉ ራሳቸውን ለመከላከል ሲፍጨረጨሩ የረዳቸው የጸጥታ ሃይል አልነበረም። ለምን? ለወትሮው ለዱላ ቅድሚያ የሚቆመው ፌደራል ቆሞ መተኛትን ለምን መረጠ? እንዲህ ያለውን አሳፋሪ ድርጊት የፈጸመ ቡድን ስንት ዓመት ነው የሚቀጣው? ሁሉም ተጫዋቾች በህገወጥ ድርጊቱ ተሳታፊ ነበሩ። መሪያቸውን ጨምሮ።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ታዲያ ፌዴሬሽኑ ሁሉንም ማገድ ወይስ ክለቡን መቅጣት ይቀለዋል።  የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ቡድንን ከእንግዲህ ወዲያ እንዲጫወት ከተፈቀደ ሌሎች ክለቦች፣ ዳኞች እና የሚመለክታቸው አካላት አቋም መያዝ ይገባቸዋል። በፊፋ ህግ መሰረት ቅጣቱ የከፋ ነው። ይህ ህግ ክለቡን ያግዳል። ያጠፉትን ተጫዋቾች በሙሉ ያግዳል። የገንዘብ ቅጣጥ ይጥላል። ሌላም ሌላም።

ክለቡ በፍጥነት ደብዳቤ አሰራጭቷል። ጥፋት መሆኑንንም ጠቁሞ “…ዳኛ በመክበባቸው ይቅርታ….” ሲል አይን ያወጣ ቅጥፈትን በደብዳቤው አስፍሯል። ዳኛውን አባረው፣ ዘርረው  ሲቀጠቅጡ ፊልም አለ፤ እንዲህ ያለ የአደባባይ ክህደት ፌዴሬሽኑንን እንደ መናቅና ድርጊቱን ደጋፊ ሆኖ የመቅረብ ያህል ቅጣቱ ሊጠነክር ይገባል

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *