“Our true nationality is mankind.”H.G.

ከ2 አመት በላይየተደበቀ የሰበአዊ መብትጥሰት ፣ በትግራይ ህቡእ እሱር ቤት !!


ከአስገደ ገብረስላሴ

ይህ  አርእስት  ሳስቀምጥ  ዝምብዬ ያለአንዳች  መረጃ አይደለም ይህም ከ 2  አመት በፊት  አንድ ማንነቱና ስሙ   የማይታወቅ በዲያስፓራ የሚኖር  የሚኖርበት አድራሻ  የማይታወቅ ትወልደ ኢትዮጱያ ዜግነት  የአመሪካ ይሁን የአውሮፓ ፣የአውስትራሊያ ፣የከናዳ ወ ዘ ተ መሆኑ የማይታወቅ ፣ ግንደግሞ ከአባይወልዱ እና ከትግራይ ፓሊስ ኮምሽን ፣ ከማረምያ ቤት የሚያሸልኩ መረጃዎች ግን ሰውዬው አመሪካዊ ዘግነት ያለው መሆኑ ይነገራል ።  በትግራይ ክልልል የተወለደ ሲሆን የተወለደበት አውራጃ፣ ወረዳ ፣ ቀበሌ ግን አይታወቀም በወቅቱ ለማወቅ አልተቻለም  ።አሁንም አይታወቅም    ። መዋቅሮችእና አባይ ወለዱ ራሳቸው፣ፖሊስ ኮምሽን ፣ ጠቅላይ ፍርድቤት፣ አቃቢ ሀግ ፣ በህቡ ያቆምለት ጠበቃ ግን የዲያስፖራው አድራሻ ያውቁታል ። ለሀዝብና ለጸሀፊዎች ፣ለቤተሰቦቹ ግን ድብቅ ነው ።

ይህ ወገን ወደ ሀገሩ ኢትዮጱያ በተለይ በትግራይ ክልል  የመጣበት ምክንያት  የኢንቨስትመንት ጥናት  አድርጎ  ገንዘቡና ሙያው አፍስሶ ለመስራት ፈልጎ  ለበርከት ያሉ አመታት  እየተመላለሰ በመዛገጃ ቤቶች ፣በኢንቨስትመንት ቢሮ ፣በእንድስትሪ ቢሮ አመልከቶ  እዬተመላለሰ  ፍትህ አጥቶ ብዙ ደክሞ ተስፋ ሳይቆርጥ  የመጨረሻ  እድሉን  ለሞሞከር ወደ ክሉሉ ርእሰ መስተዳደር  መንግስትት  ክልል ትግራይ  አባይ ወልዱ   ለአንድ አመት ያህል በቀጠሮ ቀጠሮ ተመላልሶ  የአባይ ወልዱ ቢሮም እንደመዋቅራቸው  ቢራቸው ተንኳኩቶ   የማይሰማ   መዝግያ  እንደሆነበትና እንዳማረረ  በአባይ ወልዱ ቢሮ የሚሰሩ እና  በአባይ ቢሮ  አካባቢው የሚገኙ  የመንግስት ሰራተኞች ምንጮች  አበጥረው ያውቃሉ ቀስበቀስም ለመቀለ ህዝብ ያሳራጩ ነበር  ።

የዲያስፖራው ሰውዬ ወደ  የክልሉ መዋቅሮች ቢሮ እስከ  አባይ ወልዱ  የፍህና  የመልካም  አስተዳደር   እጦት በፈጠሩበት  ውጣ  ወረድ  አልፎ  ብዙ  ጊዜ ከለፋ በኃላ  በመጨረሻዋ ቀን ነው ከአባይ ወልዱ  ጋር እንዲያ አነጋግሩት ቀጥረውት  በቀጠረው መሰረት  ወደ አባይወልዱ ቢሮ ገብቶ  ፣ ቢሮአቸው ሲገባ በጭቅጭቅ  ቤቱ እንደተናወጠ ከቢራቸው የፈለቁ መረጃዎች  ይሰሙ ነበር ።  ጭቅጭቁ  አቋርጦ  ዲያስፓራና አባይወልዱ በቦግስና  በቢሮው ውስጥ  በሚገኙ ቁሳቁሶች ተደባደቡ ። ዝርዝር መረጃ በይኖሮኝም  በጊዜው  በፌስቡክ ጠቁሜ ነበር ። በወቅቱ ግን አንድም በዲያስፓራና  ባገር ወስጥ የሚኖሩ ወገኖች  ህዝብ  ሆነ ምዲያዎች ይህ ሰውዬ ፍትህ እንዲያገኝ  ተጽእናኖ ከማድረግ ተቆጥበዋል ።

ዲያስፓሯውና አበይ ወልዱ ሲደባደቡ ሰምተው የአባይ ወልዱ  ልዩ ጥብልል ኩማንዶዎች ተንደርድረው ወደ ቢሮው ገብተው በያዙት ቁሳቁስ  ለዲያስፖራው  ደበደቡት ዲያስፓራ በቢሮው ወለል  ውስጥ  ደሙን እያፈሰሰ ተዘርሮ  ወድቆ እንደነበረ  በከተማው ተሰራጩ ።
። ለአባይ ወልዱ ኩማንዶዎች እርዳታ የክልሉ ልዩ ሀይል ኩማንዶዎች እና የትግራይ ክልል ፓሊስ ከምሽን  ኩማነዶሮች  ፣ ዋናው ኮምሽነሩ  ዘአማኒኤል ለገሰ ወደ አባይ ወልዱ ቢሮው ገብተው እንደገና ተቀጥቅጦ  ቢሮው ወለል ደም በደም ሆኖ ተዘርሮ  ላለው   ዲያስፖራ እንደገና ልዩ ሀይሎች  እንደ ቀጠቀጡትና አእምሮው ስቶ  ወድቆ ሞተዋል ብለው እንደደበቁት ከአባይ ወልዱና ከሰራተኛው መረጃው ሸልኮ  በመቀለ ከተማ በመጠጥ ቤት ፣በካፌ  በቢሮዎች  በዲያስፓራው የደረሰ ኢሰብአዊ ድርጊት አጀንዳ ሆነ ።

በወቅቱ አባይ ወልዱና  የጸጥታ ሀይሎች ፣የፓሊስ ከመሽን ሰውዬው ሞተዋል ብለው በማመናቸው  በአባይ ወልዱ በክልሉ  ቢሮ ውስጥ  በሞቶዎች  የሚቆጠሩ  ሰራተኞች ሚስጢር እንዳያውቁ  ያለሰአታቸው ስራ አቋርጠው በአባይ ወልዱ ቀጭን ትእዛዝ  ወርዶላቸው   ከቢራቸው እንደወጡ የቢሮው ሰራተኞች አሰራጩት ።
የአባይወልዱ ቢሮ ሰራተኞች ስራ አቋርጠው ከወጡ በኃላ ዲያሰቦራው በልዩ ሀይልና የትግራይ ክልል ፓሊስ ኮሽነር ዘአማኒኤል ለገሰ ፣ የመቀሌ ከተማ ኩማንደር ገብሪሂወት ፣የድህንነት መሪዎች ያሞቶ የተባለ ወገን  በሽፍን መኪና  ጭነው ዜጎች በህቡእ ወደ  እሚታሰሩበት ህቡእ እሱር ቤት (06) እየተባለ የሚጠራ በበረሀ የህወሓት እሱር ቤት  የነበረ ስም የተሰጠው )  ወደ ባሎኒ እንዳየሱስ ተራራ  ዩንቨርሲቲ ግርጌ ወደ እሚገኜው ድብቅ እሱር ቤት   ወሰዱት ሰውው ግን መታሰሩ ህዝብ ወስጥ ለውስጥ በማወቁ ፣መረጃው በፌስ ቡክ ስላአሰራጨው  ፣የፈጸሙት ኢፍትሀዊ  ድርጊት መጋለጡ አይቀርም በሚል ሰግተው በሀቡህ የፓሊስ ሀኪም አክሞት ስትንፋስ  ከዘራ በኃላ ለአንድ አመት ያህል ሳይከሰስ በዛ እቡእ  እሱር ቤት  ለብቻው በዝግ ጨለማ  ቤት ሰውና ጸሀይ ሳያይ ፣አካላቱ ተዳክሞ ይኖር ነበር ። ስለዚህ ሰውዬው ኢሰብአዊ ድርጊ የተወሰን ሰወች ያገኜነው  መረጃ በፌስቡክ አናሳራጭ የኖርን ስንሆን  ።የአገር  ውስጥና  የውጭ ሚዲያዎች የተወሰነ መረጃ ሰምተው ዝም ከማለት ውጭ ያደረጉት ነገር የለም ።

አሁን ዲያስፓራው የት አለ  በምን ደረጃስ  አለ???
————————————————————
ዳያስፖራው በህቡእ እሱር ቤት ከአንድ አመት በኃላ  የዲያስፖራው  በግፍ  መታሰር ቡዙ ህዝብ ስላወቀው ውሎ አድሮ መታወቁ ስለማይቀር ብለው ታሳቢ በማድረግ   ሰውዬው በህቡእ የጠቅላይ ፍርድቤት በአንድ ዳኛ ፣አንድ አቃቢ ህግ ከሻሽ ወንጀል መፈጸሙ አባይወልዱና የደበደቡት ኮማንደዎች ፣የአባይ ወልዱ  ጸሀፊ  ምስክሮች በማድረግ  ክስ ተመሰረተበት ።ተከሳሹ ችሎት ቀርቦ  የክህደት እምነት  ቃል ሲጠየቅ ፣እምነት ክህደት ከመስጠቴ በፊት ተከላካይ ጠበቃ ይደረግልኝ ብሎ በመጠየቁ  በባለስልጣኖች  ሚስጢር የማያባክን ጠበቃ ታማኝ መቀለ ከሚገኙ  በሞቶዎች  የሚቆጠሩ ጠበቆች  አንድ ተከላካይ ጠበቃ ተመለመለ ባስቀመጡት መመልመያ ነጥብ  አንድ ተከላካይ ጠበቃ አቶ ተሰፋይ  ገብረስላሴ አድራሻ መቀለ ቀበሌ ዘጠኝ ተክለሀይማኖት ቤተክርስቲያን አካባቢ ጽፈት ቤቱ የሆነ  የስልክ ቁጥር  0914704196  በህቡእ ችሎት ከተከራከረ በኃላም ፣ዲያስፖራው ከህቡኡ እሱር ቤት ( 06 ) ወደ  መቀለ ግዙፉ ማረምያ ቤት አዘወሩት ።

ዲያስፖራው  የውስጥ አዋቂ ምንጮች  እንደሚናገሩት  በማረምያ ቤቱ  ለብቻው ሌላ እስሮኞ እንደማያዩት በአንድ ቤት ተዘግቶ ፣ ምግብ የሚያቀርብለት ፣ሽንት የሚያሸኛውም አንድ ታማኝ የሚባል ወታደር ብቻ ነው ።ሌሎች  ጠባቂዎች እዲያዩት አይፈቀድም ። ተካላካይ ጠበቃ ሊያማክረው ወደ ተዘጋበት እሱር ቤትም ለስሙ ነው ጥብቅናው የተሰጠው እንጅ ብቻው ሆኖ ከእስረኛው  (ደንበኛው ) መረጃ እንዲወስድ ፈልጎ ስሄድ ታማኝ  ጠባቂ  ፓሊስ እንደሚጠብቀው ምንጮች ጠቁመዋል ።

ይህ ጠበቃ መጀመሪያ ሲመለመለ ሚስጢር እንዳያበክን ፣ካባከነ ደግሞ  ራሱ የሚያዝ መሆኑ ማስጠንቀቅያ እንደተሰጠውም ይነ ገራል ።

ዲያስፖራው ከቡዙ ክርክር በኃላ  በትግራይ ጠቅላይ ፍርድቤት ጥፋተኛ ተብሎ የመጨረሻ ከባድ ውሳኔ እንደተወሰነበት እና የተግራይ ሰበር ችሎትም  የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ውሳኔ ይጸናል እንዳለው ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ ። ድያስፖሯው ወደ ፈደራል ሰበር ችሎት ይግባይ ብሎም  መልስ አጥቶ  ለረጅም ጊዜ  በዝግ  እሱር ቤትቱ  እንደቆዬ  ይነገራል ።

ትንሽ ቆየት ብሎ በትግራይ ክልል ጠቅላይ  ፍርድ ቤት    ወደ ፈደራል ጠ/ ፍርድቤትና የፈደራል   ሰበር ፍርድ  በውክልና የሚመለከተው   ስልጣን ስለተሰጠ   ። በተጨማሪ ለዚሁ የፈደራል ጉዳይ በሚመለከት በክልሉ የፈደራል ፓሊስ ምርመራና  የፈደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ቅርንጫፍ በመቋቋሙ   ። እነዚህ ተቋማት ለክልሉ አቃቤ ህግና ፖሊስ ምርመራ  ፈደራል ጉዳይ የሚመለከቱ የገበን (የወንጀል ) ክሶች  ለኛ ስለሚመለከት  አስረክቡን ስላሉዋቸው ፣ሁሉም ለፈደራል አቃቢ ህግና የፈደራል ፓሊስ ምርመራ የሚመለከቱ ሰነዶች  እንዳስረከቡዋቸው ምንጮች ይጠቁማሉ ።
የዲያስቦሯው የክስ ሰነድም  ለፈደራል አቃቢ ህግና ለፈደራል ሰበር ችሎች እንደተላለፈም   ታማኝ ምኝጮች ይጠቁማሉ ። ይህን ከላይ በትግራይ ክልል የተፈጸመ አፈና  ዘርፈ ቡዙ   የፍት ጥሰት መረጃ  ተከትለው የሚመለከታቸው ወገኖች ፍንጩን ተገንዝቦው ለሚመለከታቸው አካላት ቢጠይቁ የተሻለ ነው ።

እኔ   በዲያስቦራው የደረሰ  የሰብአዊ መብት ጥሰት ስገልጽ በክልላችን ሌላ ሰብአዊ መብት ጥሰት የለም ማለቴ አይደለም ።በክልላችን እንደሱ ያሉ እና ከሱ የባሱ ሰቆቋዎች እንዳሉና 27 አመት መሉ ጭሆናል ። የህወሓት መሪዎች  ግን ከመጤፍ እንኳን የሰብአዊ መብት ጥሰት አለ ብለው ትንፍሽ ብለው አያውቁም ።  ዘንድሮ ግን በዝብ ብሶት ተጽእኖ ባለፉት 27 አመታት የፈጸሙት ኢሰብአዊ ድርጊትና የዜጎች የሰብአዊ መብቶች ጎድተናል ብለው እንደባለ ዛር በህዝብ ሀይል ተጽኖ የተወሰነ ትንፍሽ ብለዋል ። ሆኖሞ ግን አሁንም በዚሁ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሰት አተቋረጠም ።

ሌላ የዚህ ዲያስቦሯ  የደረሰበት ግፍና የመብት ጥሰት  ወንጀል አልፈጸመም በሚል አይደለም ፍትህ ብቻ ማግኜት አለበት ማለቴም  አይደለም ።
ይህ ወገን በህግ መሰረት ይቅርና ለክልል አስተዳዳሪ ቢሮ  መድፈር  ይቅር የሆነ ዝቅተኛ ቢሮ መድፈርም  ሊያስቀጣው  ይችላል  ። በመሆኑም  እኔ  ለትግራይ ክልል  እምቃወማቸው  በጭፍን አይደለም ። በፈጸመው ወንጀል ሰብአዊ መብቱ ሳይነካ   በፍርድ ቤት መቀጣት  ነበረበት። የመንግስት ቢሮ መድፈሩ  አንድ ገበና ሆኖ እነ አባይወልዱ  ሂወትን እስከማጥፋት የሚዘልል  እርምጃና ኢሰብአዊ ድብደባ ከማድረግ በትእግስት ይዘው በሀገራችን ስነስርአት ህግ ለማስቀጣት ይችሉ ነበር ። ነገር ግን ለሞት የሚዳርግ እርምጃ መውሰድ አልነበራቸውም ።

ግን ማሰብ የነበራቸው ይህ ሰውዬው ወደዚህ የሂወት መስዋእት የሚጠይቅ እርምጃ ለመውሰድ ለምን ተገደደ ብለው መሰላሰል ነበረባቸው ። በእኔ እምነት ይህ ዲያስፖራ በስደት ደክሞና ጥሮ የሰበሰበው ገንዘብ ወደ ትውልድ ቃያው መጥቶ ኢንቨስመነት  አድርጎ ሊኖር አሰቦ በህወሓት ቢሮክራሲ የመልካም አስተዳደርና ፍትህ እጦት በጊዜ መጓተት ምክንያት ሰርቶ ደክሞ ያመጣው ሀብት  በምልልስ በአዬር ትራንስፖርት ፣በሆቴል ከዛም ጉቦ ተጨሙሮበት ።የቀጠሮ መንዘዛት ብዛት ዲያስፖራ ከነበረበት አገር የማይጠጋ የተባላሸ አሰራር ስላጋጠው  ነው ወደወንጀሉ የገባው ።ስለ ሆነ ወንጀሎኞቹ አባይወልዱ እና መዋቅራቸው ናቸው። በመሀኑም ዲያስፖራው በቢሮክራስ የተጨማለቀ አሰራር  ተገፋፍቶ የወሰደው እርምጃ በመሆኑ አምነው በኩማንዶ ከማስደብደብ ፣በጨለማ ቤት የግፍና የስነልቦና  አሰቃቂ ፍጻሜያቸው በማመን  ይቅርታ ብለውት ቢሆን ንሮ ለሁሉም ይበጅ ነበር  ።የህወሓት መሪዎች ኢሰብአዊ    ተግባራቹ መቋጫ ብታደርጉበት ለናንተም  ለህዝባችንም ፣ለሀገራችንም ይበጃል!!
ከአስገደ ገብረስላሴ
መቀለ
23  / 08 /2010

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0