ዛጎል ዜና – የኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ ዓመታዊ ውድድሩን በዳላስ ከሰኔ ፪፬ እስከ ፴ ያካሂዳል። በተመሳሳይ አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሰኔ ፪፮ ወይም ፪፯ ወደ አሜሪካ እንደሚያቀኑ ስለ ጉዞው የሚያውቁ ለዛጎል ተናግረዋል። የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ ጉዞ የታሰበበትና ሰፊ ዝግጅት የሚደረግበት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።


abye 3

እንደ አቶ አብይ እምነትና እቅድ በአሜሪካ ቆይታቸው ከዜጎች ጋር መደማመጥ የሰፈነበት ውይይት ያደርጋሉ። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንዳሉት አቶ አብይ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት ጉዞ በአሜሪካ በኩል ሙሉ ድጋፍ ያለውና አስፈላጊው ሁሉ ትብብር የሚደረግለት ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ አዙሪት ያሳሰባት አሜሪካ በአገሪቱ የሰከነ የፖለቲካ ለውጥ እንዲኖር፣ ለዚሁም ተግባራዊነት ድጋፍ የምታደርግ፣ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ይህንን ለውጥ የማይቀበል ከሆነ ኮሮጆውን እስከማድረቅ የሚያደርስ እርምጃ እንደምትወስድ እያስጠነቀቀች መቆየቷ ይታወሳል። በሂደት ላይ ያሉ የህግ ጉዳዮችም አሉ።

በዚሁ ቅኝት መሰረት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአሜሪካ ጉዞ በዲያስፖራውና በመንግስት በኩል ያለውን ልዩነት ለማርገብ፣ የወደፊቱን የለውጥ ሂደት የማስረዳትና በዝርዝር የማሳየት እንዲሁም አፋኝ የሚባሉት ህጎችን አስመልክቶ የሚደረገውን ማሻሻል በይፋ የምሳወቅ ነው። ተያይዞም አገራቸው መግባት ለሚፈልጉ በይፋ ዋስትና የሚሰጥ ግብዣ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በዚሁ መሰረት ውይይቱ ከመዘላለፍ፣ ከሁከትና ውጤት ከማያስገኝ እንከኖች የጸዳ ይሆን ዘንድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንን የዜናው ሰዎች አመልክተዋል። ስለ አጠቃላዩ ዝግጅት ከመናገራቸው ውጪ ስለሚደረገው ዝግጅት በዝርዝር አላብራሩም።የአሜሪካ ሚና ምን እንደሚሆንም አላስታወቁም።

ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት አቶ አብይ ወደ አሜሪካ የሚሄዱበት ወቅት እና የሰሜን አሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው ውድድር መገጣጠሙ ምን አልባትም ያልተጠበቁ ሁኔታዎች እንዲከሰቱ ሊያደርግ ይችላል። ከተመረጡበት ማግስትም ሆነ ከምርጫው ጥቂት ወራት በፊት ወደ አደባባይ በመውጣት የኢትዮጵያዊያንን ቀልብ መሳብ የቻሉት አቶ አብይ በስፖርቱ አማካይነት ሰፊ ቁጥር ያለው ህዝብ የማግነትና የማነጋገር አጋጣሚም እንደሚያገኙ ግምት አለ።

“ዜግነታቸውን እናጣራለን” በሚል በሊቢያ በተሰየፉት ወገኖች ሲያላግጡ የነበሩትን ያህል አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር “በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ግብጽ ተጉዤ በሊቢያ ታርደው በግብጽ የተቀበሩ ኢትዮጵያውያንን አስክሬን ይዤ እመለሳለሁ።ሰዎች እንደ እብድ ቢያዩኝም ይህንን ማድረግ አለብኝ።” ማለታቸው ይፋ ከሆነ በሁዋላ በዲያስፖራው መካከል ትልቅ የመወያያ እርዕስ ሆነዋል። በዚህና በሌሎች ተግባሮቻቸው ሕዝብ እሳቸውን ከኢህአዴግ ለይቶ ድጋፍ እየሰጣቸው በመሆኑ እንደ ሌሎች ባለስልጣኖች ተቃውሞ ይገጥማቸዋል ተብሎ እንደማይገመት  ጉዳዩን የሚከታተሉ ለዛጎል ገልጸዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ከሱዳን ፣ ከኬንያ፣ ከሳዑዲ አረብ በሺህ የሚቆጠሩ እስረኞችን ያስፈቱት አቶ አብይ በአገሪቱ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንደሚካሄድ ቢናገሩም ምርጫ ቦርድን አስመልክቶ የተወሰደ እርምጃ አለመኖሩ፣ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ስብሳቢ የኢህአዴግ አባል መሆናቸው፣ በአገሪቱ ያሉት አፋኝ ህጎች እንዳሉ መቆየታቸው፣ አገሪቱ በአስቸኳይ አዋጅ ስር መሆንዋ፣ የጋራ ተጠቃሚነት፣ የእስረኞች ሙሉ በሙሉ አለመፈታት፣ አሁን ድረስ የዘለቀው መፈናቀል እንዲሁም ከሁሉም የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ለመወያየትና ሁሉንም ያሳተፈ ስርዓት እንዲፈጠር የሚጋብዝ ተግባር አለመከናወኑ ጥርጣሬ የፈጠረ ጉዳይ መሆኑ አይዘነጋም።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአሜሪካ ቆይታቸው ሚኖሲታ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላትን ለይተው ስለማነጋገራቸው የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ለጊዜው በስም ያልተገለጹ አክቲቪስቶችና ፖለቲከኞችን ያነጋግራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዜናው ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

አብይ አህመድ የአስቸኳይ አዋጁ በሂሳብ ስሌት ውድቅ በሆነበት የኢህአዴግ ፓርላማ ላይ አለመገኘታቸው የሚታወስ ነው። በሌላም በኩል ህዝብ ፊት ሲወጡ ኢትዮጵያን አጉልተውና ከፍ አድርገው፣ ህዝብን አክብረው በመጥራት፣ አገሪቱ ፈጣሪ እንዲባርካት በመመኘት ላለፉት ፬፭ ዓመታት አገሪቱ ከ”መሪዎቿ” ያጣችውን ውድ ስጦታ ደጋገመው በየመድረኩ የሰጡ መሪ መሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል። ከሁሉም በላይ በባዕድ አገር እስር ቤት ያታጎሩና አስታዋሽ የሌላቸውን ዜጎች ማሰባቸው አድናቆትንና ክብርን አስችሯቸዋል።

2018-05-24 (3)

የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ውድድር ሰኔ ፪፬ ተጀምሮ ሰኔ ፴ የሚጠናቀቅ ሲሆን ዋና ዓልማው ዜጎችን ማቀራረብ የሚል ነው። በዝግጅቱ ከተለያዩ ከተሞችና አገሮች በርካታ ኢትዮጵያዊያን ይገኛሉ ትብሎ ይጠበቃል። በተመሳሳይ ስም ቁጥር ፪ በሚል እነ አቶ አብነት ገብረመስቀል ያቋቋሙት ተመሳሳይ ውድድር ዳክሮ ዳክሮ ገንዘብ ከመርጨት ውጪ ፋይዳ ሊያስገኝ ባለመቻሉ በፍረሱ አይዘነጋም።

 
 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *