“Our true nationality is mankind.”H.G.

አስቸኳይ አዋጁ ሊነሳ ነው፤ አብይ ትልቁን ጥያቄ መለሱ!!

ዛጎል ዜና – በተጭበረበረ ድምጽ ጸደቀ የተባለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ አጽድቆ ለፓርላማ ውሳኔ መላኩ ታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቀደም ሲል ከመከላከያ ሰራዊት መሪዎችና ከፍተኛ መኮንኖች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ከየካቲት ፲ ጀምሮ ለስደስት ወራት ተግባራዊ እንዲሆን ታስቦ በጸደቀው የአስቸኳይ አዋጅ ድንጋጌ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አልተገኙም ነበር። የሚኒስትሮች ምክር ቤትም ቢሆን ውሳኔውን ያሳለፈው በከፍተኛ ንትርክ መሆኑና አንዳንዶች ውሳኔው እንደሚጸድቅ የሚያውቁ ሚኒስትሮች አለመኖራቸው በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።

ይኸው በአገር ውስጥ በራሱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች፣ በተቀናቃኝ ፓርቲዎች፣ ወዳጅ በሚባሉ አገራት፣ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች  ተቃውሞ የገጠመውና  ሙሉ ድጋፍ ያላገኘው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጸጥታ ሁኔታው ተገምግሟል እንዲነሳ ዛሬ የመከረው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ ነው የተስማማው።

Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?

በዚሁ መሰረት ለፓርላማ ቀርቦ አዋጁ እንዲነሳ እንደሚደረግ የተለያዩ መገናኛዎች የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ቢሮ ጠቅሰው ዘግበዋል። የአስቸኳይ አዋጁ መነሳቱን ተከትሎ የክልል የጸጥታ ሃይሎች በነጻነት ስለሚንቀሳቀሱ አሁን የሚሰሙት የመፈናቀል ዜናዎች በክልሎች የእርስ በዕርስ ውይይትና የተቀናጀ አሰራር መፍትሄ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል የሚል ግምት አለ።

 

አዋጁ እንዲነሳ የሚጠይቀው ዝርዝር ሰነድ ለሚኒስትሮች ከመቅረቡ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከመከላከያ ሰራዊት ጀነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች ጋር ተነጋገረዋል። ፋና ቀንጨብጨብ አድርጎ ይፋ እንዳደረገው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰራዊቱ ለህገ መንግስቱ ብቻ ታማኝ እንዲሆን፣ ህዝብን ማእከል እንዲያደርግ፣ አገርን እንዲያስቀድም፣ ስብእናቸውን የሚጠብቁና ስርዓት ሲፈርስ የሚበተን የኪሳራ ድምር ሊሆን እንደማይገባ ተናግረዋል።

Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች

” በወደቀ አገር ውስጥ የሚከበር፣ የተከበረ ጀነራል የለም። በጠንካራ አገር ያለው ፲ አለቃ ይሻላል” ሲሉ አጠንክረው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢህአዴግ በራሱ ችግርና ድክመት ሕዝብ ባይመርጠው፣ አዲስ ከሚመረጠው መንግስት ጋር የሚሰራ የመከላከያ ሰራዊት ሊኖር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ይህ ንግግራቸው ገና ወደ ስልታን ሲመጡ የመከላከያ ሰራዊቱ ከፓርቲ ተጽዕኖ እንዲላቀቅ እንደሚደረግ የተናገሩትን ተግባራዊ የማድረግ ዝግጅት እንደሆነ ተመልክቷል።

 

በጠመንጃ መግዛት የማይቻልበት ደረጃ ስለተደረሰ ወደ ዴሞክራሲ ማምራት እንዳለባቸው አምነው ባፈነገጡና በቀድሞው የሃይል ስልት ለመግዛት በሚያስቡ መካከል ያለው ልዩነት መፍትሄ አላገኘም። አዲስ አስተሳሰብ የሚከተሉት ክፍሎች የፖለቲካ ስልጣኑን ቢይዙም ጠመንጃውን የያዙት ክፍሎች ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ስለማይችሉ አናርኪ ሊፈጠር እንደሚችል ስጋት አለ። በዚሁ መነሻ የአስቸኳይ ጊዜ መነሳት፣ የመከላከያ ሰራዊት ገለልተኛና ህዝብን የሚያስቀድም ሆኖ እንዲዋቀር የተጀመረው የሪፎርም ስራ በአስቸኳይ ተጋባራዊ እንዲደረግ ባለሙያዎች ይመክራሉ።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲነሳ አደባባይ በመውጣት ድጋፍና ተቃውሞ እንደሚጀመር ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በብዛት ከሚወቀሱባቸው ተግባራት የሚፈልጉ ጉዳዮች አንዱና ዋናውን እንደመለሱ ተደርጎ ካሁኑ ምስጋና ቀርቦላቸዋል። አፋኝ ህጎችንም እንዲነሱና ዋና የሆነው የምርጫ ቦርድ ገለልተኛ የመሆን ጉዳይ ትክረት እንዲሰጠው ያመሰገኑት ክፍሎች ጠቁመዋል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0