አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አካሄዳቸው ያልተመቻቸው ጥቂቶች ቢኖሩም በአብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል፣ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ጨምሮ ድጋፍ እያደረጉላቸው ነው፣


“ሙስናን አታቆላምጡት” ሲሉ በጸረ ሙስና ጥምረት ጉባኤ ላይ ንግግር ያሰሙት አዲሱ መሪ በንግግራቸው በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። አገሪቱ ወደ ሊባራል የኢኮኖሚ አስተምህሮት ፊቷን ማዞሯን ባመላከቱበት የንግግራቸው ክፍል፣ የመንግስት ንብረቶችን ወደ ግል በከፊልም ይሁን በሙሉ የማዛወሩን ሂደት ሚዲያዎች በትኩረት እንዲያዩት ጋብዘዋል፤

አገሪቱ የገባችበትን የኢኮኖሚ አዘቅት ለመታደግ ስራ መጀመሩን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ሊብነቱ የተደራጀ፣ ዘርፊያው ስር የሰደደ፣ የሞራል ዝቅጠት እንደሆነ ነው ያመለከቱት። አገሪቱ ከገባችበት እንዲህ ያለ የተደራጀ ዝርፊያ እንደትወጣ ሚዲያው ትልቅ የሚባል ሃላፊነት እንዳለው ነው ያሳሰቡት።
በኢህአዴግ መሪዎች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አቀፍ ተቋማትን በመጥቀስ ኢትዮጵያ ያለችበትን የሌብነት ደረጃ በማመላከት ነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የከረረ ወቀሳና ፍጹም ድርጊቱን በመጠየፍ የገለጹት። መነሻቸው ይህ በመሆኑ ነበር ሚዲያው ጥርስ እንዲኖረው፣ አገርና ህዝብን የሚያስቀድም፣ ለዘመቻውን ደግፍ እንዲያደርግ የጠየቁት።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

ሚዲያው ከንብረት ዝውውሩ ስር ስር በመሄድ የማጋለጥና የመጠቆም ስራ እንዲሰራ ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በባለሃብቶች ሙሉ ድጎማና በማስታወቂያ ስም የሚከናወነውን አጉል አካሄድ ወርፈዋል፤

ነጻ የፕሬስ ህግ አለ በሚባልበት አገር ያሉት “ነጻ”የሚባሉ እጅግ አነስተኛ ሚዲያዎች አፈጣጠራቸውና አቅማቸው ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት አደራና ማስጠንቀቂያ ግን ከፍተኛ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም፤
በኢትዮፕያ በግልጽ በሚታወቅ ደረጃ ባለሃብቶች፣ ትልልቅ የሚባሉ ባለስልጣኖች የሚገለገሉበት ሚዲያ አላቸው፤ ቀደም ሲል በ1997 ምርጫ ዘመን ውስን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችም በነጻ ፕሬስ ስም የራሳቸው ሚዲያና አገልጋይ እንደነበራቸው የሚታወስ ነው፤
እነዚህ ሚዲያዎች / የቀድሞዎቹን ጨምሮ/ ዋና አላማቸው ደጓሚዎቻቸውን መከላከል፣ አጉልቶ ማሳየት፣ እነሱን የተመለከተ መረጃ ሲወጣ ማስተባበልና መረጃ ያወጣውን አካል የግል ህይወት፣ ቤተስብ፣ ልጆችና ማህበራዊ እሴቱን ሳይቀር በማጠልሸት ስራ የሚጠመዱ ናቸው፤

ከአገር ቤት ውጭ አሉ በሚባሉት ሚዲያዎችም ቢሆን እንዲህ ያለው አስተሳሰብ አለ፤ ግንቦት ሰባትን ሊኮንን ያሰበ ወይም በቀናነት ሊተቹ የሚነሱ ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸዋል፤ ይኑር ይሙት በውል የማይታወቀውን ኢህአፓን መንካት ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ጥምዝ ቋንቋ መደብደብን ያስከትላል፤

ይህ በአገር ቤት ከዓመታት በፊት የታየ፣ አሁንም በማንኛውም ወቅት ሊነሳ የሚችል፣ በድጎማው መጠን የሚተኮስ ተኩስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሚዲያዎች ለጠየቁት ድጋፍ እንቅፋት እንደሚሆን ከወዲሁ ፍርሃቻ አለ፤

በተቀናቃኙ ወገን፣ በገዢው ፓርቲ እህት ድርጅቶች ዘነድ፣ በአጋር ፓርቲዎች ፣ በባለሃብቶች፣ ከባለሃብት ጀርባ ባሉ ምስለኔዎች፣ ጥላ ሆነው በሚሰሩ ሃብታሞች፣ ድርጅት በሚመራቸው ሚዲያዎች ወዘተ የተሰገሰገው እጅ ትብትቡ ቀላል ባለመሆኑ አዳዲስ ሚዲያዎች እንዲከፈቱ ማበረታቻ ሊሰጥ እንደሚገባ አስተያየት የሚሰጡ አሉ፤ ከሁሉም በላይ ግን ሕዝብ ራሱ ያለውን የማህበራዊ ሚዲያ ሚዲያዎችን ለማረቅና ከሃቅ እንዳይሸሹ መከታተያው እንዲያደርጋቸው ይገባል የሚሉ ክፍሎች “ጉዳዩ ቀላል አይደለም” ባይ ናቸው።

ሚዲያው ታፈንኩ ሲል መኖሩን የሚያስታውሱ፣ ” መስራት ለሚፈልጉ በሩ ተከፍቷል”ብለዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *