የሰልፉ አዘግጆች እንዳሉት ሰልፉ የሚካሄደው ምስጋና ለማቅረብ። ላለፉት በጣት የሚቆጠር ወራት የተሰራው ስራ እጅግ ተስፋ የሚሰጥና ህዝቡን ያረካ በመሆኑ ነው ምስጋና መስጠት ያስፈለገው። የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አካሄድና አሰራር ኢትዮጵያን ከገባችበት ማጥ ውስጥ የሚያወጣት ስለሆነ ” አብረንህ ነን” ለማለት ነው።

ደስ ያላቸው ያሉትን ያህል አይናቸው የቀላ መኖራቸውን አዘጋጆቹ ጠቁመው ይህ የተጀመረው አዲስ ተስፋ እንዳይደናቀፍ ህዝብ አለኝታነቱን ሊያሳይ እንደሚገባ፣ መሰለፍና ድምጽን ማሰማት መብት በመሆኑ ሁሉም ያገባኛል የሚል ዜጋ በተጠቀሰው ቀን ወደ መስቀል አደባባይ እንዲያመራ ጥሪ አስተላልፈዋል።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

 
https://www.facebook.com/ethiopia.first2/videos/226535354616448/?t=498

ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው ጥቂት ወራት በፊትና የአገሪቱ መሪ ከሆኑበት ቅጽበት ጀምሮ የሕዝብ፣ የአካባቢንና የዓለምን ቀልብ የሳቡት አዲሱ የኢትዮጵያ መሪ እያደረጉት ያለው ነገር በሙሉ እስካሁን ለማመን የሚያስቸግር ነው። እሳቸውን ወደ ሃላፊነት ለማምጣት ዋጋ የከፈሉትን ክቡር ለማ መገርሳን በማሰብ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ህዝብ ልቡን ሰጥቷቸዋል። ሕዝብ አልቅሶላቸዋል። ሕዝብ ለሳቸው ካለው ፍቅር የተነሳ ጸሎት እያደረገላቸው ነው።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

አስፍተው የሚያዩትና የመሪነት እውቀት ካለ አንዳች ተንኮል የተካኑት አብይ ጥቂቶች እንዳልወደዷቸው ይታያል። ንግግራቸውን በመመንዘርና አካሄዳቸውን በተለመደው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መዳፍ ስር መልሶ ለመወተፍ እየሰሩ ያሉ አኩራፊዎችም እንዳሉ እየተሰማ ነው።

lema and abye.png

ከተባራሪ አስተያየቶች እንደሚደመጠው ቅዳሜ በ፩፮ ይደረጋል የተባለው ሰልፍ በ፩፱፱፯ የቅንጅት ማዕበል ጋር ይዛመዳል እየተባለ ነው። በስለፉ አስተባባሪዎች ግምት ባይሰጥም ሰልፉ ግን የተቃና ስለመሆኑ በርግጠኛነት ተጠቁሟል።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለመቃወም በህወሃት ወዳጆችና አፍቃሪዎች የተጠራው ሰልፍ እንዲቀር መደረጉ ይፋ ቢሆንም የድጋፍ ሰልፉ እንደማይቀር አዘጋጆቹ ገልጸዋል። የተጀመረው ለውጥ ወደ ሁዋላ እንዳይመለስ ድጋፍን በአደባባይ ማሳየት ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አለኝታ መሆን እጅግ ውድና አስፈላጊ ነው ተብሏል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *