የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአልጀርስን ውሳኔ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመቀበል ኢህአዴግን የወሰነውን ውሳኔ እንደማይቀበል አስታወቀ። በባድመ የሰፈረው ሰራዊት በሃይል ከያዘው ቦታ ለቆ አንዳይወጣ አሳሰበ። ውሳኔውን የተለመደ ቅጥፈት ሲል አጣጥሎታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሞት አልባ ሲሉ የሰየሙትን ለሁለት አስርት ዓመታት የቆየውን የድንበር ውዝግብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት የአልጀርስ ውሳኔንን ሙሉ በሙሉ ለመቀበል፣ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀው ነበር። ይህንኑ ውሳኔ አስመልክቶ ከኤርትራ በኩል ወዲያውኑ ምላሽ ባይሰጥም፣ የተወሰነው ውሳኔ በዓለም ታላላቅ አገሮች ድጋፍ እያገኘ ነው።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

በአገር ውስጥ የተለያየ ስሜትን ያጫረውና በትግራይ የኤሮብ ነዋሪዎችን ለሰላማዊ ሰልፍ ያነሳሳው ይህ ውሳኔ በኤርትራ በኩል ምን ዓይነት ምላሽ ይሰጠዋል በሚል ብዙዎች በጉጉት ሲጠብቁት ነበር። ዛሬ ድምጹን ያሰማው የኤርትራ መንግስት ” ጭፍራ” በሚል ወያኔን ለይቶ በመጥራት ውሳኔውን የተለምደ ማጭበርበር ብሎታል።

ኤርትራ የአልጀርሱን ውሳኔ በመርህ ደረጃ ተቀብላ ላለፉት አስራ ስድስት ዓመታት ለተግባራዊነቱ ስትሰራ መቆየቷን ያስታወሰው መግለጫ አዲሱን የሰላም ሃሳብ ” ማሰናከያ” በማለት ኮንኖታል። ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ምንም ዓይነት ንግግር እንደማያደርጉም ይፋ አድርገዋል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ይልቁኑም የባድመን አካባቢ የተቆጣጠረው ሰራዊት ስፍራውን ለቆ እንዳይወጣ አስጠንቅቋል። አስፈላጊ ከሆነም ኤርትራ አሁን ሰራዊቷ ከሚገኝበት ስፍራም ልታነቃንቅ እንደምትችል አመላክቷል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ መለስ ካሉበት / ከውያኔ ጋር ለማለት ነው/ ዘንድ ሄደው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ያወሳው መግለጫ፣ ወያኔ እስካሁን በሃይል ይዞ የቆየውን መሬት እንዳይለቅና እንዳይወጣ በጥብቅ አሳስቧል። አያይዞም ድርድሩ በቅጽበት በሚገለጽ የአንደበት ውሳኔ ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ውይይት ብቻ ሊፈታ እንደሚገባ ጠቋሟል። በውይይቱ ስለሚነሱ ቅድመ ሁኔታዎች ግን ያለው ነገር የለም።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ኢህአዴግ የአልጀርሱን ስምምነት እቀበላለሁ ሲል ያወጣው መግለጫ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ የጠረጴዛ  ውይይት የትግበራው አካል በመሆኑ የኤርትራ መንግስት አቋምና ፍላጎት ግልጽ እንዳልሆነላቸው በትርጉም የረዱን ገልጸዋል። አክለውም በኤርትራ በኩል ውይይት እንዲደረግ የሚፈለገው ከወያኔ ጋር ብቻ እንጂ ከኢትዮጵያ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር አለመሆኑ እንዳስገረማቸው ጠቁመዋል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *