ሰኔ 16፣ 2010 ዓ. ም. ለጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ በተጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በተሰነዘረው የቦንብ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

መስቀል አደባባይ በተዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የቦንብ ጥቃት ፈጽመዋል ተብለው ከተጠረጠሩት መካከል ደሳለኝ ተስፋዬ፣ አብዲሳ ቀነኒ፣ ህይወት ገዳ፣ ባህሩ ቶላ እና ጌቱ ግረማ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው ተብሏል።

በሰልፉ ላይ የታየው ክፍተት ምን ነበር?

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ በፎቶ

”በዛሬው ጥቃት ከመቶ ሰዎች በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ኮሚሽነር ግርማ ካሳ

ኢቢሲ የፖሊስ የምርመራ መዝገብን ጠቅሶ እንደዘገበው አንደኛ ተጠርጣሪ አብዲሳ ቀነኒ በዕለቱ በወንጀሉ ተጠርጥረው የህክምና ዕርዳታ እየተሰጣቸው የነበሩትን ሰዎች ለማስመለጥ ሙከራ አድርጓል ተብሎ ክስ ተመስርቶበታል። ሶስተኛው ተጠርጣሪ ጌቱ ግርማ ደግሞ የቦንብ ጥቃቱን በማስተባበር ወንጀል ነው የተጠረጠረው።

አራተኛ ተጠርጣሪ የሆነችው ህይወት ገዳ በዕለቱ የአእምሮ ህመምተኛ በመምሰል በወንጀሉ ተሳትፋለች የተባለ ሲሆን አሁንም በአማኑኤል ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለች መሆኑን የምርመራ ቡድኑ ገልጿል።

የምርመራ ቡድኑ ምርመራውን አጠናቆ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ አንዳስረከበ ኢቢሲ ዘግቧል።

አቃቢ ህግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ ለመመስረት 15 ቀን ይሰጠኝ ብሎ የጠየቀ ሲሆን ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ለአቃቢ ህግ ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም፤ የዋስትና መብታችን ይጠበቅ፤ በማረፊያ ቤት የሚያጋጥመንም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይቁም ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

“ያለፉት 27 ዓመታት ብዙ ቆሻሻ ነገሮች የተሰሩበት ዘመን ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

ጀዋር እና ዐብይ ምን ተባባሉ?

አቃቢ ህግ በበኩሉ ለተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት ሊፈቀድ አይገባም ሲል ተቃውሟል። ፖሊሲም ተጠርጣሪዎቹ ተፈጽሞብናል ያሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ትክክል አለመሆኑን ለዚህም የቪዲዮ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚችል አሳውቋል።

ፍርድ ቤቱ ሁለቱንም ወገን ካደመጠ በኋላ አቃቢ ህግ የጠየቀውን የክስ መመስረቻ የ15 ቀን ጊዜ ፈቅዷል። ከዚህ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎችም በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ አዟል።

ሌላው ተጠርጣሪ የብሄራዊ መረጃ ደህንነት መምሪያ አዛዥ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ የሶስት ተጠርጣሪዎች የምርመራ መዝገብ ጉዳይ የፊታችን ረቡዕ በችሎቱ ይቀርባል።

የስራ ክፍተት በመፍጠር የተጠረጠሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የነበሩት ግርማ ካሳን ጨምሮ ዘጠኝ የፌደራል ፖሊስ አባላትን በተመለከተ ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጠው ቀጠሮ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሚታይ ይሆናል በማለት የዘገበው ደግሞ ፋና ነው።

BBC Amharic

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *