ዛጎል ዜና – የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጁሃር መሐመድ እሳቸው የሚመሩት የሚዲያ ተቋም ወደ አዲስ አበባ እንደሚገባ በተለይ ከዛጎል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስታወቁ። ስርጭታቸው በአስር ቋንቋዎች የሚተላለፍ ሲሆን ብሄራዊ አጀንዳ ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

ለጊዜው እሳቸው ወደ አዲስ አበባ ባያመሩም የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ስርጭቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ ጥራቱንና አቅሙን ይበልጥ በማሳደግ እንደሚሰራ ያስታወቁት አቶ ጁሃር ይህ የሚሆንበትን ቀን ለይተው አልተናገሩም።

Related stories   በኢትዮጵያ የትግራይ ጉዳይ ላይ የጸጥታው ምክር ቤት ሳይስማማ ተበተነ፤ አማራ ትህነግን በህግ ሊጠይቅ ነው

media-share-0-02-04-97d213059819ee2a0d647cf20da4068342bb0c6b33f3b48f21d25f12d0512254-09153fdd-728e-49d8-97de-c247fdcab241

ኢትዮጵያ ሁሉንም የምታስተናግድ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ አገር እንድትሆን መስራት፣ ማስተማር፣ ማማከርና ልምድን ማካፈል ዋና ዓላማቸው እንደሆነ አመልክተዋል። ውሳኔው አብረዋቸው ከሚሰሩት ባልደረቦቻቸው ጋር ተመክሮበት በግልጽ አቋም የተያዘበት እንደሆነ የገለጹት አቶ ጁሃር፣ ሁሉም ነገር የሚሆነው በገሃድ መሆኑንንም ገልጸዋል።

“ሃላፊነት አለብኝ” ሲሉ  የሚፈናቀሉ ዜጎችን አስመልክቶ ችግሩ ሌሎች ወገኖች ጋር እንደሆነ ጠቁመዋል። ድርጊቱን ለመቆጣጠር በቄሮ የተለያዩ ደረጃ ባሉ አመራሮች ቀደም ሲሉ ጀምሮ ጥብቅ ውይይት እየተደረገ መሆኑንን አስታውቀዋል። በዚህም ደረጃ ዜጎችን በብሄራቸው ለይቶ ለማፈናቀል የተሞከረ ተግባር መክሸፉን ገልጸዋል።

Related stories   The Legend of the “Greater Republic of Tigray” and the Delirious TPLF Media

አቶ ጁሃር መሐመድ ከዛጎል ጋር በስፋት ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ሙሉውን በሳምንቱ መጨረሻ እናትማለን። አቶ ጁሃር ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆናቸውን፣ በዚሁም የተነሳ በአገር ደረጃ ሃላፊነት የሚሰማቸው እንደሆነ፣ ለውጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊካሄድ እንደሚገባውና ጊዜ ከፈጀ ሊቀለበስ እንደሚችል፣ ላለፉት አስር ዓመታት የሳቸው ወደ ፖለቲካው ትግል መግባት አዳዲስ የለውጥ ሃይሎች ከውስጥም ከውጭም ለመነሳታቸው ምክንያት መሆናቸውን አመልክተዋል……..

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *