ሰው በምንም ምክንያት መገደል የለበትም። በእምነቱ፣ በማንነቱ፣ በምንም መገደል የለበትም። እውነታው ግን ይህ አይደለም።

ኢትዮጵያውያን በማንነታቸው ሲገደሉ ኖረዋል። ለ27 አመታት! ገዳዩ ደግሞ ህወሓት ነው። ኢትዮጵያዊያን በተለይ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ…… ተለይተው ሲኮላሹ ኖረዋል። አማራው ላይ የደረሰው እጅግ የከፋ ነው። ሰው በማንነቱ ተለይቶ ተኮላሽቷል። በማንነቱ ምክንያት ዘሩን እንዳይተካ ተደርጓል። ይህ የቁም ሞት ነው!

ሰው በሀገሩ “መጤ” እየተባለ ተጨፍጭፏል። ተባሯል። ሀብትና ንብረቱን አጥቷል። በማንነት ተቧድነው የመጡት የትህነግ/ህወሓት ሰዎች ከተራ መስርያ ቤት ጀምሮ እስከ ዋናዎቹ ሕዝብን በማንነት አፈናቅለዋል! ዜጎች በማንነታቸው ታስረዋል፣ ተገድለዋል፣ ተኮላሽተዋል። በሺህ የሚቆጠሩ

በማንነታቸው ከንግድ ስራቸው፣ ከግብርና ተፈናቅለዋል፣ በምትኩ ትህነግና ደጋፊዎቹ ተተክለዋል። መርካቶንና 22ን ማሰብ ነው። ወልቃይትን ማሰብ ነው። ይህ ሁሉ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት የተደረገው በአጋጣሚ አይደለም፣ በፖሊሲ ነው። ይህ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ዜጎችን ብቻ አይደለም፣ ሀገርን አዘቅት ውስጥ ከትቷል። 88 ቢሊዮኑ የት ገባ፣ አባይ የት ደረሰ፣ የባቡር መንገዱስ ጉድ? አየር መንገዱ የገባበት እዳስ? በእየ እስር ቤቱ የተፈፀሙትስ?

አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ትህነግ የራሱን ሲያግብስ የቀሪዎቹን ሲደቁስ የመጣ ነው። በሁለት ሶስት ዜጎች ሞት የሚለካ አይደለም። ትወልድ ገድሏል። እየገደለ ያለው ግን የትግራይን ሕዝብንም ነው። እንዲያውም ከአሁኑ ከልተቀጨ መጭው ለትግራይ ህዝብ የከፋ ነው። ህዝብን ይወክልም አይወክልም ማዕከላዊ “እኛ ትግሬ፣ አንተ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ” እየተባለ ሲገረፍ የነበረ ሰው፣ በዚሁ መንገድ ከስራው፣ ከቀየው የተፈናቀለ የሞተበት ሰው አያቄምም? ሰው አይደለም የሞተበት? ይህ ግልፅ ነው!

የትግራይ ሕዝብ በትግሉ ዋጋ ከፍሏል። ሲሆን በልጆቻችን ደም መቀለድ የለብህም ብሎ ትህነግን መቃወም ነበረበት። ባይቃወም ትህነግ/ህወሓት በዜጎች ላይ የፈፀመው ወንጀል ሊያስፀይፈው ይገባል። መኮላሸትና ጭፍጨፋ ካስፀየፈው ደግሞ ቢያንስ ቢያንስ የትህነግ መነገጃ አይሆንም ነበር።

ሰው በአገዛዝ ቂም ይይዛል፣ ቁስሉ ያልጠገገው ብዙ ነው። ትህነግ ርቃኑን ሲቀር መሸፈን የሚፈልገው በሕዝብ ነው። መዳን የሚፈልገው “የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ነው” ሲል ነው። ከአሁን ቀደም አንድ ይሁን አይሁን ሌላ ነገር ነው። የትግራይ ሕዝብ መዳን ያለበት የትህነግን ርቃን ባለመሸፈን ብቻ ነው! በደም የተጨማለቀው ትህነግን ባለማቀፍ ነው! አንድ ነን ሲለው፣ አይደለንም በማለት ነበር።

ትህነግ ባለፉት 27 አመታት የሰራቸውን ጉዶች ከመቸውም ጊዜ በተሻለ አሁን እየሰማ ነው። በዚህ ወቅት ትህነግን የሚሸከም ከሆነ “በማንነት ማኮላሸቱ፣ መግደሉ፣ መዝረፉ፣ መግረፉ ትክክል ነበር” ማለቱ ነው። ይህን ትህነግ ዘርን መሰረት አድርጎ የፈፀመው ወንጀል ከምንም ከቆጠረ ለቀሪ ኢትዮጵያዊያን ምንም ርህራሄ አልተሰማውም፣ ወይንም ከዚህ ሁሉ ሰቆቃ እጁ በደም የጨቀየው ትህነግ ተሽሎታል ማለት ነው!

የትግራይ ህዝብ በመላ ኢትዮጵያ ተበትኖ ይኖራል፣ ትህነግ “የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ናቸው” ሲል ዝም ከማለት አልፎ ፣ “አንድ ነን” ሲባል ዝም ካለ ትህነግ ያቆሰለው ሕዝብ የትግራይ ሕዝብንና ትህነግን በምን መስፈርት ሊለይ ይችላል? አማራውና ኦሮሞው የትግራይን ሕዝብና ትህነግን አንድ ላይ አንመዝንም ሲል፣ ለምን አብሮ ለመመዘን የትህነግ መነገጃ ይሆናል?

ትህነግ የፖለቲካ ድርጅት ነው። ትህነግም ቢሆን ህጋዊ እንጅ ግድያ ሊፈፀምበት አይገባም። ግን ትህነግ የፖለቲካ ድርጅት እንደመሆኑ ትህነግ ላይ የሚወሰድ የተሳሳተም ይሁን እርምጃ ፖለቲካዊ ነው። የኦህዴድ አባላት፣ የብአዴን አባላት፣ የደኢህዴን አባላት ሕዝብን ስላስመረሩ በንብረታቸውና በራሳቸው ላይ ጥቃት ደርሷል። ይህ ጥቃት ፖለቲካዊ ነው። ፖለቲካዊም ቢሆን ሰው በምንም ምክንያት መገደል፣ ንብረቱ መውደም የለበትም! ግን የትህነግ አባል ሲሆን ነው የማንነት ጥቀት የሚሆነው?

እነ ዶክተር አብይን የትግራይ ሕዝብና ትህነግ የተለያዩ ናቸው ሲሉ እነ ደብረፅዮን ይህን ተቃውመው “አንድ ነን” ብለዋል። ሕዝብን መከታ አድርገው ለመዳን ነው። ለትህነግ የዶክተር አብይን ያህል ጠቃሚ ሰው አልነበረም። ዘርፈውም፣ ገድለውም በይቅርታ እንዲኖሩ ማድረግ ይችል ነበር። ከትህነግ በላይ ግን ለትግራይ ሕዝብ የዶክተር አብይን ያህል አዳኝ አልነበረም። ትህነግ የሰራውን በደል ከሕዝብ ነጥሎ አስቀምጧል። ሕዝብ ግን ወዶም ይሁን ተገዶ ወደ እነ ደብረፅዮን ወገን የሆነ ይመስላል።

እነ ደብረፅዮን ያቆሰሉትን ሕዝብ እንዳለ ያውቃሉ። ሊበቀላቸው የሚያስችል ቁስል እንዳለበት ያውቃሉ። ለዚህም በመላ ኢትዮጵያ በሚኖር የትግራይ ተወላጅ ደም ለመደበቅ ወስነዋል። አንድ ነን አሉ። ሕዝብን “እኔን በደለኝ ካልክ አብሮህ የሚኖረው የትግራይ ሰውም በድሎሃል” ብለው አቋም ያዙ። በአማራ ክልል የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ አይደሉም ተብሎ ሰልፍ ተወጥቷል። የትግራይ ሕዝብም ራሱ ለራሱ መመስከር ነበረበት። 27 አመት ሙሉ በደል የተፈፀመባቸው ከቀን ጅቦቹ ጋር አንመድብህም ሲሉት ገዳዮቹን ሰምቶ ከገዳዮቹ ጋር ነኝ ማለት አልነበረበትም!

ትህነግ የሰራውን ሰርቶ በሕዝብ ስር ሲወሸቅ ፖለቲካውን እየሰራ ነው። በማንነቱ ምክንያት ፊቱ ላይ ግንባሩን የተመታ ወንድሙን በስሜት የሚያስታውስ አለ፣ የተገረፈ፣ የተኮላሸ አለ። ስሜታዊ የሚያደርጉ ክስተቶች አሉ። ያኔ ኦሮሞው ክፉ ሰራ የሚለውን ኦህዴድ አባል ቢያገኝ አይምረውም፣ አማራው የብአዴን አባል ነው ያለውን አይምረውም፣ ትህነግ አንድ ነኝ ሲል “አዎ” ያለውንም የትግራይ ሰው ያጠቃዋል። ይህ ፖለቲካዊ እርምጃ፣ ከመበደል ከመገፋት የመጣ የተሳሳተ እርምጃ እንጅ የተለየ የብሔር ጥቃት አይደለም።

ትህነግ በደም መጨማለቁን ሕዝብ እየሰማ ነው። በእነ ደሙ “አንድ ነን” ሲል ህዝብ አይደለንም ማለት አለበት። ካልሆነ ግን እዳውን ለመሸከም ወስኗል ማለት ነው! ከኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ውስጥም “ይቅርታ” የጠየቁ አሉ። እንደ ግለሰብ የሚጠይቁ አሉ። እንደ መሪ እነ አብይ እየጠየቁ ነው። ትህነግ ያን ሁሉ ግፍ ግፍ አላለውም። ትህነግ የራሱ ጉዳይ ነው። የገዥው ፓርቲ አባላት ከፈፀሙት ወንጀል አንፃር የሚመጣባቸውን አውቀው ይቅርታ ሲጠይቁ የትግራይ ሕዝብ በደም የተጨማለቀውን ትህነግን የሚያቅፍ፣ አንድ ነን ሲለውም የሚስማማ ከሆነ ጥፋቱ የሕዝብ ወይንም ሕዝብን እንወክላለን የሚሉት አካላት ይሆናል።

ከምንም በላይ ግን ራሱ የሚናገረውን ቋንቋ የሚናገሩትና አንድ ማንነት የሚጋሩትንም አልዳኑም ብሎ፣ በደለውኛል ብሎ የሚያጠቃ ሕዝብ ከትህነግ ጋር አንድ ነኝ ያለን ግለሰብ የሚያጠቃ ከሆነ ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው። የዘር አይደለም። እንዲያውም የዘር የሚሆነው የትግራይ ሕዝብ ከትህነግ ጋር ያለው መተቃቀፍ ነው። ኦሮሞው ክፉው የኦህዴድ አባል ላይ ዘምቷል፣ አማራው ክፉው የብአዴን አባል ላይ ዘምቷል። ትግሬው ክፉው የትህነግ አባልና መሪን ከእነ ደሙ የሚያቅፍ ከሆነ ዘር ይመጣል። አማራው የብአዴኑን አባል፣ ኦሮሞው የኦህዴዱን አባል ብቻ ሳይሆን አማራው የኦህዴድ፣ ኦሮሞው የብአዴኑ አባል ላይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችለው ሁሉ አማራውና ኦሮሞው የትህነጉ አባል ላይም እንደ ግንዛቤውና ስሜቱ እርምጃ ሊወስድ ይችላል። የትግራይ ሕዝብ ስለ አማራና ኦሮሞ ወንድሙ ተጨንቆ ትህነግን ባይታገል እንኳ ትህነግ ከእነ ደሙ ሲያቅፈው ዝም ማለት የለበትም። ካልሆነ ግን ኦሮሞው ክፉ ያለውን የኦህዴንና ብአዴን አባል፣ አማራው ክፉ ያለውን የኦህዴድና ብአዴን አባል እንደጠላው፣ ክፉዎቹ የትህነግ መሪዎች አባሌ ነው ያለውን የትግራይ ሕዝብ ስሜታዊ በሆነና የትህነግን ስራ የሰራ ሲመስለው የተሳሳተም ቢሆን እርምጃ ቢወስድ መመዘኛው ዘር ሳይሆን ፖለቲካ ነው። ቀሪው ሕዝብ “ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ የተለያዩ ናቸው” ብሎ ነበር። ለዚህ መልስ ትህነግ የሰጠው መልስ አንድ ነን የሚል ነው። የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ አይደሉም ያለ ሕዝብ፣ ከትግራይ ሕዝብ አንድ አይደለንም የሚል አቋም ብቻ ሳይሆን ምስጋና ይገባ ነበር።

ሆኖም የትግራይ ሕዝብ እነ ደብረፅዮን በጅብላ አባል ሲያደርጉት ዝም ብሎ ለፖለቲካ ጥቃት ተዳርጓል። የትግራይ ሰው በመሆኑ በዘር ሳይሆን የትህነግ አባልነት የፖለቲካ ጥቃት ሰለባ ሆኗል። ጥቂቶች ላይ ይደርስ የነበረውን ብዙሃኑ ዝም ብሎ ተቀብሎታል። በዚህ መንገድ የሚፈፀም ጥቃት ካለ የዘር ሳይሆን የፖለቲካ ጥቃት ነው! ሕዝብ አንድ አይደለንም ቢል ጥቃት እንኳ ቢኖር የሚያሰጋው የትግራይ ሰው የሆነው ሁሉ ሳይሆን የትህነግ አባል፣ ከእነዚህም መካከል ክፉዎቹ ላይ ይሆን እንደነበር ጥርጥር የለውም!

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ለ27 አመት በፖሊሲ ታቅዶ በማንነታቸው ጥቃት የደረሰባቸው፣ በማንነታቸው ተለይተው የተኮላሹ፣ በማንነታቸው ተለይተው ትግራይ ውስጥ የታፈኑ ከ2000 በላይ ንፁሃን፣ አማራ ነን ስላሉ አለ የተባለ ወንጀል የሚፈፀምባቸው የወልቃይት፣ ራያና ሌላም አካባቢ ያሉ ዜጎች ጥቃት እንኳ ያለወገዘ አካል፣ ክፉው ትህነግ አንድ ነን እያለ፣ በሀዘን ወቅት መብራት አጥፍተዋል ተብለው ከዘር በተለየ የተጠቁ ዜጎችን ጉዳይ ሰማይ ማስነካት ከዚሁ ትህነግ ለመዳን ከትግራይ ሕዝብ ለመደበቅ የሚጠቀምበት ስልት ተለይቶ የሚታይ አይደለም።

*******************************************
እውነታው ሲገለጥ ይሄ ነው የትግራይ ተወላጆች በአማራ ተገደሉ የተባለው ፎቶ እውነት ነው?

የትግራይ ወያኔዎች በጣና በለስ ፐስኳር ፕሮጀት አካባቢ የተገደሉ የትግራይ ሰዎች ብለው በፌስቡ ፕሮፕጋንዳ እየሰሩበት ያለው የተሳሳት /FAKE/ የሆነና በናይጀርያ የተገደሉ ሰዎች ፎቶ ሲሆን በ Mon, Feb 12th, 2018 Fulani Herdsmen Kill Two Civil Defence Corps In Benue በሚል ርዕስ ከተጻፈ ከሚከተለው ዌብ ሳይት ነው፡፡

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *