May 9, 2021

ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ብርሃኑ ነጋ በድንገት" አካሄድ እንቀይራለን " አሉ አገሪቱን መልሶ ወደ ጦርነት መክተት እንደማይገባ ተናገሩ

ወቅቱን ” የቂም መወጣጫና ሂሳብ ማወራረጃ አይደለም። አዲስ አገር የመገንባት፣ አዲስ ታሪክ የመስራት ሂደት ነው። ማን ያሸንፋል፤ ማን ስልጣን ይይዛል፣ ማን ይገባል የሚባልበት አይደለም” ሲሉ ገልጸውታል። ይህንን እንዲሉ ያስቻላቸው መነሻ ሃሳብ ምን እንደሆነ ባያብራሩም “

ዛጎል ዜና – ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ድርጅታቸው የአካሄድ ለውጥ እንደሚያደርግ አስታወቁ። ድንገት ስለ አካሄድ ለውጥ መናገራቸው ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል። ከሳምንት በፊት በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን የለውጥ ሂደት አስመልከተው ድጋፍ እንደሚሰጡ በጠቆሙበት ንግግራቸው የድርድር ጥያቄ እንዳልቀረበላቸውና “ድርድር ሲኖር፡ ማለታቸው ነው እንደሚያስታውቁ ተናግረው ነበር። 

የአቶ አንዳርጋቸውን ከእስር መለቀቅ ተከትሎ በትናንትናው እለት ባቀረቡት ንግግር ” አካሄዳችን ትንሽ ቀየር ይላል” ሲሉ ተደምጠዋል። እንዴትና የትኛው የትግል አካሄድ እንደሚቀየር ይፋ ግን አላደረጉም። የተቀየረ የፖለቲካ መንፈስ ሊከተሉ እንደሚችሉ ሲገልጹ መዳረሻው ግን ኢትዮጵያን ዴሞክርሲያዊ አገር ማድረግ ብቻ መሆኑንን አመላክተዋል።

የዶክተር ብርሃኑ ንግግርና ድንገተኛ የፖለቲካ አካሄድ ለውጥ ዜናቸው በሚመሩት ድርጅት አመራር በስብሰባም ይሁን በአቋም ደረጃ የተወሰነ ስለመሆኑ የተባለ ነገር የለም። ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ሰራዊት ኤርትራ ምድር ያለው ድርጅታቸው የአቋም ለውጥ ስያደርግ ሰራዊቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አልተጠቆመም። ጥያቄም አልቀረበም።

” መንገዱን ጀምረናል። እዛ እስከምንደርስ ትንሽ ጥናት ያስፈልገናል” ሲሉ የተደመጡት ዶክተር ብርሃኑ፣ ግማሽ ነጻነት፣ ግማሽ መብት፣ ግማሽ ኢትዮጵያዊነት እንደሌለ አመልክተዋል። ወቅቱን ” የቂም መወጣጫና ሂሳብ ማወራረጃ አይደለም። አዲስ አገር የመገንባት፣ አዲስ ታሪክ የመስራት ሂደት ነው። ማን ያሸንፋል፤ ማን ስልጣን ይይዛል፣ ማን ይገባል የሚባልበት አይደለም” ሲሉ ገልጸውታል። ይህንን እንዲሉ ያስቻላቸው መነሻ ሃሳብ ምን እንደሆነ ባያብራሩም ” እንደገና ይህችን አገር ወደ ሌላ ጦርነት ሳንከት … አገራችንን እዛ ደረጃ እናደርሳታለን” በማለት የአካሄድ ለውጡን አመላክተዋል። ይሁን እንጂ ቃል በቃል የትጥቅ ትግሉን እንደሚያቆሙ፣ የአካሄድ ለውጡ በማንና እንዴት እንደሚተረጎም  አልገለጹም።

ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ አገር ከማድረግ ወደ ሁዋላ የሚጎትት አንዳችም ነገር አለመኖሩን ያመለከቱት አርበኛ ብርሃኑ፣ አቶ አንዳርጋቸው ሲፈቱ የአዲስ አበባ ወጣቶች ያሳዩት ይህንኑ እንደሆነ ገልጸዋል። ካታለመው ዓላማ ሳይደረስ የሚቆም ትግል እንደሌለም አስረድተው ” ለእነ አብይ፣ ለእነ ለማ፣ ለእነ ገዱ የምንነግራቸው መልዕክትም ይህ ነው” ሲሉ ብዙም ግልጽ ያልሆነና ቀስ እያለ የሚጠራ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ዶክተር ብርሃኑ የለውጥ ሃይለ የሚባሉትን መሪዎች ስም ከመጥራታቸው ውጪ የህወሃት ሰዎችን አላነሱም። 

ዶክተር ብርሃኑ በሳምንቱ ማብቂያ በኖርዌይ ኦስሎ ንግግርና ውይይት ያደርጋሉ። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት በስብሰባው ተሳታፊዎች ይህንኑ የአካሄድ ለውጥ እንዲያብራሩ ጥያቄ ይቀርብላቸዋል ብለው ይገምታሉ።

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ እውነተኛ እርቅና የሰላም ውይይት እንደሚያስፈልጋት የሚያምኑ ወገኖች ወደ እርቅ የሚያመራውን መንገድ ይደግፋሉ። ወቅቱ በስሜትና በእልህ የሚጋለብበት እንዳልሆነም ያምናሉ። አስተያየት ይሰጣሉ። ይሁን እንጂ ይህ አገራዊ እርቅ ጸሐይ ሞቆት በግልጽ ሊሆን ይገባዋል ሲሉ ይከራከራሉ። 

በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ጓዛቸውን ጠቅልለው የገቡት የኦሮሞ ዴሚክራቲክ ግንባር አመራሮች ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ቢሆንም “በድብቅ ወሰኑትና አደረጉት” ተብለው ከህብረቱ በይፋ እንዲወገዱ እስካሁን አለመወሰኑ ለፖለቲካ በላቾች ትርጉሙ ከፈተኛ ነው። 

 
 
 
 

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0
Read previous post:
የ"ሽብር" ክስ የተመሰረተባቸው ነጻ ሆኑ – ከዛስ? "አዲስ ነገር ሲኖር እነግራችኋለሁ" ብርሃኑ ነጋ

በሕዝብ ትግል አቶ አንዳርጋቸውን ከሞት ቅጣት የመነጨቀውን ውሳኔ ተከትሎ የፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በኢሳት እና ኦ...

Close