በአሜሪካ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር መገናኘታቸውን ማምሻው ላይ የኋይት ሃውስ ጽህፈት ቤታቸው ባወጣው አጭር መግለጫ አስታውቋል። በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ያለውን የተሃድሶ ጥረት እንደሚያደንቁ ሚስተር ፔንስ ተናግረዋል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ በትላንትናው ዕትም ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከምክትል ፕሬዚዳንት ፔንስ ጋር እንደሚገናኙ በዘገበ ወቅት ግንኙነቱ ወሳኝና ጠቃሚ እንደሆነ መጥቀሱ ይታወሳል። ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ዐቢይ “ሰብዓዊ መብቶችን በማክበር፣ የንግዱን ማኅበረሰብ ሁኔታ በማሻሻል እና ከኤርትራ ጋር ሰላም በመፍጠር ረገድ” እያካሄዱ ያሉትን ለውጥ በማድነቅ አገራቸው የተሃድሶ ለውጡን እንደምትደግፍ አረጋግጠዋል።

ከዚህ ሌላ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክርስቲን ላጋርድ ጋር ተገናኝተዋል። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ አይ ኤም ኤፍ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት በመግለጽ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከኤርትራ ጋር የደረሱት ስምምነት ለቀጣናው መረጋጋት በማምጣት አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚያደርግ ያለውን ዕምነት ገልጾዋል።

አይ ኤም ኤፍ በነጻ “የሚሰጠው ምሳ” እንደሌለ የሚታወቅ ሲሆን የምዕራባውያን ድርጅቶች አገልጋይ ሎሌ የነበረው ሟቹ መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን በነጻ ለዕርድ እንዳቀረበ ይታወሳል። በአስተሳሰብ፣ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በራዕይ፣ በአመለካከት፣ በባህርይና በኢትዮጵያዊነት ፍጹም ልዩ የሆኑትና ለውድድር በማይቀርብበት መልኩ እጅግ የላቁት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከሚከተሉት አገራዊ መርህ አኳያ ተመሳሳይ ተግባር እንደማይፈጽሙ ይታመናሉ።  (ፎቶዎቹ የተወሰዱት ከዕልፍኝ አስከልካዩ አቶ ፍጹም አረጋ የትዊተር ገጽ ነው)

ከአይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክርስቲን ላጋርድ ጋር 

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከአይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክርስቲን ላጋርድ ጋር


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ200 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *