ተወልደ በዓየር፤ አለሙ በባህር፣ ጌታቸው በባቡር፣ መለስ በሃድሮፓወር፣ ግርማዬ በምድር፣ አባይ በስኮር፤ አርከበ በኢንዱስትሪ መንደር፣ ተክለወልድ በባንክ ብር፣ደብረፂዮን በቴሌኮም ብድር፣ አዜብ የኢፈርት የዶላር አጥር፣ ክንፈ የሜቴክ የብር በር፣ ኢኮኖሚያችን ወደቀ ከሸረሪቶ ድር!!!

መንግሥታዊ የመገናኛ ብዙሃን ፕራይቬታይዝ ይደረጉ፣ የፌዴራልና የክልል መገናኛ ብዙሃን የቴሌቪዝን፣ ሬዲዩና ኤፍ ኤም ሬዲዮኖች ለግሉ ዘርፍ በአክሲዮን ይሸጡ፡፡ ነፃ ፕሬስና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ነፃነት የሚረጋገጠው አድርባይ ምላሳዊ ጋዜጠኞች ተወግደው የህዝብ ልጆች ንብረትና ኃብት ሲሆኑ ብቻ ነውሙስና ሌብነት ከኢትዮጵያ ምድር የሚጠፋው፡፡ ነፃ ጋዜፆችና መጥሄቶች እንደአሸን እንዲፈሉ አፋኙ የፕሬስ ህግ፣ ፀረ-ሽብርተኛነት ህግ በአፋጣኝ እንዲነሳ እንታገል!

ለኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረ ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጋሩ፣ ለሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራቶች፡- ቀጣዮን ብሄራዊ የወጣቶች የትግል አቅጣጫ ማሳየት ይጠበቅባችኃል፡፡ የኦሮሞ ቄሮ፣ የአማራ ፋኖ፣ የደቡብ አቦሸማኔ (የጉራጌ ዘርማ)፣ ለአፋር፣ ለሱማሌ፣  ለትግራይ አናብስቶች!!! ለዴሞክራሲያዊና ፕሬስ ነፃነት እውን መሆንና መከላከያ ሠራዊቱና ኮማንድ ፖስቱ በተግባር ወደ ጦር ካንፑ መመለሱን ማረጋገጥ የህልውና የትግላችን ውጤት መሆኑን አንርሳ፡፡

{1} ዕዳ ከጂዲፒ በመቶኛ፣ Debt as a Perentage of GDP፣ በ1992 እኤአ ህወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን በያዘበት ዓመት የኢትዮጵያ ዕዳ ከአማካይ ብሄራዊ ምርት ድርሻ በመቶኛ  12,550 ዶላር በእያንዳንዱ ዜጋ ድርሻ ነበረው፡፡ በ1995 እኤአ 12,001  ዶላር ዕዳ፣ በ2000 እኤአ 7,707 ዶላር እዳ፣ በ2005 እኤአ 9,695 ዶላር እዳ፣በ2010 እኤአ 12,114 ዶላር እዳ፣በ2015 እኤአ 34,931 ዶላር ዕዳ፣ በ2016 እኤአ የኢትዮጵያዊያን የወከፍ ዕዳ 40,219 ዶላር በእያንዳንዱ ዜጋ ድርሻ ሆኖ አደገ፡፡ እዳው የመንግስት ልማት ድርጅቶችን›ብድር አይጨምርም፡፡

 

የመንግስት ልማት ድርጅቶችን፣ State Owened Enterprise

{1}አየር መንገድ፣(5.6 ቢሊዮን ዶላር)፣{2} ኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን፣ (4.8 ቢሊዮን ዶላር)፣ {3} የኢትዮጵያ መብራት ኃይል፣ (5.4 ቢሊዮን ዶላር)፣ {4} ኢንዱስትሪያል ፓርኮ (10 ቢሊዮን ዶላር)፣ {5} የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን (5.5 ቢሊዮን ዶላር)፣ {6} የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (5.9 ቢሊዮን ዶላር)፣ {7} የኢትዩጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት (301.5 ሚሊዩን ዶላር)፣ {8} የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ (300 ሚሊዩን ዶለር) ከባህር ማዶ ሃገራት ሃገራት (ከቻይና፣ ህንድ፣ ዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ባንክ፣ አይ ኤፍ ኤም ወዘተ) ብድር ተበድረዋል፡፡ የመንግሥታዊ ኢንተርፕራይዝ ብድር እዳ ሲጨመር፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በነፍስ ወከፍ 15 እስከ 20 ሽህ ብር ዕዳ አለበት፡፡

 

የነፍስ ወከፍ ዕዳ፣ Debt Per Capita በ1992 እኤአ ህወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን በያዘበት ዓመት የኢትዮጵያዊያን የነፍስ ወከፍ ዕዳ 878 ብር በእያንዳንዱ ዜጋ ድርሻ ነበረው፡፡ በ1995 እኤአ 7595 ብር ዕዳ፣ በ2000 እኤአ 4235 ብር እዳ፣ በ2005 እኤአ 4515 ብር እዳ፣በ2010 እኤአ 5110 ብር፣ በ2015 እኤአ 13615 ብር የነፍስ ወከፍ፣ በ2016 እኤአ የኢትዮጵያዊያን የነፍስ ወከፍ የዜጋ ዕዳ 441 ዶላር በእያንዳንዱ ዜጋ ድርሻ ሆኖ አደገ፡፡

Ethiopia፡ Evolution of Debt

Ethiopia፡ Evolution of Debt as a perentage of GDP (in millions)

Date   Debt Debt (%GDP) Debt Per Capita Debt Per Capita(Dollar) Debt PerCapita(Birr) 1 =35
2016 36,335 40,219 54.97% 398€ 441$ 15435
2015 31,483 34,931 54.01% 351€ 389$ 13615
2014 19,551 25,974 46.80% 221€ 294$ 10290
2013 15,384 20,432 42.88% 177€ 235$ 8225
2012 12,635 16,233 37.66% 148€ 190$ 6650
2011 10,410 14,491 45.33% 124€ 172$ 6020
2010 9,138 12,114 40.53% 110€ 146$ 5110
2009 8,813 12,292 37.81% 108€ 151$ 5285
2008 7,600 11,178 41.68% 95€ 139$ 4865
2007 6,724 9,215 46.78% 85€ 117$ 4095
2006 8,514 10,690 69.95% 110€ 139$ 4865
2005 7,793 9,695 78.24% 104€ 129$ 4515
2004 8,411 10,462 103.10% 115€ 143$ 5005
2003 7,907 8,944 103.69% 111€ 125$ 4375
2002 8,925 8,440 107.37% 133€ 126$ 4410
2001 8,936 8,003 97.33% 137€ 122$ 4270
2000 8,345 7,707 93.63% 131€ 121$ 4235
1999 7,004 7,465 97.78% 113€ 121$ 4235
1998   6,948 89.29%   115$ 4025
1997   6,898 80.26%   118$ 4130
1996   11,382 132.80%   200$ 7000
1995   12,001 146.58%   217$ 7595
1994   12,258 155.16%   229$ 8015
1993   12,516 140.96%   242$ 8470
1992   12,550 87.94%   251$ 8785

Source:-   © Statista 2018 በዚህ ፁሁፍ ሁሉም መረጆቹ የተገኙት ከዚህ ድረ-ገፅ ነው፣ ይመልከቱት፡፡

ማሳሰቢያ፤ ሠንጠረዡ የኢትዮጵያ የውጭ እዳ የ‹መንግስታዊ የልማት ድርጅቶች› ብድር አያካትትም!!!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ እዳ፣ National Debt of Ethiopia Billion U.S. Dollars.  የሃገሪቱ ብሄራዊ ብድር፣ ከ2012 እኤአ እስከ 2022 እኤአ የባህር ማዶ መፃሂ የዕዳ ትንበያ በቢሊዮን ዶላር በ2018እኤአ 45.33 ቢሊዩን ዶላር፣ በ2019እኤአ 52.17 ቢሊዩን ዶላር፣ 2020እኤአ 59.32 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2021 እኤአ 68.05 ቢሊዮን ዶላር እና በ2022እኤአ 78.19 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ የሃገሪቱ ብሄራዊ ብድር፣ አመታዊ አማካኝ የሃሪቱ ውስጥ ምርት 50.4 በመቶ ድርሻ ሲኖረው ከዓለም አቀፍ ሃገራት 67ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡  በ2018እኤአ 56 እስከ 58 በመቶ ድርሻ ይዞል፡፡

Value & Rank: The public debt (percentage of GDP) of Ethiopia is 50.4 (% of GDP) with a global rank of 67.

Average: Ethiopia had an average public debt (percentage of GDP) of Ethiopia is 42.7 (% of GDP) in the last 5 years from (2008 to 2013).  በ2016እኤአ 32.54 ቢሊዮን ዶላር የኢትዮጵያ ዕዳ መጠን ከሃገራዊ አጠቃላይ ምርቶ 55 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2017 39.14 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ቀላል የማይባል ለውጥ በማሳየት ወደ 56 በመቶ አድጎል፡፡ ከ2018 እኤአ እስከ 2022 እኤአ ብሄራዊ እየጨመረ እንደሚሄድ ከሠንጠረጁ ማስተዋል ይቻላል፡፡ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መረጃ በተለይ የሃገሪቱ ብድርና የዕዳ ጫና በወያኔና በብሄራዊ ባንክ ገዥዎች በብረት ሣጥን ተቆልፎ የተደበቀ በመሆኑ መረጃ ማግኘት ከባድ ነው፣ ብዙ ጊዜ አንዱ ከአንዱ የተጣረሰ የስታትስቲክስ መረጃ መስጠት የተለመደ ክስተት ነው፡፡

National Debt of Ethiopia Billion U.S. Dollars.

Year 2012 2013 2014 2015 2016 2017 2018 2019 2020 2021 2022
Reserve 10.15 13.53 18.07 28.66 32.54 39.14 45.33 52.17 59.32 68.05 78.19

The statistic shows the national debt of Ethiopia from 2012 to 2016, with projections up until 2022. In 2016, the national debt of Ethiopia amounted to around 32.54 billion U.S. dollars.

የኢትዮጵያ የዕዳ መሸከም ጫናና ወለድ የመክፈል አቅም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሶል!፣ “High Risk of Debt Distress.”

ከሳህራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት የዕዳ ጫናቸው እያደረ ወደ ሰማይ መጥቶል ምክንያቱም ከፍተኛ ብድርና ያጋጠማቸውን ኪሳራና እጥረት ለመሸፈን ሲሉ በእዳ ይዘፈቃሉ ምንም እንኮን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት እያደረጉም ቢሆን ይላል ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት፡፡ የአፍሪካ አገራት ከዓለም ዓቀፍ የብድር ገበያ ብድር ማለብ ቀጥለዋል እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ብድር ሪከርድ ሰብረዋል ባልተረጋጋው የኢንቨስተሮች ፍላጎት ለቀጣይ ምርት ሂደት፡፡  የዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ዴሬክተር አበበ ዓዕምሮ ስላሴ ለሮይተር እንደገለጡት ድርጅቱን ያሳሰበውና የእዳው ጫና የእድገቱ ጭማሪ ከአማካዮ በላይ መሆኑ ነበር፡፡ ድርጅቱ የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ እድገት 3.4 ከመቶ በ2018እኤአ ሲገመት በ2017እኤአ ከነበረው 2.8 በመቶ ዓለም ኣቀፍ እድገት የምርት ዋጋ መጨመር እንደሚኖር ገልፀዋል፡፡ ምንም እንኮን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሃገራቶች   40 በመቶ አካባቢ የዕዳ ጫና በከፍተኛ አደጋና ስጋት ውስጥ ይገኛሉ፣ እዳቸውን ለመክፈልም ከፍተኛ ዋጋ ይከፍላሉ፡፡

የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ዕዳ ድርሻ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዕዳ 40,219 ቢሊዩን ዶላር ብድር ከአማካይ የአገር ውስጥ ምርት ድርሻው 54.94 በመቶ ሲሆን፣ ከ2015 እኤአ 5,288 ቢሊዮን ዶላር ጨምሮል ወይም 0.96 በመቶ አድጎል፡፡ የ2015እኤአ  ብድር ከአማካይ የአገር ውስጥ ምርት ድርሻው 54.01 በመቶ ነበር፡፡ ከሠንጠረዡ  ላይ ለመረዳት እንደምንችለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዕዳ ታሪካዊ ዝግመታዊ እድገትን መቃኘት ይቻላል፡፡ በ2006 እኤአ በዓለም አቀፍ የዕዳ ደረጃ እድገት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዕዳ 10,690 ቢሊዮን ዶላር ከአማካይ የአገር ውስጥ ምርት ድርሻው 69.95 በመቶ ዝቅ ብሎ ነበር፡፡ በመረጃው መሠረት የነፍስ ወከፍ ዕዳ ድርሻ እድገት በ2006 እኤአ 139 ዶላር ነበር፣  በ2015 እኤአ 389 ዶላር ነበር፣ በ2016 እኤአ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊያን ዜጋ የነፍስ ወከፍ ዕዳ 441 ዶላር  ደረሰ፡፡ የኢትዮጵያ የእዳ ጫና፣ ከተቀሪው ዓለም ጋር ስናወዳድር በ2016 እኤአ የነፍስ ወከፍ ዕዳ ድርሻ ከዓመታዊ አማካይ ብሄራዊ የሀገር ውስጥ ምርት መቶኛው የባሳ ነበር፡፡  በ2016 እኤአ የዕዳ ከዓመታዊ አማካይ ብሄራዊ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ (Debt/GDP) 109ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ፣ የነፍስ ወከፍ ዕዳ ድርሻ 36 ከ185 አገራቶ መኃል ትገኝ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የህዝብ እዳ እድገት ከሌሎች አገሮች ጋር በማወዳደር ከድረ-ገፁ ማስተዋል ለግንዛቤ ይረዳል እንላለን፡፡ በሃገራችን ሁሉም ዜጋ በእንግድነት መጥቶ ኖሮ ይሞታል፣ ፍቅር ብንዘራ ኃብት ይበዛል፣ ለልጅ ልጆቻችን የሚተርፍ ኃብት አለን፡፡ የኢትዮጳያ ህዝብ በ2050 እኤአ 150 ሚሊዮን ይሆናል፣ ለምን የህሊና የሃብት ሰቀቀን ደዌ ተጠናወተን፣ ከሠራን ለሁላችንም የሚተርፍ ኃብት እያለን፣ በዘርና ብሄር ተለከፍን፡፡

{2} የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብና ወርቅ፣ የሃገራችን የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብና ወርቅ ክምችት በ2013 እኤአ 3.3 ቢሊዮን ሲሆን ከዓለም አቀፍ አገራቶች በ101 ደረጃ ላይ ትገኝ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ በ2017/18 እኤአ ያላት የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብና ወርቅ ክምችት ከወራት ወደ ቀናት የሚሆን ነው፡፡ ለህክምና መገልገያ የላብራቶሪ ኬሚካሎችና መድኃኒት መግዣ የሚሆን ዶላር ጠፍቶል፡፡ ብሄራዊ ባንክ ገዥ የሃገሪቱ የወርቅ የማዕድን ፋብሪካዎች ከሜድርክና ከኢዛና ወርቅ ተመርተው የሚወጡ የወርቅ ምርቶች  ብሄራዊ ባንክ  ሳይገቡ በቀጥታ ወደ ውጭ ሃገር ተልከው እንደሚሸጡ ታውቆል፣ ለዚህ ነው በኢትዮጵያ በመንግሥት ውስጥ ሥውር መንግሥት እስካለ ድረስ የውች ምንዛሪ መጠባበቂያና ወርቅ ክምችት በብሄራዊ ባንክ እንደማይኖር የምንገልፀው፡፡

Reserves of Foreign Exchange and Gold (Millions Of $)-Ethiopia)

Value& Rank: The Reserves of foreign exchange and gold of Ethiopia is 3.38(billions$) with a global rank of 101.

Average: Ethiopia had an average Ethiopia had an average Reserves of foreign exchange and gold of 2.30 (billions of $) in the last 5 years from (2008 to 2013).

Reserves of Foreign Exchange and Gold (Millions Of $) -Ethiopia)

Year 2005 2006 2007 2008 2009 2010 2011 2012 2013
Reserve 1,226 833 1,290 871 1781 1,808 2,671 3,272 3,382

{3} የኢትዮጵያ መንግሥታዊ በጀት ከብሄራዊ አማካይ ምርት በመቶኛ፣ Ethiopia’s budget balance in relation to GDP

በሃገሪቱ የገንዘብ እጥረት ቀውስ ተከስቶል በዚህም ማህበራዊ ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል አሳስበዋል፡፡ የውጭ ንግድ ደካማ መሆን የተነሳ በውጭ ምንዛሪ እጣት የኮፒታል ጉድስ ከውጭ መግዛት አልተቻለም፡፡ እንዲሁም ከውጭ መንግሥታትና ተቆማት ጭምር አዲስ ብድር ማግኘት አልተቻለም፣ ሃገሪቱ ያለባት ብድርና የብድር ጫና አስጊ ደረጃ ላ እንደሚገኝ ኤ ኤም ኤፍ አስታውቆል፡፡የኢትዮጵያ በጀት ሚዛን ጉድለት ከ2012 እስከ 2022 እኤአ ትንበያ መሠረት ኔጌቲቨ መሆኑን ከሠንጠረዡ ላይ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ሁለተኛው የእድረትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ወድቆል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ዓመታዊ ባጀት(ቢሊዩን ብር) ከ2002/2009 እንደ ኢትጵያዊያን አቆጣጠር

የባጀት ዓይነት 2002ቢሊዩን ብር 2004ቢሊዩን ብር 2006ቢሊዩን ብር 2007ቢሊዩን ብር 2008ቢሊዩን ብር 2009ቢሊዩን ብር 2010ቢሊዩን ብር
ለመደበኛ ወጪ 14.5 23.0 32.56 45.05 50.288 82 91.7
ለካፒታል ፕሮጀክቶች ወጭ 29.1 48.0 64.29 66.99 84.300 115 113.6
ለክልል መንግስት ድጋፍ 20.9 31.4 43.09 51.50 76.808 117 135.6
ለምዕተ አመቱ የልማት ግቦች ማጠናከሪያ 15.0 15.00 15.00 12.000    7.0 6.0
ጠቅላላ ዓመታዊ የፌዴራል መንግስት ባጀት 64.5 117.8 154.94 178.6 223.3 321.8 346.9

 

{4} የመንግሥታዊ ወጪ ድርሻ ከኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ዓመታዊ ባጀት በመቶኛ እንዲሁም የፌዴራልና የክልል መንግሥት የበጀት ጅርሻ በመቶኛ  ከ2002ዓ/ም እስከ 2010 ዓ/ም ይቀርባል፡፡

 አመት 2002 2004 2006 2007 2008 2009 2010
ካፒታል ወጪ ከአጠቃላይ በጀት በመቶኛ 45.1 40.7 41.5 37.5 37.8 35.7 32.7
የፌዴራልና የክልል መንግሥት የበጀት ጅርሻ በመቶኛ 77.5 67.4 69 66.3 72 72.1 71.8

መንግሥታዊ ኢንቨስትመንት ወጪ ከብሄራዊ አማካይ ምርት በመቶኛ Ratio of Government Expenditure to GDP

በኢትዮጵያ መንግሥታዊ ኢንቨስትመንት ወጪ ከብሄራዊ አማካይ ምርት በመቶኛ  ከ50 እስከ 60 በመቶ እንደሚሸፍን ይታወቃል በዚህም ምክንያት የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ እድረቱ የቀጨጨ ለመሆን በቅቶል፡፡ መንግሥት መር ‹‹ ልማታዊ መንግሥት›› የኢንቨስትመንት ወጪ ያለጥናት  በመከናወኑ ምክንያት ገንዘቡ ለምዝበራ መዳረጉን ዋናው ኦዲተር ቢሮ ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት በተደጋጋሚ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ የወያኔ ኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች ሃገሪቱን በቁሞ የራጡ ዘራፊ ድርጅቶ መሆናቸው ተጋልጦል፣ ለዳክተር አብይ አህመድ ኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች ንብረትና ሃብት በመውረስ ለህዝብ በአክሲዎን በመሸጥ ታሪክ እንዲሰራ ህብረ ብሄር የወጣቶች ህዝባዊ ዴሞክራቲክ ጋርድ በሚሥጢር በማደራጀት ድጋፍ ማድረግ የሞት ሽረት የትግላችን ሂደት ካልሆነ አየር መንገድ፣ ቴሌኮም፣ ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ሃድሮፓወር፣ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ወዘተ የቻይናና የወያኔ ኢፈርት/ሜቴክ ንብረት እንደሚሆን አንጠራጠርም!!!

የኢትዮጵያ በጀት ሚዛን ጉድለትEthiopia: Budget balance  የኢትዮጵያ በጀት ሚዛን ጉድለት ከ2012 እስከ 2022 እኤአ ትንበያ ከብሄራዊ አማካይ ምርት በመቶኛ፣ መሠረት ኔጌቲቨ መሆኑን ከሠንጠረዡ ላይ ማስተዋል ይቻላል፡፡ በ2011 ዓ/ም በጀት ዓመት 59 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንዳለበት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ገልፀዋል፡፡

The statistic shows Ethiopia’s budget balance in relation to GDP between 2012 and 2016, with projections up until 2022. A positive value indicates a budget surplus, a negative value indicates a deficit. In 2016, Ethiopia’s budget deficit amounted to around 2.34 percent of GDP.

Budget Balance in Relation to GDP

Year 2012 2013 2014 2015 2016 2017 2018 2019 2020 2021 2022
Gov Exp -1.17% -1.93% -2.58% -1.95% -2.34% -3.35% -2.46% -2.44% -2.29% -2.2% -2.13%

The statistic shows Ethiopia’s budget balance in relation to GDP between 2012 and 2016, with projections up until 2022. A positive value indicates a budget surplus, a negative value indicates a deficit. In 2016, Ethiopia’s budget deficit amounted to around 2.34 percent of GDP.

የህወሃት/ኢህአዴግ አንባገነንና ፀረ-ዴሞክራሲ  አገዛዝን እንዋጋ!!!

ህብረ ብሄር የወጣቶች ህዝባዊ ዴሞክራቲክ ጋርድ በሚሥጢር  ይደራጅ!!!፡

(ተፃፈ ሰኔ 2010ዓ/ም )

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *