በተሳሳተ የቅዠት ፖለቲካ ኢትዮጵያን ባህር አልባ ያደረጉትን፣ ከሰባ ሺህ በላይ ዜጎችን ያስጨፈጨፉትን፣ የአገሪቱን ሕዝብ አብሮ የመኖር እሴት ያወደሙትን፣ ኢትዮጵያን ለዚህ ቀውስ የከተቱትን መሪ እያመለክ የኖረው ኢህአዴግ የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበል አስታወቀ። በስምምነቱ የዛላንምብሳና የባድመ መሬት ወደ ኤርትራ ይካለላል።

ያልተጠበቀ ስብሰባ ያካሄደው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ መገለጫ እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነት የምትቀበለው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። መግለጫው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ የተካሄደው ጦርነት በአፍሪካ ከተከሰቱ የድንበር ጦርነቶች ሁሉ ደም ያፋሰሰ ነው። ከሁለቱም ወገን በርካታ ሺህ የሰው ህይወት መጥፋቱን፣ ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከኤርትራና ከኢትዮጵያ የድንበር አካባቢ የመኖሪያ ቀዬያቸው ተፈናቅለዋል።

በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለቱ ሀገር ሕዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል የኢትዮጵያ መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት እና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የወሰነና ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን በመግለጫው አረጋግጧል።

ውሳኔውን የሰሙ ” ለምን ሙሉ ትግራይን አይሰጡም” ሲሉ የስምምነቱን ሃሳብ መጨረሻ ባማስላት የምጸት አስተያየት አሰምተዋል። ግራ የተጋባው የህወሃት ፖለቲካ ኪሳራው ገና ተደምሮ የሚያልቅ ባለመሆኑ አገር ወዳድ ዜጎች በጥልቀት እንዲያስቡ መክረዋል። ስምምነት መልካም ቢሆንም ይህ ስምምነት ቀደም ሲል ሲነቀፍ ቆይቶ ዛሬ የትግራይ ህዝብም ሆነ  የኢትዮጵያ ህዝብ በገሃድ በሃሳብ ደረጃ ሳይተየቅ Image result for badme warመወሰኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል። የሌጋሲው መጨረሻ  ይህ ሆነ ሲሉም አስተያተ ሰጥተዋል።

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

 
 

በሌላም በኩል ህወሃት የማያዳግም፣ ተመጣጣኝ፣ አጭርና ውጤታማ ወዘተ እያለ ኤርትራን እንደሚደቁስ ሲፎክር ቢቆይም አሁን ከራሱ አጋር ድርጅቶች፣ በጥቅሉ ከህዝብ በደረሰበት መተፋት የተነሳ ወውደቂያ ፍለጋ ያደረገው እንደሆነም ጭምጭምታ ሲሰማ ነበር። አዲሱ የትግራይ ክልል መሪ ሰሞኑንን በሰጡት መገለጫ ከፌደራል መንግስት ጥረት በተጨማሪ ህወሃት ከኤርተራ ጋር ለመታረቅ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረው ነበር። በጉዳዩ ላይ የኤርትራ ምላሽ እስካሁን አልታወቀም።

ፋና ይህንን ዘግቧል

ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ወሳኔ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀብላ ለመተግበር ወሰነች

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለውን የድንበር አለመግባባት ለመፍታት ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመተግበር ተስማማች።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው የኢትዮ-ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በጥልቀት በመገምገም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃና በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር ጥሪ ማቅረቡን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተውን ጦርነት በአፍሪካ ከተከሰቱ የድንበር ጦርነቶች ሁሉ ደም አፋሳሹ ነው ያለ ሲሆን፥ ከሁለቱም ወገን በርካታ ሺህ የሰው ህይወት መጥፋቱን፣ ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከኤርትራና ከኢትዮጵያ የድንበር አካባቢ የመኖሪያ ቀዬ ማፈናቀሉን መግለጫው አስታውሷል።

Related stories   ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ህልማቸው አይሳካም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረገው ጦርነት በሀገራቱ ያሉ ቤተሰቦችን አፍርሷል፣ በድንበር አቅራቢያ የሚኖሩ ዜጎች ሁሌም ያለመረጋጋትና የስጋት ስነ-ልቦና ሰለባ አድርጓቸዋል፤ በድንበር አካባቢ በንግድ የሚተዳደሩ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል ነው ያለው መግለጫው።

በድምሩ ላለፉት 20 ዓመታት በሁለቱም ሀገራት ህዝቦች ላይ መጠነ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ፈጥሯል ያለው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፤ በመሆኑም የሁለቱ ሀገራት የወደፊት ግንኙነት ምን ሊሆን ይችላል? የሚለው ጥያቄ የአብዛኛው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን እንዲሁም የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ጥያቄ ሆኖ መቆየቱን አንስቷል።

ከጦርነቱ በኋላ በአፍሪካ አንድነት ድርጅትና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አደራዳሪነት የአልጀርሱ ስምምነት ቢደረግም ላለፉት 20 ዓመታት በሁለቱ ወንድማማች ሀገሮች መካከል ጦርነትም ሆነ ሰላም የሌለበት ሁኔታ መፈጠሩን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በመግለጫው አንስቷል።

የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ወደነበረበት ለመመለስ ላለፉት 20 አመታት የተደረጉ ሙከራዎች በሙሉ ውጤት አላመጡም ያለው ማእከላዊ ኮሚቴው፥ በዚህም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በሁለቱ ሀገራት መካከል የዕውነት ሰላም ለማስፈን ከቀድሞው የተለየ አቋምና አካሄድ ያስፈልጋል ብሏል።

Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

“እኔ እበልጥ፣ እኔ እበልጥ የሚል ፉክክር ለሁለቱም ህዝቦች የሚፈይደው ነገር አይኖርም” ያለው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፥ ከዚህም በተጨማሪ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገሮችና አካባቢ የፖለቲካ ቀውስ መብረድና መረጋጋት ዘላቂው መፍትሄ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጤናማ ግንኙነት መመሥረት ነው ብሏል።

ይህን ባለማድረጉም በርካታ ለሁለቱ እህትማማች ሀገሮችም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ትልቅ ፋይዳ ያላቸዉ እድሎች አምልጠዋል ብሏል መግለጫው።

“የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ቀድሞም ቢሆን ወዳጅ ነን” ያለው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፥ “በደም፣ በባህል፣ በቋንቋና በረጅም ጊዜ የጋራ ታሪክ የተሳሰርን ሕዝቦች ነን” ብሏል በመግለጫው።

በመሆኑም በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለቱ ሀገር ሕዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል የኢትዮጵያ መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት እና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የወሰነና ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን በመግለጫው አረጋግጧል።

የኤርትራ መንግስትም ተመሳሳይ አቋም በመውሰድ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ በሁለቱም ወንድማማች ህዝቦች መካከል ከዚህ በፊት የነበረውን አብሮነትና ሰላም ወደነበረበት ለመመለስና በቀጣይም ዘላቂነቱን ለመጠበቅ ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት እንዲሰራ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ጠይቋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *