“Our true nationality is mankind.”H.G.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከሳዑዲ አረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መከሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አደል ቢን አህመድ አል ጁበይር የሚመራውን ልዑክ ቡድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

አብይ ሳዑዲ.pngዶክተር አብይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር የተነጋገሩት በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ነው። ሁለቱ ሃገራት ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው መንገዶች ላይም መክረዋል።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እንደተናገሩት በሃገራቱ መካከል ዘመናትን የተሻገረውን የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዴት ይበልጥ ማሳደግ እንደሚቻልም ተነጋገረዋል።

ዶክተር አብይ በአደል ቢን አል ጁቤይር ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር በነበራቸው ቆይታ በሀገራቱ የኢንቨስትመንት ግንኙነት ላይም መክረዋል። በቱሪዝም መስክ ያላቸውን ትብብር ማሳደግም የውይይታቸው አካል ነበር።

F.B.C

0Shares
0