ጎሳ ላይ ለተተከለ አስተሳሰብ ፍጹም ቦታ የሌላቸውና ዘረኝነትን በመቃወም ላለፉት አስርት ዓመታት በግንባር ቀደም ሲታገሉ የነበሩት አቶ ኦባንግ ሜቶ / ጥቁሩ ሰው አገራቸው ለመግባት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ታወቀ። ከጠቀላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተከታታይ ንግግር ካደረጉ በሁዋላ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል።

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን መሪ የሆኑት አቶ ኦባንግ ዘረኝነትን በመቃወምና ፍቅርን በመስበክ በኢትዮጵያ ደረጃ የመጀመሪያው ሰው መሆናቸውን ዜጎች የሚመሰክሩላቸው ናቸው። በባህሪያቸው እጅግ ሩሩህና ደግ መሆናቸው የሚነገርላቸው አቶ ኦባንግ፣ በኢትዮጵያ ቀደም ብለውየጀመሩትን ፍቅርን የመስበክ ስራ አጠናክረው ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአሜሪካ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር የተወያዩት አቶ ኦባንግ ወደ አገር ቤት እንደሚገቡ መወሰናቸውን፣ ይህም የሚሆነው እጅግ ቅርብ በሆነ ጊዜ እንደሆነ  ለዛጎል ተናግረዋል።

አቶ ኦባንግ በከፍተኛ ደረጃ የሚሰሩዋቸውን ጉዳዮች ብዙም መናገር የማይወዱ፣ ለወገኖቻቸው ቀደመው የሚደርሱ፣ ኢትዮጵያን በከፍተኛ ቦታዎች የሚወክሉ፣ በአሜሪካና በአውሮፓ ባለስልጣናት ዘንድ ይሁንታ ያላቸው፣ ግንኙነታቸው እጅግ ሰፊ የሆነና ለሰው ልጆች የሰብአዊ መብት መከበር የጸና አቋም ያላቸው ናቸው። በዚሁ እምነታቸው መነሻ የሚመሩት ድርጅት ” ከጎሰኝነት ይልቅ ቅድሚያ ለሰብአዊነት” በሚል መሪ ቃል የሚመራ ሲሆን ” ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ነጻ አይወጣም” መፈክር ላይ የተተከለ ነው።

አቶ ኦባንግ በቅርቡ ከወይዘሮ አቻላ ጋር ትዳር የመሰረቱ መሆናቸው ይታወሳል። ጋብቻቸውን አስመልክቶ በዋሽንግቶን በተካሄደ ዝግጅት ላይ በተለያዩ ሰዎች ከተሰጡ ምስክርነቶች ” ኦባንግ ሁላችንንም ተሸክሞ የኖረ” ስትል ዓለምጸሃይ ወዳጆ ኦባንግን ያየችበት መነጽር በርካቶችን አስደምሞ ነበር።

 
 
 

Related stories   በግለት ተጀምሮ የደበዘዘው የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ወዴት?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *