ሰሞኑንን አገር ተጨንቃ ከርማለች። ዶክተር አብይ ወደ መሪነት ከመጡበት ጊዜ አንስቶ የህዝብ ቀልብና ልብ የሳቡና በአገሪቱ ታሪክ በህዝብ ድምጽ ሳይመረጡ ” መሪያችን” የተባሉ መሆናቸው ነው የጭንቀቱ መነሻ። አብይ መሪ ከሆኑበት እለት ጀምሮ አርፈው አያውቁም። አገሪቱ የተነከረችበትን ጣጣ ለመጥረግ እላይ ታች ሲሉ ፊታቸው ገርጥቶ፣ አይናቸው ፈዞ፣ ሰውነታቸው ተዳክሞና ዝሎም ቢሆን አያርፉም። የዛኑ ያህል ቅር የተሰኙ እሳቸውን ለማጥፋት የሚሮጡ መኖራቸው ድብቅ አልነበረም። በዚሁ ስጋት መነሻ በሄዱበት መድረክ ሁሉ ስለደህንነታቸው መጠየቃቸውና መወያየት የተለመደ ሆኗል፣ በጓዳቸው የሚጸልዩላቸው ጥቂት አይደሉም።

ሕዝብ ድጋፉን ሊሰጣቸው ወዶና ፈቅዶ መስቀል አደባባይ በወጣበት ቀን እስካሁን ማንነታቸው በይፋ ያልተገለጸና ብህግ ወንጀለኛ ያልተባሉ ቦንብ በማፈንዳት ሊያጠፏቸው ሞከሩ። እሳቸው ግን ይህ ሳይበግራቸው የሳቸውን እጣ የተጎነጩትን ወገኖቻቸውን ቀድመው በመሮጥ ጎበኙ፣ ደም ሰጡ። ለውጥ አራማጅን እንጂ ለውጥን መግደል እንደማይቻል አጠንክረው ተናገሩ። ለአገር መሞት ክብር እንደሚሆናቸው በሙላት አወጁ። ነገር ሲሞት የማይገባቸው ሲሉ እሳቸውን በማስገደል ነገር ለመለወጥ የሚታትሩትን ወደ ፍቅር መንገድ እንዲመለሱ መከሩ። ተማጸኑ።

አብይ

ለአገር መሞት ክብር ነው!! መግደል ሽንፈት ነው!! የለውጥ አራማጅን እንጂ ለውጥን መግደል አይቻልም!!

ወደ አሜሪካ ሄደው አድካሚ ጉዞና እጅግ የሚያስደንቅ ተግባር ፈጽመው ስደተኛውን ፓትሪያርክ ይዘው አገር ቤት በደስታ ሲመለሱ በአውሮፕላን ውስጥ መቆየታቸውና ቶሎ እንዲወርዱ አለመደረጉ በርካቶች ከሰሞኑ መጥፋታቸው ጋር አያይዘውት ከርመዋል። በድካምና በእረፍት ማጣት ምክንያት ምን አልባትም ሃኪሞቻቸው ምክር ለግሰዋቸው አርፈው ሊሆን ይችላል የሚል ግምት የሰጡም ጥቂት አይደሉም። ምክንያቱም ተከታታይ ረዥም በረራዎች፣ስብሰባ፣ ጥያቄና መልስ፣ ሽምግልና፣ ውይይት፣ …. በወጉ እርፍት ስለጡ።

የተለያዩ ግምቶች ቢኖሩም ከግል ጠባቂዎቻቸው መካከል አንዱ ሸጣናዊ ሃሳብ አስቦ በሌሎች አጃቢዎቻቸው ጥረት መትረፋቸው ሚስጥር ሰማን ያሉ ቢያትቱም ሃተታው ወሃ የሚያነሳ አልሆነም። በእርግጥ አውሮፕላን ውስጥ ቢቆዩም ሲወርዱ መግለጫ መስጠታቸው በሰውነታቸው ላይ እክል ላለመድረሱ አመላካች በመሆኑ ወሬው ሚዛን የሚደፋ አልሆነም። ግን ብዥታው የእሳቸውን በሞገስ መመለስ ለሚጥብቁ ወገኖች የቀጥታ ስርጭት አንጻር አሉባልታ ሆኖ የሚጣል ግን አልነበረም።

” እሳቸው ስራ ላይ ናቸው” በሚል ጉዳዩን አቀዛቅዘው ያዩት እንዳሉት ከትናንት በስቲያ የውጭ አገር እንግዶችን ሲያስተናግዱና ወጣቶችን ለበጎ ፈቃድ ተግባር ሲያሰናብቱ መታየታቸው ለወዳጆቻቸው ሁሉ እረፍት የሰጠ ጉዳይ ሆነ። ያም ሆኖ ግን በጅግጅጋ በደረሰው አሰቃቂ ወንጀል እንደተለመደው በሚዲያ ቀርበው ምንም ዓለማለታቸው አሁንም ሃሳቡና ጭንቀቱን ግን አላራገፈውም።በዛሬው ቀን ከሳዑዲ ባለልጣኖች ጋር መገናኘታቸው ይበልጥ እርፍት የሰጠ ጉዳይ ሆነ። ከዜናው በላይ የሳቸው ደህንነት መሰማቱ ገነነ፤ ይህም ሆኖ ግን የወዳጆቻቸው ልብና ቀልብ ” መሪዬ የት ከረመ፣ ምን ሆኖ ነበር፣ ቢያንስ የጅግጅጋው ጉዳይ እረፍት የሚነሳው አይሆንም፣ ከጀርባ አንድ ነገር አለ” የሚለውን ጭንቀት ሊያስወግድ አልቻለም።

በኖርዌይ የሚኖሩ አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሰው ” ወንድማችን ውጭ አገር ህክምና ላይ እንደነበር ሰምቻለሁ” ሲሉ ይህን ካተምነው በሁዋላ ገልጽዋል። ምክንያቱንና መረጃውን እንዴት እንዳገናኙት ግን አላብራሩም።
አሁን መጨረሻ ላይ በጽህፈት ቤታቸው ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ስም የሚከተለው መረጃ ተሰራጭቷል። የአቶ ፍጹም አረጋ የፌስ ቡክ ገጽ ሌላ ቢሆንም መረጃውን ያሰራጨው ሰው ከሚሰጣቸው እጅግ ስሜት የሚሰርቁ ፍንጮች አንጻር መረጃውን እንደመረጃ አትመነዋል። መረጃው አብይ አህመድ ቦሌ እንዳረፉ ለምን ወዲያው ከአውሮፕላን አልወጡም በሚለው ጉዳይ ላይ የሚንተራስ ሲሆን በኦፊሳል ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ አልቀረበበትም። አንባቢያን መርምሩት

Fitsum Arega

በጣም ያሳዝናል ከአሜረካ ስንት ከሀገሩ ተሰዶ የሄደዉን ህዝብ አስታርቆ በድል ወደ ሀገሩ ሲገባ የጠበቀዉ የጀግና አቀባበል ሳይሆን ቦንብ ነበር ፡፡
በእለቱ እንደሚታወቀዉ ብዙዋቻችንም በ ሚዲያ እንዳየነዉ ከ ፓትሪያርኩ አቡነ መርቆሪዮስ ጋር በአንድ አዉሮፕላን እየተጫወቱ እየተወያዩ ነበር የመጡት ፡፡ ይሁን እንጂ አዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ሲደርሱ የደህንነት ሰዋች ጥርጣሬ ያድርባቸዉና ዉስጥ ሳይወጡ እንዲቆዩ ያደርጋሉ ፡፡ ሁላችንም በእለቱ በ ETV በቀጥታ እንደተመለከትነዉ አዉሮኘላኑ ቆሞ ለሰአታት ሳይወርዱ ቆይተዋል ፡፡

በመሀልም በ ETV ሰበር ብለዉ ሊያቀርቡት ብለዉ ከላይ በመጣ ትዕዛዝ ወዲያዉ ትተዉታል ፡፡ በዕለቱ ፖትሪያሪኩን ሊቀበሉ ከመጡ አንዲት መነኩሴ የሚመስሉ ሴት ቦንብ ይዘዉ መገኘታቸዉ ነበር ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነው፡፡ በእርግጥም ፖሊስ እያጣራዉ ያለ ነገር ቢሆንም ቦንቡ ለአብይ ይሁን ለጳጳሶቹ በዉል አልታወቀም ፡፡ በእርግጥ ስለ “መነኩሴዋ” የተባለ ነገር ባይኖርም ከሌላ ክፍለ ሀገር በ TRANSIT እንደገቡ ተረጋግጧል፡፡ ሴትየዋ ከተያዙ በኋላ በከፍተኛ ጥንቃቄ አብይ ወደ ዉስጥ እንዲገባ ተደርጓል ፡፡

ቀጥሎም ምንም እንኳን የጀግና ስራ ሰርቶ ቢመጣም በኢንጅነር ሞት ልቡ ተሰብሮ ነበር ፡፡ አዲስ አበባም እንደገባም ወደ ስመኘዉ ቤት የመሔድ እቅድ ነበረዉ። ይሄ ያልታሰበ ገጠመኝ ግን ከሁሉ ከለከለዉ ፡፡ በመሀል ካልሄድኩ እያለ ሲያስቸግር እነ ኦቦ ለማ እና ሚስቱ ልመና ነዉ የቀረዉ ፡፡ ያዉ ያልተሳካላቸዉ ዘረኞች እዛም እንደሚሄድ ገምተዉ በለቅሶ ቤት ሌላ ለቅሶ ቢፈጥሩስ፤ እና ይሄ ሳምንት ለዶክተር ከባድ ነበረ ይሄም ሳይረጋጋ በሶማሊ ክልል ደሞ ብዙ ሰዉ ተገደለ። ቤተክርስቲያናት ተቃጠሉ። ታዲያ አስቡት በምን አይነት ስብራት ዉስጥ እንደሚገኝ ???

ቢያንስ_ያላሰብነዉን_ነገር_ለ3_ወር ሙሉ ያሳየንን መሪያችን ሁላችንም ከጎንህ_ነን እንበለዉ!

ዘረኝነት_ይጥፋ 
ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም
ፍፁም_አረጋ_ነኝ_ፀረ_ዘረኛ

“ወዳጆቼ መነኩሴ የተባሉት ሴት በእርግጥ ምንኩስነታቸዉ አልተረጋገጠም ይሁን እንጂ በቦታዉ የነበሩት ሰዋች አብዛኛዎቹ ከቤተክርስቲያን ፓትሪያሪኩን እንዲቀበሉ የተመረጡ ስለነበሩና እኚህም ሴት በመሀል በመገኘታቸዉ የተነሳ ጥርጣሬ ነዉ ፡፡ የማንንም ሃይማኖት ለመንካት አይደለም “

abye - 1

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *