ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ በክፈተኛ ደረጃ ሃብት መዘረፉንና በውጭ አገር ባንኮች መቀመጡን ማስታወቃቸውን ተከትሎ ጉዳዩን አሜሪካ እየተከታተለችውና መረጃ እያሰባሰበች መሆኑ ተሰማ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንዳንድ መንግስታት ድጋፍ ማግኘታቸውን ማስታወቃቸው የዚሁ ማሳያ ነው ተባለ።

” አታቆላምጧቸው ሌቦች በሉዋቸው” በሚል አጥብቀው የሚያወግዙትን የሙስና ችግር አስመልክቶ ለአሜሪካ ዲፕሎማት ምንጮች ቅርብ የሆኑ ለዛጎል እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ተግዟል የተባለውን በሁለት አሃዝ የሚቆጠር  ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያሸሹት ተለይተዋል።

ከፍተኛውን እርዳታ የምትሰጠው አሜሪካ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በህወሃት ላይ ያላት እምነት መመናመኑንን ተከትሎ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመርዳት ቁርጠኛ አቋም እንዳላት በተደጋጋሚ ስታስታውቅ ቆይታለች። በግልጽ ባይወጣም አሁን በምስራቅ አፍሪቃ ቀጠና የተጀመረው የኢኮኖሚ ትስስርና እስከ ውህደት የሚዘልቅ እንቅስቃሴ ከአሜሪካን ድጋፍ አለው።

በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን ከፍተኛ ሃብት ስትከሰክስ የቆየችው አሜሪካ የቀጠናውን ሃላፊነት ኢትዮጵያ በበለይነት እንድትመራው ያላት ፍላጎት ባይቀየርም፣ የቀድሞውን አካሄድ ግን አትፈልገውም። በቀተናው እስከ መዋሃድ የሚደርስ መስተጋብር እንዲፈጠር ፍላጎት ስላላት ይህንን ትረዳለች። 

የዜናው መረጃ አቀባይ እንዳሉት አሁን ከኤርትራ ጋር በሚደረገው ስምምነት፣ በሶማሌ ወደብ ላይ ለሚደረገው ስምምነት፣ አሜሪካ ተሳትፎዋ አለበት።

አሜሪካ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ህዝብ የሚቀበለው አመራር፣ መሪና አስተማማኝ ሰላም ያለው አስተዳደር እንዲመሰረት ትፈልጋለች። በዚሁ መነሻ  ለዲሱን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በሙሉ ፍላጎት ድጋፍ እያደረገች እንደሆነ ምክንያት እየፈለገች ማረጋገጫ የምትሰጠው አሜሪካ፣ ለአዲሱ መሪ እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮችን ከደህንነት ስጋት ጀመሮ እንደምትከታተል መረጃውን ያቀበሉት ተናግረዋል።

በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከኢትዮጵያ በሁለት ዲጂት የሚቆጠር ቢሊዮን ዶላር ከኢትዮጵያ ተዘርፎ መውጣቱን መዘገባቸውና ሪፖርት በተደጋጋሚ ማውጣታቸው አይዘነጋም። በተለያዩ ወቅቶች የወጡትን ሪፖርቶች በማታታል የሚታወቀው ኢህአዴግ፣ አሁን በተመረጡት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርና የድርጅቱ መውሪ አማካይነት ይህንኑ ሲስተባበል የኖረውን ሪፖርት ዋቢ በማድርገ በአደባባይ ምስክርነቱን ሰጥቷል። ዶከተር አብይ ” እመኑኝ” ሲሉ ከፈተኛ የሃገር ሃብት መዘረፉንና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ከትናንት በስቲያ ለፓርላማ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *