“Our true nationality is mankind.”H.G.

በጅግጀጋ እርዳታ ተጀመረ ኮማንድ ፓስት ተቋቋመ

 ከኢፌዴሪ መከላከያ ሃይል ከፌደራል ፖሊስ እና ከሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ።በዛሬው እለት የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም፣ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እና ሌሎች የፀጥታ ሃይል አዛዦች በተገኙበት በጂግጂጋ ከተማ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱም የፌደራልና የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ለክልል ሰላም በትብብር እና በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል።ዋና አዛዡ እንደተናገሩት የፀጥታ ሃይሎቹ ክልሉን ወደ ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ በመከላከያ ሰራዊት ዕዝ ስር ሆነው እንዲሰሩ ተወስኗል።የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ለክልሉ ሰላምና ደህንነት በጋራ የሚሰራ መሆኑንም ዋና አዛዡ ተናግረዋል።ዋና አዛዡ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሃይል ተፋጠዋል በሚል የተሰራጨው ወሬ የሃሰትና ውዥንብር ለመፍጠር የታሰበ መሆኑንም ገልጸዋል።

በጂግጂጋ ከተማ በደቡብ ምስራቅ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለተጠለሉ ዜጎች የዕለት ደራሽ እርዳታ መከፋፈል ጀመረ

በጂግጂጋ ከተማ በደቡብ ምስራቅ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የዕለት ደራሽ እርዳታ መከፋፈል ጀመረ።የዕለት ደራሽ እርዳታው ዛሬ ከዕኩለ ቀን ጀምሮ እየተከፋፈለ መሆኑን በስፍራው የሚገኘው ባልደረባችን መታዘብ ችሏል።እርዳታው ባለፉት ቀናት በከተማዋ በተፈጠረው ሁከት ምክንያት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በማሰልጠኛ ጣቢያው ለተጠለሉ ዜጎች ነው እየተከፋፈለ ያለው። በዚህም ለተወሰኑ ቀናት የሚያገለግል ሩዝ፣ የምግብ ዘይትና አልሚ ምግብ እየተከፋፈለ ይገኛል።
በማሰልጠኛ ጣቢያው በሁከቱ ምክንያት የተፈናቀሉ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በመከላከያ ሃይል ጥበቃ ስር ተጠልለው ይገኛሉ። በአንጻሩ በከተማዋ በሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ዜጎች እርዳታ አልቀረበላቸውም።
በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ህጻናትና አረጋውያንን ጨምሮ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በዛፎች፣ በፀሎት ቦታዎች እና በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጠልለዋል።
FBC NEWS

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ፋኦ በትግራይ ክልል ለአርሶ አደሮች የእህል ዝርያዎችን ማሰራጨትና እንስሳቶችን መከተብ ጀመረ
0Shares
0