“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኦህዴድ ፓርቲ እንደሚሆን ይፋ ሆነ፤ ከኢህአዴግ አባልነቱ አይለቅም

“ Roorroo Miidhaa Keenyaa…” የሚለው መዝሙር ባለፉት ስርዓቶች የነበረዉን ጭቆናና ግፍ ብቻ አጉልቶ የሚያሳይ፣ ብሩህ ተስፋ እና መነቃቃትን ከመፍጠር አኳያ ክፍትቶች ያሉበት በመሆኑ በአዲስ መዝሙር የሚቀየር ይሆናል። በመሆኑም አሁን የደረስንበትን የትግል ምዕራፍ ከግምት በማስገባት፣ ፓርቲዉ ነፃነት፣እኩልነትና ወንድማማችነት ለማስፈን ህዝቡን በመምራት የሚያደርጋቸዉን ትግሎች፣ በትግሉም የሚያስመዘግባቸዉን ድሎች እና የኦሮሞ ህዝብ እና የኢትዮጵያዉያንን መፃኢ ብሩህ ተስፋን በሚያሳይና አነቃቂ በሆነ መልኩ የሚዘጋጅ ይሆናል።

Oromo Democratic Party (ODP)

የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) አሁን የደረስንበትን የትግል ምዕራፍ ከግንዛቤ በማስገባት በሀገራችን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ጠንካራ እና ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ ለመቀጠል በማሰብ ፓርቲዉን ሪብራንድ ለማድረግ ወስኗል። ቀጣይ በሚደረገዉ የፓርቲዉ ጉባዔም ፓርቲዉ አዲስ ስያሜ፣ አዲስ ድርጅታዊ አርማ እና አዲስ ድርጅታዊ መዝሙር ይኖረዋል።

1.አዲሱ የፓርቲዉ ስያሜ Oromo Democratic Party (ODP) እንዲሆን መነሻ ሀሳብ ቀርቧል።

2.ፓርቲዉ በዚህ የሪብራንዲንግ ሂደት የፖለቲካ ፕሮግራም ማሻሻያ አያደርግም። ሆኖም የፓርቲዉ መተዳደሪያ ደንብ አንዳንድ አንቀፆች ላይ ማሻሻዎች ሊደረጉ ይችላሉ። ፓርቲዉ የኢህአዴግ አባል ድርጅት ሆኖ ይቀጥላል።

3.የፓርቲዉ አርማ በሶስት አማራጮች የቀረበ ሲሆን የኦሮሞን ህዝብ የዴሞክራሲ ዕሴቶች፣ የገዳ ስርዓት ህብረቀለማት እና የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ነፃነት፣እኩልነትና ወንድማማችነት የሰፈነባት በኢኮኖሚ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚያደርገዉ ጥረት ፓርቲዉ የመሪነት ሚናዉን በብቃት የሚወጣ መሆኑን ታሳቢ ያደረገ ነዉ። ከዚህ በፊት የዉዝግብ እና የልዩነት መነሻ የነብሩ የቀለማት አቀማመጥ ቅደም ተከተል እና በዓርማው ላይ የሚታየው ኦዳ ላይ ማስተካከያዎች ተደረገዋል። አዳዉ ባለ ባላ ከመሆን ይልቅ ወጥ እና ድፍን ሆኖ እንዲስተካክል ተደርጓል። ይህም የኦሮሞን ህዝብ ጠንካራ አንድነት ለማሳየት የቀረበ ነዉ። ከሶስቱ አማራጮች የፓርቲዉ አባላት በስፋት ከተወያዩበትና ማሻሻያዎች ከተደርጉበት በሗላ የተመረጠዉ አርማ ለጉባዔ ቀርቦ የሚፀድቅ ይሆናል።

4.እስካሁን ኦህዴድ ከአርማ በተጨማሪ ድርጅታዊ ባንዲራ አገልግሎት ላይ ሲዉል ነበር። ከቀጣይ ጉባዔ በሗላ ፓርቲዉ በሎጎዉ ብቻ የሚወከል ይሆናል። የፓርቲ ባንዲራ አይኖረዉም።

5.ኦህዴድ ባለፉት 27 ዓመታት ሲጠቀምበት የነበዉ “ Roorroo Miidhaa Keenyaa…” የሚለው መዝሙር ባለፉት ስርዓቶች የነበረዉን ጭቆናና ግፍ ብቻ አጉልቶ የሚያሳይ፣ ብሩህ ተስፋ እና መነቃቃትን ከመፍጠር አኳያ ክፍትቶች ያሉበት በመሆኑ በአዲስ መዝሙር የሚቀየር ይሆናል። በመሆኑም አሁን የደረስንበትን የትግል ምዕራፍ ከግምት በማስገባት፣ ፓርቲዉ ነፃነት፣እኩልነትና ወንድማማችነት ለማስፈን ህዝቡን በመምራት የሚያደርጋቸዉን ትግሎች፣ በትግሉም የሚያስመዘግባቸዉን ድሎች እና የኦሮሞ ህዝብ እና የኢትዮጵያዉያንን መፃኢ ብሩህ ተስፋን በሚያሳይና አነቃቂ በሆነ መልኩ የሚዘጋጅ ይሆናል።

6.በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በሀገራችን እየተደረገ ያለዉን እንቅስቃሴ ተከትሎ የኦሮሞን ህዝብ አጀንዳ ይዘዉ በሰላማዊም ሆነ የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ በርካታ ድርጅቶች ወደሀገራቸዉ ተመልሰዉ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ይታወቃል። በዚህ አጋጣሚ እነዚህ ድርጅቶች እንደ ድርጅትም ሆነ እንደግለሰብ የፓርቲያችንን የፖለቲካ ፕሮግራም ተቀብለዉ ለመንቀሳቀስ ፈቃደኛ እስከሆኑ ድረስ ፓርቲያችን አብሮ ለመታገል ዝግጁነቱን ያረጋግጣል።

Addisu Arega Kitessa

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች
0Shares
0