“Our true nationality is mankind.”H.G.

ዋይታ በሶማሌ ክልል – ህወሃት በይፋ ሚናውን ለየ!! "እኛ ካልመራን" አገር ትውደም !!

” መውጪያ ብቻ፣ አስወጡን… ነብሰ ጡሮች፣ አራሶች፣ ህክምና የሚሹ ወገኖች፣ ህጻናት፣ አረጋዊያን፣ እናቶች፣…. በቃ ሁሉም ዓይነት ዜጎች በጣር ውስጥ ናቸው። ጥይት፣ ጠኔ፣ የሞት ጥላ፣ የጅምላ ጭፍጨፋ ከቧቸው ዋይዋይ ይላሉ። አውሬዎች ” በለው” እያሉ ያዛሉ። ” አሁን አብዲሌን አናግሬዋለሁ። የፌደራል ፖሊስ ከጂግጅጋ እንዲባረር አድርገናል። የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ተቆጣጥሯል እያሉ በደም አበላ ሰክረው ይደንሳሉ። የማይገባቸው ጀንፈሎች እርስ በርስ ይነታረካሉ። አይናቸው መካከል እብሌኑ ውስጥ ድራማው በደም ተነክሮ እያዩትም እርስ በርስ …. ሰከን ብለው የሚያስቡ የሚሉት ነው።

” እርስ በርስ ስንባላ፣ ወንድም ወንድሙን ሲጠልፈው መኖራችን ከውርደት ውጪ ያተረፈልን ነገር የለም  ሲሉ አቶ ለማ እንደተናገሩት ዛሬ በሶማሌ ክልል ወገን እየረገፈ፣ አገር በውክልና እየፈረሰ፣ በቁማችን አውሬዎች ሲማማሉበን እንዴት ሊገባን እንደማይችል አይገባኝም” ሲል አስተያየቱ የሚሰጠው ጸጋዬ ባዩ የጅግጅጋ ነዋሪ ነው።

በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ ያስከፋቸው ወገኖች አልመውና አቅደው ሲንቀሳቀሱ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በለውጡ የደስታ ስካር የተነሳ ማስተዋላቸው መሰረቁ አሳሳቢ እንደሆነ የተጠቆመው ጸጋዬ ፣ ኢትዮጵያን እንወዳለን የሚሉ ወገኖች በዚህ የስካር መንገድ ከቀጠሉ ገና ብዙ ዋጋ ሰለመከፈሉ አይጠራጠርም። በሶማሌ የኢትዮጵያዊያን ዋይታ መልኩን እንዳይቀይር ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑና የመከላከያ ሰራዊት ከመግለጫ የዘለለ እርምጃ አለመውሰዱ ብስጭት መፈጠሩ እንዳለ ሆኖ፣ አንዳንድ ወገኖች መከላከያ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሆነ መደመጡ ሌላ ተስፋ መሆኑን የሚጠቁሙ ወገኖች ሁሉም ነገር ጥንቃቄ ያሻዋል ባይ ናቸው።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

በኢትዮ ኤርትራ ድንበር የፈሰሰው ሰራዊት እንኳን የሶማሌ ክልልን ድፍን ኢትዮጵያን ሊታደግ  እንደሚችል ለዛጎል የጠቆሙ እንደሚሉት ጨዋታው ከአብዲ ኢሌ ጋር ባቻ አለመሆኑ ጉዳዩን አወሳስቦታል። አብዲ አስፈላጊ የሚባለውን መረጃ ሙሉ በሙሉ የሰጠ ቢሆንም፣ በክልሉ በልዩ ፖሊስ ስም የተደረጀው ሃያ ሺህ የሚጠጋ ሃይል የሚታዘዘው በሌሎች ወገኖች መሆኑ፣ መከላከያ ዘሎ እርምጃ እንዲወስድ ቢታዘዝ የሚከፈለው ዋጋ እጅግ የከፋ እንዳይሆን ስጋት አለ።

Related stories   እስራኤል አልጃዚራ ቴሊቪዥን፣ አሶሲየትድ ፕሬስና ሌሎች ሚዲያዎች የሚጠቀሙበትን ህንጻ አወደመች

ይህ እስከ አፍንጫው የታጠቀና ከጀርባው አይዞህ ባይ ያለው ሰራዊት በቀላል ዋጋ ወደ ሰላም የሚመጣበት አግባብ እስኪፈለግ ጊዜ መፍጀቱ አይቀሬ መሆኑንንም ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ይናገራሉ። ይሁን እንጂ በክልሉ ያለው ጉዳይ በቅርቡ እንደሚቋጭ እመነታቸው የጸና ነው።

በጅግጅጋና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች የደረሰው ስብዓዊ ቀውስ እጅግ አሳዛኝና ምን ግዜም የማይረሳ መሆኑንን የሚናገሩ የአይን ምስክሮች በጅግጅጋ ያለው ሁኔታ የሚያስደስታቸው ወገኖች ለፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ እንዲህ ባለው ድርጊት ውስጥ መሳተፋቸው አስገርሟቸዋል። በተለይም በማህበራዊ ገጾች የፌደራል መንግስት ጣልቃ መግባት የለበትም በሚል ጽንፍ ወጥተው የሚክራከሩ ክፍሎች ላይ የማይረሳ ጥቁር ነጥብ መያዛቸውን እየገለጹ ነው።

በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ክልሉን ጥለው እንዳይወጡ በታገቱበት፣ እመጫት ሶስት ቀን ያልጸና ልጇን ይዛ ሜዳ በወደቀችበት፣ ነብሰ ጡር እህቶች ሁለት ነብስ ሆነው በጅምላ በተጣሉበት፣ ቤተ እምነቶች ሲጋዩ፣ የሰው ልጅ እትብቱ በተቀበረበት ምድሩ ላይ ጠኔ ሲጥለው እያዩ የማይራሩ ወገኖች፣ ቀኑ ሲደርስ እንዴት ሌላውን ርህራሄ ይለምኑት ይሆን!! ይህ ቀኑን ቆጥሮ መልስ የሚያገኝ ቢሆንም እንዲህ ያለ ጭካኔ በተራ ዜጋ ላይ አድሞና ወጥኖ ማቀናበር በየትኛውም መስፈርት ሰዋዊ ተግባር ሆኖ አይወሰድም። እኒህ ክፍሎች በሌሎች ወገኖች ላይ እዚህ የጭካኔ ጥግ ወረደው ክፉ ተግባር መፈጸማቸው ተላላኪ ፖለቲከኞች ያጎናጸፉዋቸው ሃይል መሆኑ ደግሞ እጅግ ያማል።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

የሕዝብ ስቃይ መላ እንዲባል፣ የታገቱ ዜጎች ቢያንስ ክልሉን ለቀው እንዲወጡ እንዲመቻች ማድረግ ካልተቻለ፣ ለዓለም አቀፍ ተቋማት ይህንኑ እንዲፈጽሙ ባስቸኳይ ማሳወቅ!! ከዚያም ኦብነግን ጨምሮ የውክልና ጦርነት የሚያካሂዱትን ክፍሎች ይፋ አድርጎ አገር ወዳዶች አገራቸውን እንዲታደጉ የዚያድባሬን ወረራ እንደመከትነው ሁሉ ክትት ይታወጅ!! ሰልጥነን፣ ታጥቀን፣ ጊዜው ሲደርስ …

በመጨረሻ እንደተሰማው መከላከያ ወደ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በመግባት ላይ ነው!!
 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0