photo – An honorable exit for Samora Yunis and Getachew Assefa after being treated with a shock therapy.  Photo: Seare Mekonen in Green and Adem Mohammed in Blue.

ባሕርዳር፡ግንቦት 30 /2010 ዓ/ም (አብመድ)የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጄኔራል አደም መሐመድን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾሙ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጄኔራል አደም ከግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የተሾሙ ሲሆን፥ ያላቸው የስራ ልምድ ከግምት ውስጥ መግባቱ ተመልክቷል።
ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በጥር 26 ቀን 2010 ዓ.ም ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ወታደራዊ ማዕረጎችን በሰጡበት ወቅት ለሌ/ጀኔራል አደም መሐመድ የጀኔራልነት ማዕረግ መስጠታቸው ይታወሳል።

ከዚህ በፊትም በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ማዕረግ መሾማቸው ይታወሳል።
በሌላ በኩል በመንግስት የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ሁለት የሥራ ኃላፊዎች በጡረታ ተሰናብተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፥ ለረጅም ዓመት በተለያየ የመንግስት ኃላፊነት ያገለገሉ ሁለት የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ከግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በጡረታ ተሰናብተዋል።

በዚሁ መሰረት በጡረታ የተገለሉት በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔነታቸውን ያስተላለፉት አቶ አባዱላ ገመዳ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ግርማ ብሩ ናቸው።
አቶ አባዱላ ገመዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል። ቀደም ብሎም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው መስራታቸው ይታወሳል።

በአሜሪካ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር የነበሩት አቶ ግርማ ብሩ ደግሞ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታና በሽግግሩ ወቅት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል።

መንግሥት በቅርቡ ለረጅም ዓመት ያገለገሉ አምስት የስራ ኃላፊዎች በጡረታ ማሰናበቱ ይታወሳል።
በዚህም መሰረት በጡረታ እንዲያርፉ የተደረጉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ ዶክተር ካሱ ኢላላ ከፖለሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ አቶ በለጠ ታፈረ ከተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም፣ ዕቅድና ፖሊሲ ዝግጅት ፕሮጀክት፣ አቶ ታደሰ ኃይሌ ከንግድና ኢንዱስትሪ የፖሊሲ ዕቅድ አፈጻጸምና ክትትል፣ እና አቶ መኮንን ማንያዘዋል ከፖሊሲ ምርምር ማዕከል መሆናቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውሳል።

Source – Amhara Mass Media Agency

ላለፉት ዓመታት በጠቅላይ ኢታማዡር ሹምነት ሲያገለግሉ የነበሩት ጀነራል ሳሞራ የኑስ በክብር ተሸኙ። ዛሬ በብሄራዊ ቤተመንግስት በተካሄደ ስነስርዓት ላይ ነው ጀነራል ሳሞራ የኑስ በክብር የተሸኙት።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለጀነራል ሳሞራ የኑስ የሀገሪቱን እጅግ ከፍተኛ የኒሻን ሽልማት በብሄራዊ ቤተ መንግስት በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ አበርክተውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፥ ሽልማቱ በአንድ በኩል በክብር ለማሰናበት በሌላ በኩል ደግሞ ለስራቸው እውቅና ለመስጠት ነው የተበረከተው ብለዋል።

ጀነራል ሳሞራ የኑስ ከ40 ዓመት በላይ ከተዋጊነት አዋጊነት እንዲሁም እስከ ጦር ሀይሎች ኢታማዡር ሹምነት ሀገርን ላገለገሉበት በኢትዮጵያ ህዝብ ስም እና በራሳቸው ስም ምስጋናቸውንም አቅርበዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድ በሽኝት ዝግጅቱ ላይ ባደረገጉት ንግግር፥ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ለዚህ ሀገራዊ ክብር ስለበቁ እንኳን ደስ ያልዎት ብለዋል።

ጀነራል ሳሞራ ሀገርን ከወራሪ በመከላከል ረገድ ከፍተኛ የአመራርነት ብቃት ማሳየታቸውን የገለጹት ዶክተር አብይ፥ እስካሁን ላበረከቱት አትዋፅኦም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አክለውም፥ ወታደርነት ሀገርን መጠበቅ እና ሰንደቅ ዓላማን ማስከበር መሆኑ ቢታወቀም፥ በተለያዩ የፖለቲካ ጉድለት የተነሳ ልናፈርሳቸው የሚገቡ በርካታ ግንቦች፤ ልንገነባቸው የሚገቡ መርካታ ድልድዮች አሉ ብለዋል።

የጥላቻ፣ የዘር ግንቦች፣ የመናናቅ ግንቦች መፍረስ ይገባቸዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የፍቅር እና የይቅርታ ድልድዮች ደግሞ ሊገነቡ ይገባል ብለዋል።

ይህ የሚታይበት በሀገር መከላከያ ሚኒስትር ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ፣ በተለያየ ምክንያት ከመከላከያ የወጡ እና ማእረጋቸውን ያጡ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሀይል አዛዥሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ በይፋ ማእረጋቸው ተመልሶ በክብር የሚሰናበቱበት እለት ነው ብለዋል።

እንዲሁም ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በእስር ቤት የቆዩ፤ አሁን ከእስር ከወጡ በኋላ ማእረጋቸው ተመልሶ ከነ ሙሉ ክብራቸው ጡረታ የሚወጡበት እለትም ጭምር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ባስተላለፉት መልእክት፥ መከላከያ ብሄር እና ዘር የለውም፤ ለአንድ ሀገር፣ ለአንድ ባንዲራ በክብር የሚሞት መሆኑን በማወቅ በልዩ የፍቅር ስሜት የሚወጡትን እያከበርን የምንሸኝ፣ የትናንትናውን የምናስታውስ እና የአንድ ሀገር ወታደሮች መሆናችንን እንድንሳብ እንደዚህ አይነት መልካም ዝግጅት ላዘጋጁት ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ጀነራል ሳሞራ የኑስ በበኩላቸው፥ ሽልማቱን ለሀገሪቱ ሰራዊት የተሰጠ እውቅና አድርጌ እወስደዋለሁ ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት ሰራዊቱ ብቁ እና ዝግጁ እንዲሆን የመከላከያ ሰራዊቱ አቅሙ እንዲያድግ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት ጀነራል ሳሞራ፥ አሁን ያለው መከላከያ ሰራዊት ጠንካራ ሰራዊት ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጀነራል ሰዓረ መኮንንን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዡር ሹም አድርገው ሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጀነራል ሰዓረ መኮንንን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዡር ሹም አድርገው ሾሙ

የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጀነራል ሰዓረ መኮንንን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዡር ሹም አድርገው ሾሙ።
ጠቅላይ ኢታማዡር ሹሙ ከግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሲሾሙ የአላቸውን ልምድ ከግምት ውስጥ መግባቱን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በጥር 26 ቀን 2010 ዓ.ም ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ወታደራዊ ማዕረጎችን በሰጡበት ወቅት ሌ/ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ይመር የጀኔራልነት ማዕረግ መስጠታቸው ይታወሳል።
ጀነራል ሰዓረ ከዚህ በፊት በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ማዕረግ መሾማቸው ይታወቃል።
Fana broadcasting
Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *