የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የአቶ መላኩ ፈንታን እና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል እንዲፈቱ ትዛዝ ሰጠ።

በዚህም መሰረት በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ክስ ተቋርጣል።

ከሁለቱ ግለሰቦች በተጨማሪም አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄር፣ አቶ ከተማ ከበደ፣ አቶ ጌቱ ገለቴ፣ አቶ ገብረስላሴ ገብረ፣ አቶ ስማቸው ከበደ፣ ኮሎኔል ሀይማኖት ተስፋዬ፣ አቶ ገምሹ በየነ፣ አቶ ፍፁም ገብረመድህን፣ ጂ ኤች ሲ ኔክስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ጌታስ ኩባንያ፣ ኮሜት እና ነፃ ትሬዲንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ክሳቸው ተቋርጧል።

በተጨማሪም ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በሙስና ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ዓለማየሁ ጉጆ፣ አቶ ዋስይሁን አባተ፣ አቶ አክሎክ ደምሴ፣ አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል፣ አቶ ዘርፉ ተሰማ፣ አቶ መስፍን ወርቅነህ፣ አቶ ጌታቸው ነገሪ፣ አቶ ነጋ መንግስቱ፣ አቶ ሙሳ መሀመድ፣ አቶ ሲራጅ አብዱላሂ፣ ኮሎኔል መላኩ ደግፌ፣ ትርሲት ከበደ፣ ገዛኸኝ ኢጀራ፣ ቤዛዓለም አክሊሉ፣ ወንድሙ መንግስቱ፣ አቶ ቢልልኝ ጣሰው እና ማህደር ገብረሃናን ክስ ተነስቶ ከማረሚያ እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል።

በተጨማሪም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛና 4ኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተከሰው የነበሩት ድሪብሳ ዳምጤ፣ አንበዶ ጎንፋ፣ ዓለሙ አንበሳ፣ ዋቆ መርጋ፣ ሞሲሳ ዳግም፣ ሌሊሳ መርጋ፣ ሙሉ በለጠ፣ ፍቃዱ ቶሎሳ፣ ፀጋዬ ዓለሙ፣ በዳዳ ድሪብሳ፣ ታሪኩ በዳሳ፣ ረመዳን መሀመድ፣ በዳዳ አያና፣ ግርማ ወርቅነህ፣ ወዬሳ በቀለ፣ አህመድ ኢብራሂም፣ አብዮት አበበ፣ መሀዲ አልዬ፣ እስማኤል ዑመር፣ አህመድ አደም እና አብዱልሰመድ አህመድን ጨምሮ 137 ተከሳሾች በጠቅላይ አቃቤ ህግ ጥያቄ ጥያቄ መሰረት ክሳቸው እንዲቋረጥ ትእዛዝ ሰጥተዋል።

አቃቤ ህግ የግለሰቦቹ ክስ እንዲቋረጥ እና እንዲነሳ የጠየበትን ደብዳቤ ዛሬ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያስገባ ሲሆን፥ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ፣ 19ኛ እና 4ኛ የወንጀል ችሎቶች ጥያቄውን በመቀበል ግለሰቦቹ እንዲለቀቁ ትእዛዝ በመስጠት ይህም ተፈፃሚ እንዲሆን ለማረሚያ ቤቶች የትእዛዝ ግልባጭ ልከዋል።

በታሪክ አዱኛ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) 

Related stories   በኢትዮጵያ እየተካሄደ ላለው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ አሜሪካ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሆነች አስታወቀች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *