ሀገሪቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግብፅ ጉብኝታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት በደረሱት ስምምነት መሰረት ነው ኢትዮጵያውያኑን የፈታችው።

ከእስር የተለቀቁት 32 ኢትዮያውያንም ዛሬ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የጠቅላይ ሚኒስቴር ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ በሊቢያ የባህር ዳርቻዎች በአሸባሪው አይ ኤስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን አስከሬንን ለማግኘት በሚደረገው ጥረት ሃገራቸው እገዛ እንደምታደግርም ቃል ገብተዋል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ግብጽ ያመሩት ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር አብይ አህመድ፥ ከግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታ አል ሲ ሲ ጋር በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ሃገራቱ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሁለቱን ሃገራት የመልማት ፍላጎት ባከበረ መልኩ በአዲስ መንፈስ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

ከዚህ ባለፈም መሪዎቹ ሁለቱ ሃገራት በተለያዩ መስኮች በተለይም በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

ሁለቱ መሪዎች ሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በማጠናከር በጋራ መስራት እንደሚገባቸው ጠቅሰው፥ በወንድማማችነት መንፈስ በሃይል ዘርፍ መሰረተ ልማቶችን በጋራ ለማልማት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። መሪዎቹ በውይይታቸው የሃገራቱን ግንኙነት በትብብር መንፈስ በተቃኘ ስትራቴጂክ አጋርነት ለማሳደግም ነው የተስማሙት።

ከዚህ ባለፈም ሃገራቱ የጋራ በሆኑ ጉዳዮቻቸው ላይ በቅርበት ለመስራትም ስምምነት ላይ ደርሰዋል። መሪዎቹ በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ባደረጉት ውይይት በደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት በትብብር ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

የግብጹ ፕሬዚዳንት አዱል ፈታ አል ሲ ሲ በኢትዮ – ኤርትራ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ባሳለፈው ውሳኔ ላይ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

fana

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *