የመኪናውን ገልባጭ በማንሳት ተሳፋሪዎችን እንደ አፈር የገለበጠው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ባሕርዳር፡ግንቦት 16/2010 ዓ/ም (አብ


 
መድ) በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በፎገራ ወረዳ የመኪናውን ገልባጭ በማንሳት ተሳፋሪዎችን እንደ አፈር የገለበጠው አሽከርካሪ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን የፎገራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደግ አረገ መሰለ እንደገለፁት በክርስትና እምነት ተከታዮቹ ዘንድ በየዓመቱ ግንቦት 12 የሚከበረው የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ በዓል ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ ምዕመናን በዓሉን አክብረው ሲመለሱ በቀን 12/09/2010 ዓ/ም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3.83913 ኢት የሆነ ሴኖትራክ የደረቅ ጭነት መኪና ከ30-40 የሚሆኑ ሰዎችን የጫነ ቢሆንም በዋጋ አለመግባባት ምክንያት ሰዎችን እንደ አፈር ገልብጦ በመጣል ጉዳት ማድረሱን አስታውቀዋል ፡፡

እንደ ዋና ኢንስፔክተር ደግ አረገ ገለፃ በህብረተሰቡ በደረሰን መረጃ መሰረት የምርመራ ቡድን በማቋቋም በ15/09/2010 ዓ/ም ተጠርጣሪውንና መኪናው በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን አስፈላጊውን የማጣራት ስራ በመስራት ለፍርድ እንደሚያቀርቡና በቅርቡ ለህብረተሰቡም የተደረሰበትን እንደሚያስታውቁ አብራርተዋል ፡፡

ከተሳፋሪዎች መካከል አንድ ግለሰብ በጉዳቱ ምክንያት ህክምና ላይ እንደሚገኝ ሃላፊው ጨምረው ገልፀዋል ፡፡
መረጃው የወረዳው የመግስንት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው፡፡

አማራ መገናኛ ብዙሃን

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *