ባንዲት 80እሥረኞች በሚገኙባት ዛኒጋባ 81ኛው እሥረኛ ሆነው  ከገቡ በኋላ ለበርካታ በሽታዎች ተዳረጉ።ይሄ ቢታወቅም በጊዜው አሥፈላጊውን ህክምና በመነፈጋቸው በሽታው ሥር እየሰደደ ሄዶ አሥጊ ደረጃ ላይ ሲደርስ ሆስፒታል ገብተው ተስፋ በሌለው ሕክምና ቆይተው፣ነገ ዛሬ ህይወታቸው ያልፋል በሚል ሥጋት ላይ እንዳለን  ለተሻለ ህክምና ወደውጭ አገር  ሄዱ።አሁንም ተስፋ በማይሰጥ ሕክምና ቆይተው አረፉ።


ግንቦት 6ቀን  2010ዓ.ም.
አያሌው ፈንቴ

ሰማዕቱ ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ወልደዬስ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት(የመዐሕድ)ፕሬዝዳንት የዛሬ 19ዓመት ግንቦት 6ቀን 1991ዓም(እ አ አ ሜይ 14ቀን 1999ዓም) ፊላደልፊያ አሜሪካ አገር በፔንሲልቫንያ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ከዚህ ዓለም እንደተለዩ ይታወቃል።በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣በተለይ ደግሞ የአማራው ሕዝብ ይህን ዕለት አስቦት የሚውለው በታላቅ ሀዘንና ቁጭት ነው።

ክቡርነታቸው! የአማራን ሕዝብ የመኖር ዋስትና ተግባራዊ ለማድረግ ከመጣራቸውም ሌላ ለኢትዮጵያ ሀገራዊና ሕዝባዊ አንድነት እንዲሁም እኩልነትና ዲሞክራሲያዊ ሕይወት ግኝት የከፈሉት አቻ የለሽ መሥዋዕትነት፣በታሪክ ዓምድ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ከመያዙም ባሻገር፣ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የሚኖር ነው።

ፕሮፌሰር! የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር(ትነግ)የሚባለው የትግሬ ዘረኞች ሥብስብ፣በ1983ዓም ከዕድምተኞቹ ጋር በመሆን ያካሄደውን የኢትዮጵያን ሀገራዊና ሕዝባዊ አንድነት የመናድ ተግባር፣የኮንፈረንሱን ምንነትና ተልዕኮ በጀግንነት በመዋጋት ድምፃቸውን አጉልተው ያሠሙ ብቸኛው ጀግና ነበሩ።ይህ ከትግሬ ዘረኞች ሥልጣን መያዝ ጋር ተያይዞ የመጣው የጎሳ ፖለቲካ ገና ከመነሻው ችግር ሊያሥከትል እንደሚችል በግልፅ ከመናገር አንሥቶ የመከራ እሳቱም ሲቀጣጠል ያንን ለማጥፋት በቀዳሚነት የተሰለፉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ። ።

በ1984ዓም በዐማራው ላይ በወልቃይትና በራያ ከሚደርሰው ግፍ በተጨማሪ በአርባጉጉ፣በበደኖ፣በአረካ፣በአሰቦት ገዳም፣በአሩሲ ነገሌና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ህይወቱ እያለ ዓይኑ ሲጎለጎል፣ሕይወቱ እያለ ቆዳው ሲገፈፍ፣ሕይወቱ እያለ ሥጋውን ቆርጠው “ብላው እያሉ” ሲያሰቃዩት፣ሕይወቱ እያለ ቤት ዘግተው ሲያቃጥሉት፣ሕይወቱ እያለ ወደገደል ሲወረውሩት፣ሕፃናት ከእነቤተሰቦቻቸው ሲታረዱ፣የዕርጉዞች ሆድ ሲቀደድና ሽሉ ሲጣል፣ የዐማራው ልጃገረዶች ሲደፈሩ፣ሲዋረዱና ተማርከው በባርነት ሲያገለግሉ፣አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉና ሌሎችም ተዘርዝረው የማያልቁ የዘር ማጥፋት ሰቆቃዎች ሲፈፀሙበት፣ፕሮፌሰር አሥራት አይተው እንዳላዩ፣ሰምተው እንዳልሰሙ ሆነው ማለፍ አልቻሉም።

በዚህን ጊዜ ዐማራው አለሁ ባይ ተቆርቋሪ የሌለው መሆኑን ተገንዝበው፣አጋር ሊሆኗቸው ከሚችሉ ወገኖች ጋር ዐማራውን ከጨርሶ ጥፋት ለማዳን በሚቻልበት ጉዳይ መክረው መዐሕድን በ1984ዓ.ም በመመሥርት፣ቀን ጨልሞበት አለሁ ባይ ወገን አጥቶ በደም ተጨማልቆ የሚቃትተውን ዐማራ የሚያሥጥልህ ሕግና ሥርዓትየለም፣ሞት ወይም ሕይወት ብለህ ራሥህን አዘጋጅተህ ባላጋራህን ተቋቁመህ ባለህ ኃይል ተከላከል” በማለት በሥነ ልቦና ለመገንባት ጣሩ።

profesor Asrat

ፕሮፌሰር! በንቃት የመጠቁ ሥለነበሩ ለአማርኛ ቋንቋ አክብሮት ነበራቸው፣በመሆኑም በንግግራቸው ውስጥ እንግሊዝኛ ደባልቀው መናገር አይወዱም ነበር።ሥለሆነም ለተማረውም ላልተማረውም፣ለትንሹም ለትልቁም የሚናገሩትም ሆነ የሚያሥተላልፉት መልዕክት በቀላሉ ይገባል፣ይደርሳልም።

ፕሮፌሰርም “ በአራት እግሩ በመሄድ ላይ የነበረው ዐማራ አንገቱን ቀና አድርጎ በሁለት እግሩ መሄድ ጀመረ” ማለታቸውን አንዘነጋውም።ይህም የመጀመሪያው የፕሮፌሰር አሥራት ቆራጥ አመራር የሕይወት ፍሬ  ውጤት ነበር።በዚህን ጊዜ የትግሬ ዘረኞች  የፕሮፊሰር እንቅስቃሴ ሥላስደነገጣቸው እግር በእግር ክትትሉን ተያያዙት።

ፕሮፌሰር አሥራት! ዙሪያ ገባውን በጠላት ተከብበው  ሲዋከቡ፣ ችግርና ፈተና ሳይበግራቸው፣ከፊት ለፊታቸው የተጋረጠውን ግዙፍ ኃይልና አደጋ ከምንም ሳይቆጥሩ፣በዚህ በቀውጢ ሰዓት ከማንም ቀድመው በአማራው ላይ የሞት፣የመታሰርና የመሰደድ አደጋ  ማጥላቱን ተገንዝበው፣የአገር ግንጠላም ወደፊት የሚያስከትለውን ችግር አሻግረው አይተው ሀቁን በመናገር ለአገርና ለሕዝብ ዘላቂ ሰላም፣ለፍትሕና እኩልነት ያለማወላወል በቁርጠኝነት በመቆም ሳይቃጠል በቅጠል በማለት እምቢ ለሀገሬ፣እምቢ ለወገኔ፣እምቢ ለዳር ደንበሬ፣ብለው በታላቅ ቆራጥነት መታገላቸው አርአያነቱ ምንጊዜም የማይረሳ ነው።  

በአማራው ህልውና፣በኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት፣በህዝቡ የጋራ ዕድልና ተስፋ ላይ ዘወትር በማሴር ላይ ያለው ፀረ-አማራው የትግሬው ቡድን፣ ፕሮፌሰር አሥራትን  ከጎጃም ከመጡ ገበሬዎች ጋር በመዐሕድ ጽህፈት ቤት በመሰብሰብ የአድማ ወንጀል ፈፅመሀል” በሚል የሀሰት ክስ መሥርቶ 2ዓመት ፈረደባቸው፣ “ደብረ ብርሃን ላይ ሕዝብ የሚቀሰቅስ ንግግር አድርገሃል በሚል አንድ ሌላ ክስ መሥርቶ 3ዓመት ፈረደባቸውየጎጃም፣የጎንደርንና የሰሜን ሸዋን ሕዝብ ለአመፅ አዘጋጅተሃል”በሚልም ወንጅሎ፣ ባንዲት 80እሥረኞች በሚገኙባት ዛኒጋባ 81ኛው እሥረኛ ሆነው  ከገቡ በኋላ ለበርካታ በሽታዎች ተዳረጉ።ይሄ ቢታወቅም በጊዜው አሥፈላጊውን ህክምና በመነፈጋቸው በሽታው ሥር እየሰደደ ሄዶ አሥጊ ደረጃ ላይ ሲደርስ ሆስፒታል ገብተው ተስፋ በሌለው ሕክምና ቆይተው፣ነገ ዛሬ ህይወታቸው ያልፋል በሚል ሥጋት ላይ እንዳለን  ለተሻለ ህክምና ወደውጭ አገር  ሄዱ።አሁንም ተስፋ በማይሰጥ ሕክምና ቆይተው አረፉ።

ዘረኞቹ ትግሬዎች!  ፕሮፌሰር አሥራትን በፈጠራ ወንጀል አሥረው  አምስት ዓመት አንገላተውና አሠቃይተው በቁመና ከገደሏቸው በኋላ በማምጠጫ ዕድሜያቸው ወቅት ለይስሙላ ህክምና ወደውጭ አገር ማስወጣታቸው በዘረኞቹ ላይ የሚመጣውን ተቃውሞ ለማርገብ የሚረዳቸውና የፖለቲካ ትርፍ የሚያሥገኝላቸው መሥሏቸው ይሆናል ግን አይደለም። ይህ ድርጊት የሚያሳዬው ዘረኞቹ፣በአማራው ሕዝብ ላይ ያላቸውን መረን የለቀቀ ጥላቻና ፋሽስታዊ ተልዕኮ በመሆኑ፣ቁጣችን አይሎ፣ጥርስ እንድንነክስ ተገደናል።

በማይቀረው የሠው ልጅ መጨረሻ በሆነው ሞት በአካል ከእኛ የተለዩን ፕሮፌሰር አሥራት፣ጉልበታቸውን፣ዕውቀታቸውን፣ገንዘባቸውንና ዕምነታቸውን፣ብሎም ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡት፣በቅድሚያ የአማራው ዘር ከምድረገፅ እንዳይጠፋ በመከላከል ህልውናውን ተግባራዊ ለማድረግ፣ቀጥሎም ለአገርና ለሕዝብ አንድነት ሲሉ ነበር።በመሆኑም ዘረኛውን የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባርን በልበሙሉነትና በጀግንነት ሲታገሉ አልፈዋል።

አሪስቶትልሥለጀግንነት ሲናገር “ለታላቅነት ተግባር ራሱን ያዋለ ሠው፣የሠብዓዊ ክብር ዓርማ ነው ብሎ ነበር።

ጀግኖች ግብና ዓላማ ቀርፀው የሚራመዱ በመሆናቸው ድፍረት፣ልበሙሉነትና አይበገሬነት መለያቸው ሥለሆነ ታላቅነት ከውስጣዊ ጀግንነት ሥሜታቸው ሥለሚመነጭ ምንጊዜም ከትግሉ ግንባር በቅድሚያ የሚቆሙ የትግል ፋና ወጊዎችና ገድል ፈፃሚዎች ናቸው።መከራና ፈተና አይበግራቸውም።ድሎት አያታልላቸውም።ለህዝብ ኖረው፣ሥለሕዝብ ታግለው፥ለሕዝብ ሲሉ ሕይወታቸውን ሠጥተው ያልፋሉ።

በየዘመናቱ ያለፉ መሪዎችንና የሀይማኖት አባቶችን፣ለምሳሌ የእነአቡነ ጴጥሮስንና የእነአፄ ቴዎድሮስን ተጋድሎ ሥናጤን፣የጠላትን ቅሥም ሰብረው የኢትዮጵያዊንትን የጀግንነት ገድል አሥመዝግበው ማለፋቸውን እናስታውሳለን። አፄ ቴዎድሮስ!ለጠላት እጄን አልሰጥም ብለው በጀግንነት እንደተሰው ለማንኛችንም ገሀድ ነው።ፕሮፌሰር አሥራት! የእነዚህ ትውልዶች አደራ ተረካቢ በመሆን ለህይወታቸው ሳይሳሱ ጠላትን ፊት ለፊት ተጋፍጠው አልፈዋል።

ኢትዮጵያ በሽዎች ለሚቆጠሩ ዘመናት የነፃነት ባለቤት ሆና የኖረችበት የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋናውና አንዱ ኢትዮጵያ የጀግኖች መሀን አለመሆኗና ጀግኖች ልጆቿ በተለያየ ቦታና ጊዜ በከፈሉት መሥዋዕትነት እንደነበር ታሪክ ይመሠክራል።የክቡር ፕሮፌሰር አሥራት የመስዋዕትነት ትግል ለዚህ በቂ መረጃ ነው።

ሥለሆነም ለአማራው ህልውና፣ለሀገር ሉዐላዊነትና ለህዝብ አንድነት ቀናኢ የሆነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ታሪክና ትውልድ የማይረሳው ተግባር ፈፅመው ያለፉት ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ፣ከዚህ ዓለም የተለዩበትን 19ኛ ዓመት አሥመልክቶ በታላቅ ሀዘንና ቁጭት አሥቦት እንዲውል እያስታወስን፣ይህን ዕለት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋና ድል ጋር አያይዞ የሚከበርበት ወቅት አሁን ባለው የጊዜና የሁኔታ ውስብስብነት ቢዘገይም አይቀሬ መሆኑን ሳናሰምርበት አናልፍም።

አሥራት የዘመናችን ታላቅ ሠው፣የፅናትና የልበሙሉነት፣የሀቀኝነትና የብልህነት፣የአርቆ አስተዋይነትና ሚዛናዊነት ተምሳሌት በመሆን በእያንዳንዱ አማራ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ልብ በህያውነት የሚታወሱ ናቸው።

ዛሬ ፕሮፌሰር አሥራት ቢያልፉም፣ዓርማውን አንግበው፣በአይበገሬነት ሞትን እየሞቱ  የሚታገሉ እንደ እንጉዳይ የፈሉናእሳት የላሱ ሚሊዮን አሥራቶች መፈጠራቸው ሊያኮራን ይገባል።

የሚሊዮን አሥራቶች መፈጠር ቢያስደስተንም፣እሥካሁን ድረስ በአገር ውስጥ ወሳኙን ተግባር ለመፈፀም፣ለአማራው ሕዝብ መከታና ጠበቃ የሚሆን አንድም የህቡዕ ድርጅት እና በዚህም ህቡዕ ድርጅት የሚመራ የታጠቀ ኃይልባለመኖሩ፣በገሀድም ሆነ በድብቅ የትግሬ ዘረኞች በአማራው ላይ የሚያደርጉት የዘር ማጥፋት ተግባር መረን ለቆ፣ የአማራውን የሥቃይ ዘመን እንዲራዘም ማድረጉን ሥናጤን ያሳስበናል።እንወቅበት እላለሁ።

በዚህ አጋጣሚ ላሥታውስ የምፈልገው  እነክቡር ፕሮፌሰር አሥራት መዐሕድን  ያቋቋሙት እዚያው እሳቱ ካለበት አገር ውስጥና ሕዝቡ መሀል በመሆኑ፣ወሳኝ ሚና እንደነበረው ይታወቃል።መሆንም የነበረበት ይኸው ነው። እኛም በውጭ ሀገራት የምንኖር አማራዎች፣በየምንኖርባቸው ሀገራት የመዐሕድ የድጋፍ ኮሚቴዎች  አቋቁመን፣አገር ቤት የተቋቋመውን  የእነፕሮፌሰር አሥራትን መዐሕድ፣በገንዘብና በሎቢ ድጋፍ  እንረዳ ነበር።የምንታዘዘውም ሌሎች ጉዳዮች ሲኖሩ ትብብራችንን እናሳይ ነበር።

ዛሬም ውጭ አገር ከምንኖረው የሚጠበቀው ይኸው ነውና እንወቅበት እላለሁ። መዐሕድ ጥሩ መሪም ሥላጋጠመው  በአጭር ጊዜ ውሥጥ የሕዝብ ድጋፍ አገኘ፣በወቅቱ ያራመደው የሰላም ትግል ብቻ በመሆኑ ተጠቂ ሆነ።

መዐሕድ  እንደነበረው የሕዝብ ድጋፍ፣ሁኔታው ሥላልፈቀደለት መሣሪያ አለመታጠቁ ነው እንጂ፣ጠንካራ አባላቱን መርጦ በሥውር  የህቡዕ ድርጅት ፈጥሮ ቢታጠቅ ኖሮ ድሉ የራሱ ይሆን እንደነበር አልጠራጠርም።

ታዲያ ዛሬ እየገደልኩ እሞታለሁ በሚል የአማራ ተጋድሎዎች ግብ ግብ ላይ እሥከሆኑ ድረስ፣የአገርቤቱ ትግል አንድወጥ እንዲሆን  ሁላችንም እንተባበር፣እንረባረብ። ይህ አገር ቤት እንደእነፕሮፌሰር መዐሕድ ከሕዝቡ መሀል  የሚኖር ድርጅት ወሳኝ ሚና መጫወት ይችላል።እኛ  ውጭ አገር የምንገኘው ደግሞ  የሲቪክም ሆነ የፖለቲካ ድርጅቶች  አገር ቤት ለሚንቀሳቀሰው አንድ ኃይል የደጋፊነት  እንጅ፣ የወሳኝነት ሚና ሥለማይኖረን፣የገንዘብና የሎቢ ተግባራት ላይ መረባረብ ይገባናል እላለሁ።አሁን በቅርብ በውጭ የተፈጠረውም አድማስ  የተባለውም ሥብስብ ተግባር ይህ ይሆናል የሚል ዕምነት አለኝ።

ይህ መሠረታዊ የሆነ የትግል ሀ ሁ እንደሆነ ለማንኛችንም የተሰወረ ሥላልሆነ፣ ከተናጠሉ ትግል የአንድነቱ ትግል አካሄድ ብቻ ነው  ለአማራው ወገናችን ጥርጊያ መንገድ በመክፈት ያላንዳች መቆራቆስና መተራመስ ፋይዳ ኖሮት ለድል የሚያበቃው።

በመጨረሻ! የአሥራትን ውለታ እንዴት እንከፍላለን ሥንል፣ የትግል ዓርማቸውንና የመንፈስ ጥንካሬያቸውን ተላብሰን በመታገል ነው።በኢትዮጵያ ምድር የዓሥራት ዓላማ ተግባራዊ እሥከሚሆን  ድረስ ትውልድ ሁሉ ትግሉን መቀጠሉ ውለታ ከፋይነቱን የሚያረጋግጥ ይሆናል።

የሰማዕቱ የአሥራት ሥራ ህያው ሆኖ ለዘለዓለም ይኖራል!   ትግል እሥከድል !

አያሌው ፈንቴ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *