“Our true nationality is mankind.”H.G.

"ለውጥ ዋጋ ያስከፍላል … ስንተባበር የችግር እድሜ ያጥራል" ለማ መገርሳ

አቶ ለማ መገርሳን በቅርብ የሚያውቋቸው ውስጣዊ ስብእናቸው የጎላ መሆኑንን ይመሰክራሉ። ምስክርነታቸው ዛሬ እሳቸው አስኳሉን ሰብረው ሳይወጡ በፊትም ነው። ለዚሁ ይመስላል ኦህዴድን ሲመሩ በነበሩት ባልደረቦቻቸው በተደጋጋሚ ተገፍተው ነበር። በአንድ ወቅት የእነ ወይዘሮ አስቴር ማሞ ቡድን ክፉኛ በተጫናቸው ወቅት በሚኒ ባስ እየተመላለሱ የተመደቡበትን ስራ ይሰሩ ነበር።

” የእኛ ስልጣን ጥንቅር ይበል” በማለት አገርና ህዝብ እንደሚበልጡ ይፋ ካደረጉ በሁዋላ ህዝብ ” የለውጡ መሃንዲስ” በሚል ክብር ቢሰጣቸውም፣ እሳቸው ግን በበርካታ ውጣ ውረድ ውስጥ ያለፉና ብዙ ያልተነገረላቸው፣ እንዲነገርላቸው የማይፈልጉ፣ ፈረሃ አምላክ ያላቸው ብርቅ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ ስለመሆናቸው እኒሁ የቅርብ ሰዎች ይናገራሉ።

የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በቀጥታ እንዲተላለፍ በድፍረት የጠየቁትና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ወደ መሪነት ያመጡት አቶ ለማ፣ እርጋታቸውና አካሄዳቸውን በቅርብ የሚከታተሉ ” ፑቲን” እያሉዋቸውም ነው። መናገር ሳይሆን ተግባር ላይ መተኮር እንዳለበት አብዝተው የሚናገሩት ” ኢትዮጵያን ማዳን” የሚለው ትግል መሃንዲስ ለማ መገርሳ አንድ ቀን ሕዝብ ፊት በአደባባይ ምስጋናቸውን እንደሚወስዱ የቅርብ ባልደረቦቻቸው ያምናሉ።

የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ  በመስቀል አደባባዩ የቦምብ ፍንዳታ ጎዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተኝተው ህክምና በመከታተል ያሉ ዜጎችንም ከጎበኙ በሁዋላ ደም ለግሰዋል። ደም ከለገሱ በሁዋላ ለፋና የሚከተለውን ተናግረዋል።

በቦብም ጥቃቱ ጉዳት የተደረሰባቸው እና ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች ለፍቅር፣ ለሰላም እና ለአንድነት መሰዋእትነት የከፈሉ ናቸው።ይህን መሰል እኩይ ተግባር የሚፈጽሙ አካላት አለም ላይ ያሉ አሸባሪዎች ሳይሆኑ እኛው ውስጥ ያሉ መሆናቸው በእጅጉ የሚያሳዝን ነው ።የቦንቡ ፍንዳታ ጥቂት ግለሰቦችን ይጎዳል እንጂ የሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የለውጥ ፍላጉት ሊገታ አይችልም ፡፡

የተሻለችውን ኢትዮጵያ ማየት ሁላችንም እንመኛለን ። ግን ምኞት ብቻ ሳይሆን በትጋት መስራትን ይጠይቃል። ለዚህም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ነው። የተቃጣው ጥቃት የኋሊት የሚመልሰን ሳይሆን በእልህ እንድንሰራ የሚያደርገን ነው፤ ለውጥ ሁሉ ዋጋ ያስከፍላል ወደ ፊትም በአንድነት ተባብረን መቀጠል አለብን። ስንተባበር የችግር እድሜ ያጥራል። አንድነታችንን በጓዳ ሳይሆን በአደባባይ በመታገል የምንመኛትን ኢትዮጵያ መፍጠር ይጠበቅብናል።

የጥቁር አንበሳን የህክምና ባለሙያዎች ያመሰገኑት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ የሚመሩት ኦህዴድ ራሱን አጥርቶ ባለ ሃይሉ ለውጡ ተግባራዊ እንዲሆን፣ በክልሉ የቀደመውን አስተሳሰብ የሚናፍቁ ካድሬዎች የሚያካሂዱትን ማፈናቀል ለመግታት አበክሮ እየሰራ መሆኑንን መግለጹ ይታወሳል። የአማራ ክልልም ይህንኑ ዜና በማጠናከር በጥምረት እየተሰራ መሆኑን መዘገቡ ይታወሳል።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0