“Our true nationality is mankind.”H.G.

በድሬደዋ ባለ ስልጣናት ታስረዋል የሚፈለጉም አሉ፤ የጅግጅጋ ተፈናቆይች እና ጅቡቲ ያሉ ኢትዮጵያውያን እጣ

SANYO DIGITAL CAMERA

ድሬዳዋው ዉስጥ የሰዉ ሕይወት ያጠፋዉን ግጭት እና ጠብ ቀስቅሰዋል በሚል ጥርጣሬ ከተያዙ ሰዎች መካከል የከተማይቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት  እንደሚገኙበት ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች አስታወቁ። ከተያዙት መካከል የክልሉ የፀጥታ ሃላፊ እና የቀድሞ ባለሥልጣናት ይገኙበታል ነው የሚባለው። የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ግን በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ባይክዱም ማንነታቸው እና ብዛታቸው ግን የሚካሄድባቸው ምርመራ ከተጠናቀቀ በኋላ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።


በድሬዳዋ አስተዳደር 09 ቀበሌ ባለፈው እሁድ በደረሰው ግጭት እና ሑከት በትንሽ ግምት 10 ሰዉ መገደሉ ተዘግቧል።ሁከት እና ረብሻዉን ቀስቅሰዋል ወይም አባብሰዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ ሰዎች  በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ከሚሽን ሰሞኑን አስታውቋል። ፖሊስ የተያዙትን ሰዎች ማንነት እና ቁጥራቸውን ግን አልገለጸም። ይሁን እና  በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የክልሉን የፀጥታ ሃላፊ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይገኙበታል ሲሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች እየተናገሩ ነው። ሻለቃ አሊ ሰመሪ ሲገዱÄthiopien Dire Dawa City (DW/Y. Gebreegziabher)

የተቃዋሚው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር የኦብነግ እና የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጥምረት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ናቸዉ። ሻለቃዉ አለኝ ባሉት መረጃ መሠረት ከቀድሞ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ አብዲ መሀመድ ዑመር ጋር ቅርበት ያላቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ሃላፊዎች እንደታሰሩ ተናግረዋል። እንደ ሻለቃ አሊ ከመካከላቸው የክልሉ የፀጥታ ሃላፊ ይገኙበታል። 
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዋና ሳጂን ባንተ ዓለም ግርማ ግጭት በመቀስቀስ የተጠረጠሩ ሰዎች መታሰራቸውን ተናግረዋል። ሆኖም ማንነታቸውን እና ቁጥራቸውን ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል።
በሻለቃ አሊ እምነት የድሬዳዋውም ሆነ የሶማሌ ክልሉ ሁከት እና ረብሻ መነሻ ምክንያት አንድ ነው። ችግሩም የተያያዘ ነው በርሳቸው አባባል።
ዋና ሳጂን ባንተ ዓለም ግን የሶማሌ ክልሉ ግጭት እና የድሬዳዋ ሁከት ግንኙነት አለው የለውም የሚለው ከምርመራው በኋላ ይፋ የሚደረግ ይሆናል ብለዋል። 
ሳጂን ባንተ ዓለም አያይዘውም ድሬዳዋን ለማረጋጋት ፖሊስ እና ህብረተሰቡ በጋራ እይተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል። ወጣቶች በተለይ ችግር ወደ ተፈጠረባቸው አካባቢዎች በረብሻ እና ሁከት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶች እንዳይገቡ እየተቆጣጠሩ መሆንን እና በረብሻው ምክንያት የተዘጉ መደብሮች እየተከፈቱ መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

የጅግጅጋ ተፈናቆይች እና ጅቡቲ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሮሮ

ሰዉ ወደ መኖሪያ አካባቢው መመለስ አልቻለም። መንገዱ በመዘጋቱ ቤት ንብረታቸው በመውደሙ እና በፀጥታ ስጋት ከተጠለሉበት ቦታ መውጣት ያልቻሉ ብዙ ናቸው ። በሌላ በኩል የሶማሌ ክልል እና የድሬዳዋው ግጭት ጅቡቲም ተሻግሮ እዚያ በሚገኙ ዜጎች ላይ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን ጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

የጅግጅጋ ተፈናቆይች ሮሮ

የሶማሌ ክልል ርዕሰ ከተማ ጅግጅጋ በንጽጽር  ሲታይ ዛሬ ፀጥታዋ የተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ነዋሪዎችዋ ተናገሩ። ይሁን እና በሰሞኑ ግጭት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ቤተክርስቲያን ዉስጥ የተጠለሉ ነዋሪዎች የሚባላም ሆነ የሚጠጣ ማግኘት እንደተቸገሩ ገልጸዋል። የከተማዋ ሱቆች በመዘረፋቸው እና በመዘጋታቸው ገንዘብ እያላቸው እንኳን ምግብ መግዛት እንዳልቻሉ አስረድተዋል። ከከተማዋ የሚያስወጡ እና ወደ ከተማዋ የሚያስገቡ መንገዶች መዘጋታቸው የምግብ ችግሩን እንዳባባሰው በቤታቸው ሰዎችን ያስጠለሉ ነዋሬ ገልጸዋል። በሌላ በኩል የሶማሌ ክልል እና የድሬዳዋው ግጭት ወደ ጎረቤት ጅቡቲም ተሻግሮ እዚያ በሚገኙ ዜጎች ላይ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን ጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለዶቼቬለ ተናግረዋል። 
ባለፈው ቅዳሜ ጅግጅጋ ውስጥ በተፈፀመው ጥቃት ከተፈናቀሉት መካከል የባጃጅ ታክሲ አገልግሎት የሚሰጥ እና በዚሁ ስራ የሚተዳደረው የ35 ወጣት አንዱ ነው። ተወልዶ ባደገባት እና በሚኖርባት ከተማ «አይቼው የማላውቀው ነገር»ነው የደረሰው ይላል። ቅዳሜ እለት አይኑ እያየ ባጃጁ ተወሰዶበት ሌሎች ንብረቶቹም ተዘርፈውበት ቀበሌ 06 በሚገኘው ሚካኤል ቤተ

Äthiopien Stadt Jijiga (DW/T. Waldyes)

ክርስቲያን ተጠልሎ ይገኛል። ዛሬ አምስተኛ ቀኑ። በርሱ አባባል በቤተ ክርስቲያኑ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይገኛሉ። ምግብም ሆነ ውሐ ማግኘት ተቸግረዋል።  
 45 ሰዎች አስጠግተው በመርዳት ላይ የሚገኙት አንድ  የጅግጅጋ ነዋሪም የምግብ ችግር እንዳለ ይናገራሉ። ላስጠጓቸው ሰዎች ምግብ የሚሰጡት ከዚህ ቀደም ካስቀመጡት መሆኑን የገለጹት እኚሁ ነዋሪ ሱቆች እና መደብሮች አለመከፈታቸው ከበድ ያሉ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። 
ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የተጠለለው ወጣት እንደሚለው መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደ ክልሉ ከገቡ በኋላ በንጽጽር ሲታይ ጂግጅጋ የተሻለ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። መከላከያ ከገባ በኋላም አንዳንድ ለውጦች አሉ። 
ሆኖም ሰዉ ወደ መኖሪያ አካባቢው መመለስ አልቻለም። መንገዱ በመዘጋቱ ቤት ንብረታቸው በመውደሙ እና በፀጥታ ስጋት ከተጠለሉበት ቦታ መውጣት ያልቻሉ ብዙ ናቸው ።
በሌላ በኩል የሶማሌ ክልል እና የድሬዳዋው ግጭት ጅቡቲም ተሻግሮ እዚያ በሚገኙ ዜጎች ላይ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን ጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
የጂግጅጋ ነዋሪዎችም ሆኑ ጅቡቲ የሚገኙ ዜጎች መንግሥት ከሚገኙበት ችግር እንዲያወጣቸው ተማጽነዋል።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

 

ዶቼቬሌ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0