የሕወሓቱ ነውረኛ ድርጅት ብአዴን ላለፉት 27 አመታት አማራ ባገሩ ስደተኛ ሆኖ ሲፈናቀልና ሲገደል ለይምሰል እንኳ መግለጫ አውጥቶ አያውቅም። ነውረኞቹ ብአዴዎች ውክልናቸው የትግራይ እንጂ የአማራ ስላልሆነ የአማራ ጉዳይ አይመለከታቸውም።

ባለፈው ጥር ወር ላይ ግን በወልድያ፣ በቆቦና በመርሳ የትግራይ ነፍሰ በላ ወታደሮች አማራ ሲጨፈጭፉና አማራ ራሱን የመከላከያ ርምጃ ሲወስድ ሁሉም የብአዴን ድርጅታዊ መዋቅሮች መግለጫ አወጡ። የብአዴን ቃል አቀባዩ Nigussu Tilahun፣ እንደራሴው ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተብዮው፣ የነውረኛው ብአዴን ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮምቴ አባላት በሙሉ የትግራይ ተወላጆች ተጠቁ ብለው የተጨፈጨፈውን አማራ የሚያወግዝ መግለጫ በሬዲዮ፣ በጋዜጣና በቴሌቭዥን አስተላለፉ።

No automatic alt text available.

አማራ ሲፈናቀልና ሲሰደድ፣ ሲገደልና ሜዳ ላይ ሲጣል ግን ባለፈው ጥር ወር ለገዳይ የትግራይ ወታደሮች አዝነው መግለጫ ያዥጎደጎዱት እነ ንጉሱ ጥላሁን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተብዮው፣ የነውረኛው ብአዴን ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮምቴ ትንፋሻቸው የለም። እንዴውም በተቃራኒው በክህደት ተሰማርተው ከጎጃም መተከል የተፈናቀሉትን አማሮች የመለስ ዜናዊን አገላለጽ በመጠቀም «ሕገ ሰፋሪዎች» በማድረግ እየወነጀሏቸው ነው።

No automatic alt text available.

ከታች የታተሙት ፎቶዎች «ሕገ ወጦች» ተብለው የተፈናቀሉት አማሮች፣ ግብር የከፈሉበት ደረሰኝና የተፈናቀሉበት ምድር «የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ» ደብተሮች ናቸው። እነዚህ የይዞታ ደብተሮችና ግብር የከፈሉበት ደረሰኞች አገርና መንግሥት አልባ ሆነው ባህር ዳር አባይ ማዶ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ እንኳ እንዳይጠለሉ እየተሳደዱ የሚገኙ ተባራሪ አርሷደሮች የተባረሩበት መሬት «የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ» ደብተሮችና ሕጋዊ ኗሪዎች ስለመሆናቸው ግብር የከፈሉበባቸው ደረሰኞቻቸው ናቸው። ይህ በግልጽ የሚያሳየው አባወራዎቹ የተባረሩት አማራ ብቻ በመሆናቸው ብቻ እንደሆነ ነው።

የስዕል ማስረጃዎቹን በሙሉ ከስር ባለው የጌታቸው ሽፈራው ፌስ ቡክ ገጽ ይመልከቱ

Getachew Shiferaw.
Related stories   የምክትል ' ኤታ ማጆር ' ሹመት የህግ ጥያቄ ቀረበበት፤ የሹመኞቹ ሃላፊነት አይታወቅም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *