ከሳምንታት በፊት “ የአብዲሌ መጨረጫ መጀመሪያ ” በሚል ርዕስ እንደተጠቆመው የሶማሌ ክልል መሪ እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ከጀርባቸው ሆነው ለዚህ ዓይነት የለየለት እርኩስ ተጋባር የዳረጉቸው ጭምር በከፈተኛ ወንጀል እንደሚክሰሱ ተሰማ። አብዲ ኢሌ አስፈላጊውን ሁሉ መረጃ ዘርግፈዋል።
የዛጎል ምንጭ እንዳሉት አብዲሌ ይቅርታ እንደማይደረግላቸው በመገመት ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ በግፊት ወደ አልተፈለገ ጉዳይ መግባታቸውን ለመናገር ጊዜ አላባከኑም። በዚሁ መነሻ ነው የሚመሩትን ክልል ህዝብ ሰላሙን ጠብቆ እንዲቀመጥና ምንም የተፈጠረ ነገር እንደሌለ በቲቪ ቀርበው የተናገሩት።
አብዲ ኢሌ በሚመሯት ሶማሊያ ክልል እጅግ ፈርጣማ የሆነ የልዩ ሃይል ለምን እንዲቋቋም ተደረገ? የሚለው ጥያቄ መነጋገሪያ የሆነው ዛሬ አይደለም። ኦሮሚያ የገነባው የፈጥኖ ፖሊስ እንዲበተንና ትጥቅ እንዲፈታ ሲደረግ የሶማሊ ክልል ልዩ ሃይል ግን እንደ አንቁላል እንክብካቤ ሲደረግለት መቆየቱ ብቻ ሳይሆን፣ በአብዲ ኢሌ ትዕዛዝ ያሻውን ሲያደርግ ሃይ የሚለው አካል መጥፋቱ በርካታ ቅሬታና ስጋት እንደፈጠረባቸው በርካቶች ሲወተውቱ ቆይተዋል።
ይፋ ባይገለጽም በዛሬው እለት አብዲ ኢሌ የክልሉን ምክር ቤት ጠርተው ካጸደቁ በሁዋላ መገንጠልን ለማወጅ በዝግጅት ላይ እንዳሉ በማለዳ የመከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር አድርጓቸዋል። ይህንኑ ድንገተኛ እርምጃ ተከትሎ ዝርፊያ፣ የሌሎች ብሄረሰብ አባላት ላይ ያነጣጠረ ጥቃትና ንብረት የማውደም አሳዛኝ ድርጊት መከናወኑንን የተለያዩ ይፋዊ መገናኛዎችና ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
“ለሦስት ዓመታት በእስር በቆየሁባቸው ጊዜያት በፍጹም ጭለማ ውስጥ ለብቻዬ ታስሬ ነበር፤ ማታ ሲሆን ሊያሰቃዩኝ  ያወጡኝ ነበር፤ (የእስር ቤት ኃላፊዎች) ብዙ ነገሮችን ፈጽመውብኛል፤ የብልቴን የዘር ከረጢት በኤሌክትሪክ አቃጥለውኛል፤ በሽቦ ካሰሩኝ በኋላ በላስቲክ ውስጥ በርበሬ (ሚጥሚጣ) በራሴ ላይ አድርገው (አፍነውኛል)፣ በጣም እንዳልጮህ አፌን አስረውታል፤ ቀን ቀን በጣም ትንሽ ምግብ ይሰጡኛል፤ አንድ ዳቦና አንዳንዴ ጥቂት ወጥ ያለበት፤ በዚሁ ኦጋዴን እስር ቤት የነበረችውን ሚስቴን አስገድደው ደፍረዋታል፤ የኔ ያልሆነ ልጅም እዚያው ወልዳለች”።  ሙሉውን የሰቆቃ ሪፖርት እዚህ ላይ ያንብቡ
የፌደራል መንግስት ወደዚህ እርምጃ ከመሄዱ በፊት በሽምግልና፣ በክልል ክልል ስምምነት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአካል በመገኘት ችግሩ እንዲፈታ ጥረት ማድረጋቸው ይታወሳል። በትናንትናው እለት አብዲ ኢሌ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ተጠይቀው አሻፈረኝ ማለታቸውን የሚገልጽወገኖች አብዲ ኢሌ ከጀርባ ሆኖ በሚመሩዋቸው አማካይነት ክልሉን እንዲገነጥሉ ምክር ተለግሷቸዋል።
በመንግስት በገሃድ ባይገለጽም ከአብዲ ኢሌ ጋር የተጠቀሰውን ምክር ጨምሮ የተለያዩ ውይይቶች ሲደረጉ ድምጽ ተያዟል። በዚሁ መሰረት አብዲ የሶማሌ ክልልን ከኢትዮጵያ የሚለየውን ውሳኔ ለማስወሰን መዶለታቸው በመታወቁ የአገር መከላከያ ሰራዊት ርምጃ እንደ ወሰደ ለክልሉ ቅርብ የሆኑ መገናኛዎች ይፋ አድርገዋል።
በዚሁ ወቅት ይህ አቶ መለስ አደራጁት የሚባለው ሃይል ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ለመዋጋት ሙከራ ማድረጉ ተሰምቷል። የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ጽህፈት ቤትም በህጋዊ ት=የፌስ ቡክ ገጽ ” ኩዴታ ተደረገብኝ” ሲል ህዝብ ከአብዲ ኢሌ ጎን እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።
በክልሉ ይፋ የሆነው የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈር መልቀቁን፣ እጅግ አሳፋሪና አሰቃቂ ወንጀል በዜጎች ላይ እንደሚፈጸም፣ ሲቶች እህቶች ላይ የሚደርሰው ኢሳብአዊ በደልና ወንጀል ሙሉ ተዘርዝሮ ይፋ ከሆነ በሁዋላ ስጋት ላይ የወደቁት አብዲ ኢሌ፣ በራሳቸው ሚዲያ ቀርበው ወንጀል ሲያሰሩዋቸው የነበሩት የቀድሞው የደህንነት ሚኒስትሩ መሆናቸውን በመናገር ንስሃ ሊገቡ ቢሞክሩም ” ይህን ማለታቸው ከተጠያቂነት አይድናቸውም” ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች በዓለም አቀፍ የወንጀል ህግ እንደሚጠይቃቸው ማስታወቁ የፈጠረው ስጋት ቀላል አልነበረም።
ከዚሁ የከፋ ተግባራቸው ጋር በተያያዘ በውስጥ የተነሳባቸው ተቃውሞ መካረሩ፣ የኦሮሚያን ክልል አልፈው እየገቡ የሚፈጥሩት ትንኮሳና ሁከት፣ ንጽሃንን ህገ መንግስቱ በማይፈቅደው መልኩ እንዲፈናቀሉና በሰላም ሰርተው እንዳይኖሩ ማድረጋቸው የፈጠረባቸውን ቀውስ ወደየትም አገር ሄደው ማምለጥ ስለማያስችላቸው ክልሉን ገንጥለው ለተወሰነ ጊዜ ለመንፈራገጥ አቅደው እንደነበር ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

 

Related stories   ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ህልማቸው አይሳካም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አዲስ ስታንዳርድ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳስነበበው፣ ከላይ እንደተገለጸው ሳይታሰብ ክልልሉን በራሳቸው ፍላጎት ገንጥለው ከስጋት የሚድኑበትን መንገድ ለማደላደል ያደረጉት ሙከራ ከሽፏል። ይህ ከሆነ በሁዋላ ከአንዲት የዛፍ ጥላ ስር ሆነው በቪዲዮ በተደገፈ ንግግር የክልሉ ህዝብ በተለይም ደጋፊዎቻቸው እንዲረጋጉ ሲማጸኑ ታይተዋል።

ይህንኑ ተከትሎም የመከላከያ ሰራዊት ከክልሉ እየተነሳ ወደ ሌላ ክልል ሲዛመትና ሲበተን የነብረውን አመጽ የሚታገስበት ጊዜ በማብቃቱ ባገሪቱ ህግ መሰረት እርምጃ እንደሚወስድ ይፋ አድርጓል። የአገር መከላከያ ህግና ህገመንግስትን በማክበር የፈጸመውን ግዳጅ በመቃወም የትግራይ ክልል ቀዳሚ ሆኗል።

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ #ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ by Mengistu D. Assefa


በሶማሌ ክልል የተፈጠረው ግጭት ወደ ከፋ ሁከት እና ብጥብጥ ሊገባ የሚችል ተግባር ስለሆነ ጉዳዩ በእስቸኳይ ቁጥጥር ሥር እንዲውል እና የሕግ የበላይነት እንዲከር የትግራይ ክልል መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።

ምንም ዓይነት ችግር ቢፈጥር በሕጋዊ እና ኃላፊነት በተሞላ አግባብ እንጅ በኃይል ለመፍታት መውደድ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና ለፌዴራላዊ ሥርዓታችን መፍረስ አደጋ በመሆኑ በፍጥነት መቆም አለበት።

የፌዴራል መንግሥት እና የሶማሌ ክልል መንግሥት በአሁ ሰዓት በክልሉ የተፈጠረውን ችግር በተረጋጋ እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት በሚያረጋግጥ መልኩ ሊፈቱት ይገባል።ይህ አካሄድ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓታችንን በመሸራረፍ እና አደጋ ላይ የሚጥል በመሁኑ ውሎ ሳያድር እንዲታረም የትግራይ ክልል መንግሥት በጥብቅ ያሳስባል።

በዚህ አጋጠሚ በዚህ ግጭት በጠፋው የሰው ሕይወት እና በወደመው ንብረት መሪር ኃዘን የተሰማን መሆኑን እየገለፅን፣ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች እንዲሁም ለመላው የሶማሌ ክልል ፅናትን እንዲሰጣችሁ ለማለት እንወዳለን።የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕዝብ ግንኙንት ቢሮ

ሐምሌ 28 – ቀን 2010 ዓ/ም

መቀሌ

 

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

በክልሉ ቴሌቪዥን ቀርበው  ክልሉ ሰላም ስለሆነ ህብረተሰቡ እንዲረጋጋ በሶማሊኛ ቋንቋ መልዕክት ያስተላለፉ አብዴሌ፣ መግለጫ የሰጡበት ሁኔታ በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውን የሚይሳብቅ እንደሆነ አስተያየት አለ። የኦሮሚያ ቴሌቪሽን ያናገራቸው ሁለት የክልሉ የመብት ተሟጋቾች አብዴሌ ከ፺ በመቶ በላይ እስር ላይ ስለመሆናቸው መረጃዎቻቸውን ዋቢ አድርገው ሲናገሩ ተሰምቷል። ይህ ገና በማለዳ ሲሆን  ረፋዱ ላይ ግን አብዲሌ መያዛቸውና ካሁን በሁዋላ ምንም እንደማይፈይዱ ነው እየተነገረ ያለው። ይሁንና የትግራይ ክልል ከመግለጫ አልፎ የማገዝ ተግባር ላይ የሚሰለፍ ከሆነ ጉዳዩን ውስብስብና የተካረረ እንደሚያደርገው ፍርሃቻ አለ።

የአገር መከላከያ ሰራዊት በባድሜና ጾረና እንዲሁም በቡሬ ግንባር የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት ሰላም በመስፈኑና ኤርትራ ጦሯን በማስወጣቷ ከስፍራው ለማነቃነቅ መታቀዱ ህወሃትን እንዳሳሰበው፣ በድርጅት ደረጃም ይህንን የሚቃወም መግለጫ ማውጣኡን የሚጠቁሙ ክፍሎች፣ የትግራይ ክልል ከመግለጫ በዘለለ የሚያደርገው ነገር እንደሌለ ያምናሉ።

ኢትዮጵያ፣ ስማሊያና ኤርትራ በቅርቡ ወታደራዊ ስምምነት ማድርጋቸውን እግረ መንገዳቸውን የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች፣ ሌሎች ክልሎች የፈጠሩት ህብረት ህዝብ በማስተዋል ከደገፈው በአጭር ጊዜ ነገሮች እንደሚቀየሩ ይናገራሉ። እነዚሁ ክፍሎች እንደሚሉት ኢትዮጵያ አሁን አስተዋይነትን የምትሻበት ወቅት ነው። ይህንን ጊዜ ካለፈች ትሻገራለች።

የትግራይ ክልል ያወጣውን የህግ ተጣሰ ጉዳይ አስመልክቶ መልስ የሰጡ የሚከተለውን በማህበራዊ ገጾች ላይ አስፍረዋል።

የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ የሚገባበትን ሁኔታ የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 359/2003(95) ሲሆን በዚህ አዋጅ መሰረት የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ወሰኑ እስከ ምን ድረስ እንደሆነ በግልፅ ይደነግጋል፡፡

የፌደራል መንግሥት በክልሎች የሚፈፀሙ ህገመንግስታዊም ሆነ ሰብአዊ መብት ጥሰተቶች ሲያጋጥሙ ከሚወስዳቸው እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ዛሬ ያየነው የመከላከያ ሰራዊት ጣልቃ ገብነት አንዱ ነው፡፡ “ከዚህ ቀጥሎ ሊወሰዱ የሚችሉ ተግባራትስ በምን አግባብ ወደ ህጋዊነት ሊመጡ ይችላሉ?” የሚለው የዚህ ፅሁፍ ዋናውና አንኳሩ ነጥብ ነው፡፡ “የመከላከያ ሰራዊት ጣልቃ ገብቶ ያረጋጋውን ሰላምና ደህንነት ለማን አስረክቦ ይወጣል?” የሚለውም ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ የሚዳኝ ይሆናል፡፡ ለክልሉ ፖሊስ ያስረክብ የሚባል ከሆነ ከከዚህ ቀደሙ የከፋ ቀውስ ሊያጋጥመን ይችላል፡፡ እንዲሁም “ክልሉንስ ማን ያስተዳድረው?” የሚለው ሌላው መታየት ያለበት ነጥብ ነው

በአዋጁ አንቀፅ 14(2)(ለ) ስር እንደተደነገገው የፌዴራሉ መንግሥት የክልሉን ምክር ቤትና የክልሉን ከፍተኛ የህግ አስፈፃሚ አካል በማገድ ለፌዴራል መንግስቱ ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የመወሰን ስልጣን አለው፡፡ ጊዜያዊ አስተዳደሩም ክልሉን በበላይነት ከመምራት ጀምሮ በስልጣን ላይ የነበሩ የአስተዳደር አካላትንና የፀጥታ ክፍል ኃላፊዎችን ለፍርድ እስከማቅረብ የሚደርስ ስልጣን የሚኖረው ይሆናል፡፡ ስለሆነም የዛሬው የመከላከያ ሰራዊት ተልዕኮ ግቡን መምታቱ ሲረጋገጥ በቀጣይ የሚደረገው ተግባር ክልሉን ለጊዜያዊ አስተዳደር የማስረከብ ጉዳይ ይሆናል ማለት ነው፡ ሲሉ አቶ ታደሰ ተክሌ የተባሉ አስተያየት ሰጪ ኢትዮቲንክታንክ በተሰኘው ድረ ገጽ ላይ አስፍረዋል።

ህገ መንግስቱ ….. ልጅ ግሩም  የቀድሞ የጋንቤላ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ መለስ ዜናዊ ውሳኔ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ግድያ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማታቸው እሳቸውን ለማሰር ሲሉ አምልጠው በስደት ይኖሩ ነበረ። ከብዙ አመት ስደት በኋላ ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው እጅና እግራቸውን ታስረው ወደ ኢትዮጵያ ተወስደው ጨለማ ክፍል መታሰራቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። የጋንቤላ ፕሬዝዳንትን ያሰሩና የገረፉት ህዋሃቶች በጊዜው የፌዴራል መንግስትን ይመሩ ነበረ። የአንድ ክልል ፕሬዝዳንት ሲያስሩ ግን ህገ መንግስቱ ስለመጣሱ የተነሳ ነገር አለነበረም። 
አሁን አብዲ ኤሊ ሲታሰር (ለዚያውም በሰራው ወንጀል) ትግራይ ጥግ መሽገው ስለ ህገ መንግስት መከበር መናገር ምን ይባላል………?

ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ

አገራችን ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሆነች ይታወቃል። ለውጡም መላ የኢትየጵያ ህዝቦችን ባሳተፈ እና ባለቤት ባደረገ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል። እየተካሄደ ካለው የለውጥ እንቅስቃሴም መላው የአገራችን ህዝቦች ተጠቃሚ በመሆናቸው ተሳትፏቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ።

ሆኖም በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች አልፎ አልፎ የብጥብጥና የሁከት ድርጊቶች ይስተዋላሉ። እነዚህ ህገወጥ ድርጊቶች በሚስተዋሉባቸው አካባቢዎች የጸጥታ ሃይሉ ከህዝቡ ጋር ሆኖ የማረጋጋት ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው ብጥብጥ፣ ቀጥሎም ወደ ሌሎች አንዳንድ የክልሉ ከተሞች የተዛመተው ሁከት በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በፍጥነት ሊገታ እና ሊታረም የሚገባው ድርጊት ነው።
የአገር መከላከያ ሠራዊታችን ከሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን የተከሰተውን ሁከት በቅርበት ሲከታተል፣ ሁኔታውን ለመቆጣጠርና ህብረተሰቡን ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ የነበረ ቢሆንም ብጥብጡ በተፈለገው ፍጥነት ሊቆም አልቻለም።
በመሆኑም በክልሉ የህዝቦቻችን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ውስጥ እየገባ ያለበት ሁኔታ በመፈጠሩ የመከላከያ ሃይላችን ሁከትና ብጥብጡን በዝምታ የማይመለከት መሆኑንና የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ ያሳስባል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር
ሃምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም.

Share and Enjoy !

Shares

2 Comments

    1. Author

      በእርጎ መተጫ ቅል ላይ የሚደረግ፣ ህጻን ሆነን ገጠር ውስጥ ስንትዘል ማዘያው ላይ የሚደረግ ማስዋቢያ፣ ከባህር እንደሚገኝ ሼል ቅርጽ ያለው ውብ ነገር ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *