ስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ዩለን ሎፔቴጉይን ከሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ። የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቢያሌስ፥ አሰልጣኝ ሎፔቴጉይ ፌዴሬሽኑን ሳያማክሩ ሪያል ማድሪድን ለማሰልጠን በመስማማታቸው ምክንያትት ከሃላፊነት ለማንሳት መገደዳቸውን ተናግረዋል።

አሰልጣኙ የብሄራዊ ቡድን ሃላፊነት እያለባቸው ይህን ማድረግ እንዳልነበረባቸውም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል። ሁኔታው ውስብስብ ቢሆንም የስፔን የአሰልጣኞች ቡድን አባላት ብሄራዊ ቡድኑ በአለም ዋንጫው ስኬታማ ይሆን ዘንድ ሃላፊነታቸው እንደሚወጡ እምነቴ ብለዋል።

ሎፔቴጉይ ስፔንን ባለሰለጠኑበት ወቅት ለሰሩት ስራም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሩቢያሌስ። አሰልጣኝ ሎፔቴጉይ ሪያል ማድሪድን ለሶስት አመታት ለማሰልጠን ትናንት መስማማታቸው ይታወሳል። የአሁኑ የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ግን በስፔን ብሄራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ ቆይታ ላይ ተፅዕኖ እንዳይፈጥር ተሰግቷል። ስፔን ከነገ በስቲያ በአለም ዋንጫው የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከፖርቹጋል ጋር ታደርጋለች።

ምንጭ፦(ኤፍ ቢ ሲ)

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *